Page 12 - Aluma-Amaranthus for design 26.04.14
P. 12
6
ይቻላል። የአሉማ ዘር ሲዘራ በጣም መሬት ውስጥ ስለማይገባ በጎርፍ ሊወሰድ ስለሚችል በማሳው ላይ የጎርፍ
(flood) መከላከያ ስራዎች ያስፈልጋል፡፡
ማሳሳት (Thinning)፡- ሰብሉ ከተዘራ በኋላ ቁመቱ 10 ሴ.ሜ ሲደርስ በተከላ ርቀት ማሳሳት ይኖርበታል። ደካማ
እና የተበላሹ ተክሎች ተነቅለው ጠንካራ የሆኑት ይተዋሉ። የመጀመሪያው ማሳሳት የሚከናወነው የበዛውን
ለመቀነስ፣ ጥሩ የአየር ዝውውር እንዲኖር እና ብርሃን ዘልቆ እንዲገባ ሲሆን፤ ቀጣይ ማሳሳት እንደ አስፈላጊነቱ
መደረግ አለበት። በማሳሳት ወቅት የተነቀሉ ቅጠሎች እንደ አትክልት ሊያገለግሉ ወይም ለከብቶች መኖ ሊውሉ
ይችላሉ።
ምስል 1. በመስመር እና በመደብ የተተከለ የአሉማ ሰብል
ምንጭ፡- መልካሳ ግብርና ምርምር ማዕከል
3.5. የችግኝ መደብ ዝግጅት
3.5. የችግኝ መደብ ዝግጅት
እንደማንኛውም የአትክልት ሰብል የችግኝ ማፍያ ቦታ ሲመረጥ የሰብል ፈረቃን ማዕከል ያደረገ መሆን ይኖርበታል፡
፡ መሬቱ ቀድሞ የአሉማ ሰብልና ተዛማጅ ቤተሰብ የሆኑ ሰብሎች ያልተመረቱበት መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
• የሚዘጋጀው መደብ ከፍ ብሎ ሪጅ (ridge) በማውጣት 1 ሜትር ስፋትና እና 5 ወይም 10 ሜትር ቁመት
ሊኖረው ይገባል፡፡ በመደቦች መካከል 40-50 ሳ.ሜ. መተላለፊያ መንገድ መተዉ ያስፈልጋል፡፡
• የመደቡን ቁመት ተከትሎ በየ 15 ሳ.ሜ. ርቀት አግድም መስመር ማውጣት፣
የአሉማ (Amaranthus spp.) ሰብል አመራረት እና አጠቃቀም ፓኬጅ
የአሉማ (Amaranthus spp.) ሰብል አመራረት እና አጠቃቀም ፓኬ ጅ