Page 22 - Aluma-Amaranthus for design 26.04.14
P. 22
16
እራፍ ሶስት
ምእራፍ ሶስት
ም
ሰ ሰብሉን ለማስተዋቅና ለማላመድ የሚከናነወኑ የኤክስቴንሽን ኮሚኒኬሽን ተግባራት፡-
• ሰብሉን በማስተዋወቅና ማላመድ ሂደት በሁለት አካት መካከል የሚደረግ ግንኙነት (Two way
communication) ተግባራዊ ማድረግ፣
• በአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላትና በሞዴል አርሶ አደሮች ሰርቶ ማሳያ በማካሄድ የቅምሻ ፕሮግራም
እንዲኖር በማድረግ፣
• የሰብሉን ከማምረት እስከ መመገብ ያለውን ሂደት ለማሳለጥ ግንባር ቀደም የሆኑ አርሶ/አርብቶ/
ከፊል አርብቶ አደር እማወራ እና አባወራ መምረጥና ማስተዋወቅ፣
• የሰው ኃይል ማደራጀትና የባለሙያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና መስጠት፣
• አርሶ/አርብቶ/ከፊል አርብቶ አደር ሥልጠና መስጠት፣
• ሰብሉን ለማምረት የግብዓት አቅርቦት ፍላጎት መፍጠር፣
• በሰብሉ ምርት ላይ እሴት በመጨመር የሚዘጋጁ የተለያዩ የምግብ ዓይነቶችን ማስተዋወቅና የሰብሉን
ተፈላጊነት እንዲጨምር ማድረግ፣
• የሰብሉን ምርት በተለያየ መንገድ መጠቀም እንዲችሉ ለማቀነባበሪያ ማዕከላት የማስተዋወቅ ሥራ
ማከናወን፣
• በኤግዚቢሽን ማዕከላት ላይ ከሰብሉ የሚዘጋጁ የተለያዩ ምግቦችን ማስተዋወቅ፣
• የምግብ ዐውደ ርእይ በማዘጋጀት እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚዘጋጁ የምግብ አይነቶችን
በቅምሻ እንዲተዋወቁ ማድረግ፣
• የሰብሉን ከማምረት እስከ መመገብ ያለውን ሰንሰለት ለማሳለጥና ለማስረፅ በትላልቅ ሆቴሎች
የማላመድ ስራ መስራት
• የገበያ ትስስር ከሚመለከተው ጋር መፍጠር፣
• የተለያዩ የመልዕክት የማስተላለፊያ ዘዴዎችን ተጠቅሞ ሰብሉንና ከሰብሉ የሚዘጋጁ ምግቦቸን
በሚከተሉት የግንኙነት ዘዴዎች በመጠቀም ማስተዋወቅ፣
ጅ
የአሉማ (Amaranthus spp.) ሰብል አመራረት እና አጠቃቀም ፓኬጅ
የአሉማ (Amaranthus spp.) ሰብል አመራረት እና አጠቃቀም ፓኬ