Page 28 - Ayinie Magazine
P. 28

የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ



                የመጀመሪያው የብሌን ንቅለ ተከላ ተጠቃሚ








        መሀመድ  አብዲ  ሁሴን  ከበርካታ  ዓመታት  በኋላ  ወደ  ኢትዮጵያ  ቅርበት አለ፡፡ ይህንን ለሚያውቅ የኔ ዓይነት ሰው እንደ ሌላው ጊዜ ሁሉ
        የዓይን  ባንክ  መምጣቱ  ነው፡፡  መገረምና  ፈገግታ  ፊቱ  ላይ  ይነበባል፡    የቅርብት  ሰላምታ  ነው  ብሎ  ሊያልፈው  የሚችል  አይደለም  -  ይህ
        ፡  በ‹‹ሱማሊ››  ቃና  ሰላምታ  ሲሰጠኝ  አወኩት፤  አፉ  ይጣፍጣል፡        የመሀመድ ሁኔታ፡፡
        ፡  ገራገርነት  ይታይበታል፤  ሰላምታው  የጠበቀና  የናፍቆት  መሆኑን
        የሚያሳብቅበት ቁልጭልጭታው በንግግርም ታጀበ፡፡                         ነውና!!
                                                              መሀመድ ማለት የመጀመሪያው የዓይን ባንኩ ልጅ ነው! አዎ ልጅ፡፡

                                                              መሀመድ ዓይን ባንኩ በ1995 ዓ.ም ሰኔ 26 እንደተቋቋመ በማግስቱ
                                                              በዶ/ር ዮናስ አማካኝነት ንቅለ ተከላ ተከናውኖለት ማየት የቻለ ፍሬ
                                                              ነው፡፡
                                                              ነገረኝ  ፤  አዎ  እኔ  ነኝ  የመጀመሪያው  አለኝ፡፡  ዶ/ር  ዮናስ  የፃፈውን
                                                              ማስታወሻም አቀበለኝ፡፡ ምስክርነቱን የሰጠበት ማስታወሻ ነው - አሁን
                                                              ዶክመንት ማጋላበጥ አያስፈልግም፡፡

                                                              አውራኝ አልኩት ፤ ጀመረልኝ ታሪኩን፡፡
                                                              ‹‹ልጅ እያለሁ ዓይኔን ያሳክከኝ ነበር፡፡ በባህላዊ መንገድ ለማሳከም
                                                              ቤተሰቦቼ  ቢጥሩም  ጭራሽ  ሙሉ  በመሉ  ጠፋ፡፡  በዚያን  ጊዜ  ወደ
                                                              ሀኪም ቤት አመጡኝ፡፡ ወደ ዓይን ባንኩ ከመምጣቴ በፊት በዳግማዊ
                                                              ምኒልክ ሆስፒታል የዓይን ህክምና ክፍል ምርመራ ተደርጎልኝ ህክምና
                                                              እየተከታተልኩ ነበር፤ በ1995 ዓ.ም፡፡ ሀኪሜም ዶ/ር ዮናስ ነበር፡
                                                              ፡  የምርመራ  ውጤቱም  የብሌን  ጠባሳ  መሆኑ  ታወቀ፡፡  ዶ/ር  ዮናስ
                                                              ሰለሁኔታው ለአባቴ ከነገረው በኋላ ቤተሰባችን ሲጨነቅ ትዝ ይለኛል፡፡
                                                              ያኔ ገና የ13 ዓመት ልጅ ነበርኩ፡፡››

                                                              መሀመድ ትረካውን ቀጠለ፡፡
                                                              ‹‹በወቅቱ  ቤተሰቦቹ  ወደ  ውጭ  አገር  ወስደው  ሊያሳክሙኝ  ወሰኑ፡፡
                                                              አስፈላጊው ሁኔታ ሁሉ ተሟላና ፕሮሰስ ተጀመረ›› አለኝ፡፡
                                                              ከዚያስ የሚለው የኔ ጥያቄ ነበር፡፡

        ‹‹በስንት ዓመቴ መሰለህ የመጣሁት፤ በጣም ብዙ ጊዜ ሆነኝ፡፡ ዓይን            ‹‹የአየር ትኬት ለመግዛት ዝግጅቱ በተጠናቀቀበት ወቅት ዶ/ር ዮናስ
        ባንኮች ደህና ናችሁ ሁላችሁ?›› አለኝ፡፡ የቀድሞ ሰራተኞችን ስም             አባቴ  ጋ  ደወለ፡፡  የኢትዮጵያ  የዓይን  ባንክ  ሊከፈት  ስለሆነ  አሁን
        እየጠራ ሁሉ ጠየቀኝ፤ የማውቃቸውም የማላውቃቸውም አሉበት፡፡ ግን              መታከም ይችላል፡ አለው፡፡ ወደ ውጭ ለመሄድ ፕሮሰስ ላይ መሆናችንን
        ጥያቄው የቤተሰብ ያህል ነበር - ብዙ ዘመን ባጅቶ ከሩቅ እንደመጣ             የሚያውቅ አልመሰለኝም፡፡›› አለ መሀመድ፡፡
        ዘመድ ነው ሁሉ ነገሩ፡፡
                                                              ሁሉ ነገር አልቆ ትኬት በሚጠበቅበት ቤተሰብ ይህ ዜና ምን መልክ
        እርግጥ ነው በኢትዮጵያ የዓይን ባንክ አማካኝነት የብሌን ንቅለ ተከላ           ነበረው፡፡ መሀመድን ጠየኩት፡፡
        በተሰራላቸው  ታካሚዎችና  በተቋሙ  መካከል  ከዝምድና  ያልተናነሰ
   23   24   25   26   27   28   29   30   31   32   33