Page 10 - Aluma-Amaranthus for design 26.04.14
P. 10

4
            •   አሉማ በተለያየ የአፈር አይነት የሚበቅል ሲሆን፤ በተለይ ዉኃ የማይቋጥር መሬት እና ጥሩ የብስባሽ

               (Organic matter) ይዘት ያለው ቢሆን ይመረጣል።

            •   አሉማ የአፈር ኮምጣጣነቱ (pH) ከ 4.3 እስከ 8.0 የሆነ አፈር ላይ ቢበቅልም፤ ኮምጣጣነታቸዉ ከ 5.5

               እስከ 7.0 የሆነ አፈር ጥሩ ምርት ያስገኛል፡፡


            የተሻሻሉ


                        ዘዴዎች

        3.  3.   የተሻሻሉ አመራረት ዘዴዎች
                  አመራረት
          3.1.    የማሳ   ዝግጅት
               የማሳ ዝግጅት
          3.1.
        የአሉማን ሰብል ለማምረት ማሳው በደረቅ ወቅት ታርሶ፤ ተከስክሶ፤ አረሙ በሚገባ ተጎልጉሎ መውጣት አለበት፡፡
        የዘሩ መጠን ትንሽ ስለሆነ መሬቱ ከመዘራቱ በፊት ተደጋግሞ መታረስና መለስለስ ይኖርበታል።
               የዝርያ
          3.2.
          3.2.     የዝርያ መረጣ
                    መረጣ

         በሀገር ደረጃ ለአትክልት የሚሆኑ ሁለት የአሉማ ሰብል ዝርያዎች የማላመድ ሙከራ በመስራት ተለቀዋል:፡ የዚህ
        ሰብል/ዝርያዎች አመራረትና አጠቃቀም እውቀት ውስን በመሆኑ ሰፊ የማስተዋወቅ ስራ ያስፈልጋል፡በተጨማሪም
        ሌሎች ዝርያዎችን/ ብዝሀ ዘሮችን ከውጪ በማስገባት ወይም አገር በቀል የሆኑትን በማሰባሰብ የዝርያ መረጣና
        ማሻሻያ ስራዎች መሰራት ያስፈልጋል፡፡


         ለምግብነት የሚዉለው አሉማ ሁለት አይነቴዎችን (species) የያዘ ሲሆን የመጀመሪያው አትክልት አሉማ (green
        leafy vegetable) ሲሆን Amaranth dubius and A. tricolor የሚባሉትን ያጠቃልላል፡፡ አትክልት አሉማ

        በግንዱ ላይ የአበባ ግንዶች የሚያወጣ ሲሆን ዘሮቻቸው ከእህል ዓይነቶች ጋር ሲወዳደሩ የሚያብረቀርቁ፣ ጥቁር
        እና መጠናቸው ያነሱ ናቸው። በአንድ ግራም ውስጥ እስከ 3000 ዘሮች አሉት። ሁለተኛው የእህል ዓይነቴዎች

        (grain) የሚባሉት ደግሞ A. hypochondrius እና A. creuntusን ያካትታሉ። የእህል ዓይነቶች በሰብሉ ጫፍ
        ላይ ተለቅ ያለ የአበባ ግንድ ይኖረዋል። የዘር ቀለሙ ከነጭ ክሬም፣ ከደማቅ እስከ ፈዛዛ አሏቸው። ሁሉም የአሉማ
        ሰብል ዝርያዎች ግን የቅጠል ምርት መጠናቸው ቢለያይም ለምግብነት ሊውሉ ይችላሉ።





                 ሰንጠረዥ፡ 1 ከውጪ በማስገባት የማላመድ ስራዎች ተሰርቶ ለሀገር ውስጥ የተለቀቁ

                               ለአትክልት የሚሆኑ የአሉማ ዝርያዎች
        የአሉማ (Amaranthus spp.) ሰብል አመራረት እና አጠቃቀም ፓኬ ጅ
        የአሉማ (Amaranthus spp.) ሰብል አመራረት እና አጠቃቀም ፓኬጅ
   5   6   7   8   9   10   11   12   13   14   15