Page 20 - Aluma-Amaranthus for design 26.04.14
P. 20
14
ደህንነት ለመጠበቅ ንፅህናን መጠበቅ መሰረታዊ እና ቁልፍ ተግባር ነው፡፡ ንጽህና ምግቡ ከሚበስልበት ወይም
ከኩሽና ንፅህና አጠባበቅ ጀምሮ፣ የምግቡ ማዘጋጃ ቁስ ንጽህናን መጠበቅ እና የምግብ አዘጋጅ ግለሰብ የግል
ንፅህናን የሚያጠቃልል ተግባር ነው:፡ በዚህ መሰረት ለምግብነት የሚውሉ የምግብ አይነቶችን የምናዘጋጅ ከሆነ
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መርሆዎች ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
o የምግብ ማብሰያ ቦታን /ኩሽናን/ ንፅህናውን በመጠበቅ እና የሚበስለውንም ምግብ ከተለያዩ በካይ
ተባዮች መከላከል፣
o ምግብን የሚያበስሉ ከሆነ የእጅዎን ጥፍር ማሳጠርና ንጽህናውን በአግባቡ መጠበቅ
ያስፈልጋል፣ምግብን ከማዘጋጀቱ በፊትም ሆነ የዝግጅት ሂደቱ ረዘም በሚልበት ወቅት በምግቡ
ዝግጅት ሂደቱ መካከል እጅዎን በደንብ በሳሙናና ለብ ባለ ውሃ መታጠብ፣
o ምግብን ለማዘጋጀት የምንገለገልባቸውን ቁሳቁሶች በፈላ ውሃ እና በሳሙና በደንብ ካጠብናቸው
በኋላ በንፁህ ውሃ በማለቅለቅ በፈላ ውሃ ውስጥ በመቀቀል /sterilize/ በአግባቡ ማድረቅ፣
o በማንኛውም መልኩ ምግብን በሚያዘጋጁበት ወቅት ምግቡን በእጅ በቀጥታ ከመንካት ይልቅ እንደ
ማማሰያና ማንኪያ ያሉ ቁሶችን መጠቀም፤
o ፀጉር በተለይ ለሴቶች ረዥም ከሆነ ጠቅልለው በማሰር በሻሽ መሸፈን ይኖርበታል፣
o ምግብ በሚበስልበት ጊዜና ቦታ ትንባሆ/ሲጋራ አለማጤስ፤ የሚያስነጥስና የሚያስል ከሆነም አፍና
አፍንጫን በክንዳችን በመሸፈንና ከምግቡ ላይ ፊትን ዘወር በማድረግ በማስነጠስና ማሳል ምግቡን
ከብክለት መከላከል ያስፈልጋል፣
o ለምግብ ማብሰያ እቃ ማጠቢያ የሚያገለግሉ የተለያዩ ሳሙናዎች በተቻለ መጠን ከመጠቀማችን
በፊት የምግብ ደረጃ እንዳላቸው ማረጋገጥ፤ ከተጠቀምን በኋላ በአግባቡ ማለቅለቅ የማጠቢያው
ኬሚካል ቅሪት በእቃው ላይ እንዳይቀር በማድረግ ከምግብ ወለድ በሽታዎች ለመከላከል
የሚጠቅሙ መርሆዎች በመሆናቸው ተግባራዊ ማድረግ ይመከራል፡፡
o የምግብ ማጓጓዣ፣ መያዣ፣ ማከማቻ፣ ማብሰያ ቦታዎችን እና ቁሶችን በአግባቡ በሞቀ ውሃና የምግብ
ደረጃ በያዙ ማጽጃ ኬሚካሎችና ሳኒታይዘሮች ማጠብና በአግባቡ ማለቅለቅ ይመከራል፣
ጅ
የአሉማ (Amaranthus spp.) ሰብል አመራረት እና አጠቃቀም ፓኬጅ
የአሉማ (Amaranthus spp.) ሰብል አመራረት እና አጠቃቀም ፓኬ