Page 19 - Aluma-Amaranthus for design 26.04.14
P. 19
13
ቅጠሎች፣ ለስላሳ ግንዶች፣ እና አፍላ አበባዎች የተለያዩ ምግቦች ውስጥ በመጨመር መመገብ ይቻላል፡፡ ቅጠሎቹ
በሚያበስሉበት ወቅት ምንም እንኳን አብዛኛው ቀለም የሚወጣ ቢሆንም ቅጠሎቹ ደስ የሚል አረንጓዴ ቀለም
ይይዛሉ እንዲሁም ለስላሳ፤ የማይሻክሩ እና ጥሩ ጣእም አላቸው። ቅጠሎቹ እንዲለሰልሱ ጥቂት ደቂቃዎችን ብቻ
ማብሰል ይጠይቃሉ፡፡ ቅጠሎቹ ከስጋ ጋር ወይንም ከአሳ ጋር አብሮ በዘይት በመጥበስ መጠቀም ይቻላል፡፡ ቅጠሉ
እንዲሁ ወደ ሾርባዎች ይጨመራል። በአገራችን ቅጠሉ እንደ ጎመን ተቀቅሎ ይበላል፡፡ የተቀቀለ የአሉማ ቅጠል
ጣዕሙ ከጎመን በተሻለ ይጣፍጣል፡፡
የአሉማ እህል በእሳት በሚቆላበት ጊዜ እንደ ፈንዲሻ ይፈነድሻል ጥሩ ጣእምና ቃና አለው፡፡ ሆኖም ግን፣ በብዙ
አካባቢዎች የአሉማ እህል ለስለስ ባለ ሙቀት ከታመሰ በኋላ ይፈጫል፡፡ በዚህ መንገድ የተሰራ ዳቦ ለስላሳ ፣
በምግብ ንጥረ ነገር የበለጸገ፤ ጣዕም ያለው እና ግሉትን ለማይስማማቸው ሰዎች በተለይ ጥቅም ላይ ይውላል።
ስስና ለስላሳ ቂጣ (ፓንኬክ መሰል ቻፓቲ) በጥሩ ሁኔታ ከእህሉ ማዘጋጀት ይቻላል፡፡
የኢ-ንጥረ
መቀነሻ
ቆያና
ማ
4.
4. የምግብ ማቆያና የኢ-ንጥረ ምግብ መቀነሻ ዘዴዎች
ዘዴዎች
ምግብ
የምግብ
አሉማ ኢ-ንጥረ ምግብ የሆኑትን እንደ ፊኖሊክስ፣ ሳፖኖኒን፣ ታኒን፣ ፋይቲክ አሲድ፣ ኦክዛሌቶች፣ ፕሮቴዝ
ኢንሂቢተሮች፤ ናይትሬቶች፣ ፖሊፌኔሎችና እና ሌሎች በውስጣቸው ይዘዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ኦክዛሌቶችና እና
ናይትሬቶች አሉማን ለምግብነት ሲውል የበለጠ አሳሳቢ ናቸው፡፡ ሆኖም የአሉማ ቅጠል በፈላ ውሃ በማንገርገብና
ውሃውን በመድፋት ኢ ንጥረ ምግቦችን መቀነስ ይቻላል፡፡ በአሉማ እህል ውስጥ ያለውን ፋይቲክ አሲድ
በመቀቀል፤ በማመስ (ማፈንደሽ) ወይም በማብቀል መጠኑን መቀነስ ይቻላል፡፡ ታኒንን፤ፕሮቴዝ ኢንሂቢተሮችንና
ፖሊፌኔሎች በምግብ ዝግጅት ወቅት ከፍተኛ ሙቀት በመጠቀም መቀነስ ይቻላል፡፡
5. አማራጭ የምግብ አዘጋጃጀትና እሴት መጨመር ጉዳዮች
5. አማ ራጭ የምግብ አዘጋጃጀትና እሴ ት መ ጨመር ጉዳዮች
አሉማ ለቁርስ በሚሆኑ ምግቦች፣ ዳቦ ቤቶች፣ ከግሉተን ነፃ የሆኑ ምግቦች ውስጥ እንደ ጥሬ እቃነት ያገለግላል።
በተለይም ከስንዴና ከሌሎች እህሎች ጋር በማደባለቅ የተለያዩ ምግቦች በፋብሪካ ደረጃ ማቀነባበር ይቻላል፡፡
በላቲን አሜሪካና ሌሎች አገሮች ለስላሳና ቀጭን ቂጣ (ቶርቲያና ቻፓቲ) ለማዘጋጀት ይጠቀሙበታል፡፡
ዱ
ገቡ
የሚ
ሊወሰ
ጥንቃቄዎች
6. በዝግጅት ሂደት ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች
6.
በ
ሂደት
ዝግጅት
የአሉማ ቅጠልም ሆነ እህል እንደ ግብዓት የሚጠቀሙ የተለያዩ የምግብ አይነቶች ሲዘጋጁ የምግቡን ጥራትና
የአሉማ (Amaranthus spp.) ሰብል አመራረት እና አጠቃቀም ፓኬ ጅ
የአሉማ (Amaranthus spp.) ሰብል አመራረት እና አጠቃቀም ፓኬጅ