Page 15 - Aluma-Amaranthus for design 26.04.14
P. 15
9
ድህረ
የሰብል
አሰባሰብና
ምርት
5. 5. የሰብል አሰባሰብና ድህረ ምርት አያያዝ
አያያዝ
5.1.
የሰብል አሰባሰብ
5.1. የሰብል አሰባሰብ
ዘሩ በዋና ማሳ ላይ በቀጥታ ሲዘራ ለጋ ቅጠሎች ከአራት እስከ አምስት ሳምንታት ሊነቀሉ ወይም ሊቆረጡና
ለምግብነት ሊውሉ ይችላሉ። ረዘም ላለ ጊዜ በተከታታይ ምርት መሰብሰብ ሲያስፈልግ የጎን እድገትን
ለማበረታታት ሰብሉ ከመሬት በ20 ሴ.ሜ ከፍታ ላይ ሊቆረጥ ይችላል። ችግኝ አፍልቶ በማዛመት ሲመረት፤ ከተዘራ
ከስምንት ሳምንታት በኋላ ወይም ከተተከሉ ከአራት ሳምንታት በኋላ ቅጠሎቹን መሰብሰብ ይጀመራል። አነስተኛ
መጠን ያላቸው ቅጠሎች በየቀኑ ሊሰበሰቡ ይችላሉ። ሆኖም ግን ጥሩ ምርት ለመሰብሰብ፤ የሁለት ሳምንታት
ክፍተቶች ቢኖር ይመከራል። አበቦችን በማስወገድ የቅጠል ምርት ለተወሰነ ጊዜ እንዲቀጥል ማድረግ ይቻላል።
ቅጠሎች በሁለት መንገዶች ሊሰበሰቡ ይችላሉ፤ እነዚህም እያንዳንዱ ቅጠሎች በአጅ መልቀምና ቅጠሎችን ከነለጋ
ቅርንጫፎች መቀንጠስ ናቸው። ቅጠሎች የሚሰበሰቡት በእጅ ነው።
በሰብሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ በቅጠል መሰብሰብ ወቅት ጥንቃቄ መደረግ አለበት። አበባ ሲጀምር ቅጠል
መሰብሰብ መቆም ይኖርበታል፤ ቅጠሎቹም ፋይበር እና ለሰው ፍጆታ የማይመቹ ይሆናሉ።
የእህል አሉማ የእፅዋቱ/የጭንቅላቱ ቀለም ከአረንጓዴ ወደ ወርቃማ እና የዘር ጥላ በሚቀየርበት ጊዜ ወዲያውኑ
ሰብሉ እንዲሰበሰብ ይመከራል። በሚሰበሰብበት ወቅት ጭንቅላቱን አጣጥፈው ወደሚሰበሰብበት ከረጢት ውስጥ
መጨመርና ከግንዱ ተነጥሎ ወደ መያዣው ውስጥ እንዲወድቅ የአበባውን ግንድ መቁረጥ። ዘሩ በጣም ትንንሽ
ስለሆነ መሰብሰብ ያለበት ዘሩን ሊያፈስ በማይችል እቃ መሆን ይኖርበታል። በወቅቱ ካልተሰበሰበ ማሳ ላይ ሊረግፍ
ይችላል እንዲሁም በመዘግየት ምክንያት እስከ 50% ወይም ከዚያ በላይ የዘር ምርት ሊቀንስ ይችላል።
ምስል 2. ለምርት መሰብሰብ የደረሰ እና ምርቱ የተሰበሰበ የአሉማ ሰብልMምንጭ፡- መልካሳ ግብርና መምርምር ማዕከል
የአሉማ (Amaranthus spp.) ሰብል አመራረት እና አጠቃቀም ፓኬ ጅ
የአሉማ (Amaranthus spp.) ሰብል አመራረት እና አጠቃቀም ፓኬጅ