Page 29 - Ayinie Magazine
P. 29

የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ


        ‹‹እናቴና  አባቴ  እንተደተከራከሩ  ትዝ  ይለኛል፡፡  ነገሩ  ካለፈና  እኔም  ካደኩ
 የመጀመሪያው የብሌን ንቅለ ተከላ ተጠቃሚ   በኋላ እንዳወሩኝ እዚህ ይታከም ወይስ ውጭ አገር በሚለው ነበር የተከራከሩት፡፡
        በመጨረሻ እዚህ መታከሜ ግድ ሆነ፡፡ ለነገሩ ቤተሰቦቼም ሀብታም ስለሆኑ አልነበረም፡
        ፡ የልጃቸው ዓይን መጥፋቱ አንገብግቧቸው እንጅ›› አለ እየሳቀ፡፡

        ከዚያስ - አልኩት አሁንም፡፡
        ‹‹በኢትዮጵያ የዓይን ባንክ ከህብረተሰቡ ሰብስቦ በአዘጋጀው ብሌን አማካኝነት
        ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ዶ/ር ዮናስ ኦፕራሲዮኑን ሰራልኝ፡፡ የተሰራው አንድ
        ዓይኔ ብቻ ነው፡፡ ይኸው ከዚያ ጊዜ አንስቶ በጥሩ ሁኔታ እያየሁበት ነው፡፡ አሁን
        የመጣሁት ከጅግጅጋ ሁለተኛው ደግሞ እንዲሰራልኝ ለመጠየቅ ነው ዶ/ር ዮናስን››
        አለ፡፡
        ንቅለ ተከላ የተሰራለት አንድ ዓይኑን ተጠቅሞ በእነዚህ 14 ዓመታት ምን አደረገ ፤
        በህይወቱስ ምን ለውጥ አገኘ የሚለው ጉጉቴን አውጥቼ ነገርኩት፡፡ እሱም ቀጠለ፡፡
        ‹‹ያቋረጥኩትን ትምህርቴን ቀጠልኩ፡፡ በዚች ውብ ዓይኔ የፈለኩትን አደርጋለሁ፡፡
        ስፖርታዊ ውድድሮችን እወዳደራለሁ፡፡ ከጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲም ተመርቅሁ፡፡ በአሁኑ
        ሰዓት መኪና እንኳን ያለምንም ችግር እየነዳሁ ነው፡፡›› ደስታውን በሁለመናው
        እየገለፀ መሆኑን ለመገንዘብ በቂ ነው፡፡
        ‹‹እዚያ ከምኖርበት ጅግጅጋ የሚያውቀኝ ሰው ሁሉ ደስ ይለዋል፡፡ እናቴ ያን ጊዜ
        አይሆንም  ብላ  እንዳላንገራገረች  ዛሬ  ከኔ  በላይ  ለጌረቤት  ሁሉ  ወደ  ዓይን  ባንክ
        ሄዳችሁ ብሌን ጠይቁና በሀኪሞች ይቀየርላችሁ ትላለች፡፡ እኔን ያዩ ብዙዎች ወደዚህ
        መጥተው እንደታከሙና ማየት እንደቻሉ ይነግሩኛል፡፡››

        መሀመድ ቀጠለ፡፡

        ‹‹አሁን  ሁለተኛው  ዓይኔ  ብሌኑ  ንቅለ  ተከላ  እንዲደረግለት  ከዶ/ር  ዮናስ
        ጋር  ተስማምተናል፡፡  ግን  የብሌን  ወረፋ  እንዳለ  እናንተ  የዓይን  ባንክ  ሰራተኞች
        ነግራችሁኛል፡፡ መቼ ነው ግን የሚደርሰኝ ወረፋ›› አለኝ እየሳቀ፡፡

        ዛሬ ወይም ነገ ወይም ሳምንት ወይም የዛሬ ወር አልኩት፡፡ የምሬን ነው፡፡ ዓይን ባንኩ
        በልገሳ የሚያሰባስበውን ብሌን ቁጥር አስረግጦ መናገር አይችልም - ምክንያቱም                               ‹‹እንደዚህ
        ለገሾች ከህልፈት በኋላ ነውና የሚለግሱት፡፡
                                                                                     አይነት አሰራር
        ‹‹እንደ  ድሮው  አይደለም፡፡  አሁን  ብዙ  ወረፋ  የለም፡፡  በቅርቡ  ንቅለ  ተከላ
        እንደሚከናወንልህ  እገምታለሁ፡፡  ሆስፒታልን  መሰረት  ያደረገ  በብሌን  ልገሳ
        አማካሪዎች በኩል ቤተሰብ አስፈቅደን ሆስፒታል ሞት ሲያጋጥም ብሌን እየሰብሰብን                            ከጀመራችሁማ
        ስለሆነ ምናልባት በየዕለቱ ከሚያጋጥመው ሞት አንፃር አማካሪዎቻችን ቤተሰብ
                                                                                    በቅርቡ ሁለተኛዋ
        ሊፈቅድላቸው ይችላል›› አልኩት ዝርዝሩን ገልጬ፡፡
        ‹‹እንደዚህ  አይነት  አሰራር  ከጀመራችሁማ  በቅርቡ  ሁለተኛዋ  ዓይኔም
        ትበራለች!››  አለኝ  በትልቅ  ተስፋ፡፡  በዚያች  የዛሬ  14  ዓመት  በተቀየረችለት                           ዓይኔም
        ብሌኑም እየሳቀ - ተስፋንም እየሰነቀ፡፡
                                                                                      ትበራለች!››
        ተስፋውን በበለጠ ተስፋ ሞልቼ ላኩት - ወደ ጅግጅጋ፡፡

        እናንተ እና እኔ እንዲሁም ቤተሰቦቻችን በምደርገው ልገሳ ላይ የመመስረት ውጤቱ
        ይኸው ነው - ተስፋ - ያውም ጨለማን የመግፈፍ ብርሃንን የማጎናፀፍ !!!
   24   25   26   27   28   29   30   31   32   33   34