Page 34 - Ayinie Magazine
P. 34

ከሁለት  ዓመታት  በፊት  አንድ  የስልክ  ጥሪ  ወደ  ኢትዮጵያ  የዓይን  ባንክ  ይደርሳል፡፡
          ደዋዩ የዓይን ብሌናቸውን /የዓይን ብርሃን አሳላፊ መስታዎት/ ለመለገስ ቃል የገቡ
          መሆኑን  ይገልናጹና  ጤንነታቸው  እየተዳከመ  እንደመጣ  ይናገራሉ፡፡  ከሕልፈታቸው
          በኋላም  ብሌናቸው  ስለሚወሰድበት  ሁኔታ  ለመነጋገር  እንደሚፈልጉ  ይገልፃሉ፡፡  ይህ
          የሆነው ሕይወታቸው ሊያልፍ ሦስት ቀን ሲቀረው ነው፡፡ ይህ አጋጣሚ የስልክ ጥሪውን
          ለተቀበለችው የዓይን ባንኩ ባልደረባ አስገራሚ ነበር፡፡ ምክንያቱም በተለመደው አሰራር
          መሠረት አንድ ለጋሽ ሕይወቱ ካለፈ በኋላ በቤተሰብ አማካኝነት ይደወልላቸዋል እንጂ
          በቅርቡ ልሞት ነው የዓይን ብርሃን አሳላፊ መስታወቴን ውሰዱ ብሎ የሚደውል ሰው
          ስላልነበረ ነው፡፡ ባልደረባዋ ጥቂት አዋርታ፣ ደዋዩንም እጽናንታ ይሰነባባታሉ፡፡ በማግሥቱ
          መልሳ ስትደውል  ግን ስልካቸው ዝግ ስለነበር ከባድ ሀዘን ተሰማት፡፡ ሆኖም በሦስተኛው
          ቀን ከለጋሹ ቤተሰብ ስልክ ተደወለ፡፡ ‹‹መ/ር መብዐፅዮን በቅዱስ ያሬድ ሆስፒታል
          ሕይወታቸው  ስላለፈ  መጥታችሁ  ብሌናቸውን  አንሱ››  የሚል  መልዕክትም  ከስልኩ
          ተሰማ፡፡  የኢዮጵያ  የዓይን  ባንክ  ባለሙያዎችም  በቦታው  በመገኘት  የለጋሹን  ብሌን
          ሊወስዱ ቻሉ፡፡

          ከተመሠረተበት  ከ1995  ዓም  ጀምሮ  ድርጅቱ  ከላይ  የተጠቀሰውን  ጨምሮ  በሦስት
          ዓይነት  ዘዴዎች  የዓይን  ብሌኖችን  ይሰበስባል፡፡  ሁለኛው  ዓይነት  ዘዴ  ቀድመው  ቃል
          ካልገቡ ሰዎች ልገሳ የሚደረግበት መንገድ ነው፡፡ ሟቹ ስለዓይን ብሌን ልገሳ ባያውቅም
          ቤተሰቦቹ  ስለልገሳ  የሚያውቁ  ሲሆን  በሕልፈት  ጊዜ  ለዓይን  ባንኩ  ደውለው  ልገሳው
          ይደረጋል፡፡  ሦስተኛው  ዓይነት  ዘዴ  ደግሞ  ለጋሹም  ሆነ  በአካባቢው  ያሉ  ሰዎች  ስለ
          ዓይን ብሌን ልገሳ ምንም ዕውቀት ሳይኖራቸው ነው፡፡ ይህ የሚደረገው በጥቁር አንበሳና
          በጳውሎስ ሆስፒታሎች ባሉት ባለሙያዎች አማካኝነት የሟቹን ቤተሰቦች ስለ ዓይን ባንኩ
          በማስረዳትና እስኪረጋጉ ጠብቆ ልገሳውን እንዲያደርጉ በማስተማር ነው፡፡





                 ብሌኖቹ /የዓይን ብርሃን አሳላፊ

                  መስታወቶቹ/ ወዴት ይሄዳሉ?





          በ1998 ዓም በተደረገ አንድ አገር አቀፍ ጥናት ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች በዓይን ብሌን
          ጠባሳ መጠቃታቸው ታውቋል፡፡ የዓይን ብሌን ጠባሳ በልዩ ልዩ ምክንያቶች የሚከሰት
          ሲሆን  ለከፊልና  ሙሉ  ዓይነ  ስውርነት  ይዳርጋል፡፡  ሆኖም  በሕክምና  እርዳታ  መልሰው
          ብርሃናቸውን ማግኘት ይችላሉ፡፡ ግን በዓይን ብሌን ጠባሳ የተጎዱ ሰዎች መልሰው ማየት
          የሚችሉት  ብሌናቸው  ሲቀየር  ብቻ  ነው፡፡  ይህ  ሕክምና  የብሌን  ንቅለ  ተከላ  ይባላል፡፡
          የተጠቀሰው ጥናት ከተደረገ ዘጠኝ ዓመታት ተቆጥሯል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ይህ ቁጥር ምን
            32
   29   30   31   32   33   34   35   36   37   38   39