Page 35 - Ayinie Magazine
P. 35

ያክል ሊጨምር እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡

                                             በዚህ ችግር ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ቁጥር ጋር ሲናጸር በጣም ጥቂት ቢሆንም እስከ 2014
                                             እኤአ የዓይን ባንኩ ለ1067 ሰዎች የብሌን ንቅለ ተከላ እንዲያገኙ አስችሏል፡፡ በአገሪቱ
                                             ውስጥ  በአምስት  የተለያዩ  ቦታዎች  በሚገኙ  ዘጠኝ  ባለሙያዎቹም  በዓመት  እስከ  170
                                             ብሌኖችን ለታካሚዎቹ ይተክላል፡፡ ከእነዚህ ዕድለኞች አንዱ ቀሲስ አንዱዓለም ወልደትንሳኤ
                                             ናቸው፡፡

                                             ቀሲስ አንዱዓለም በኮተቤ አካባቢ የሚኖሩ የ57 ዓመት አባወራ ናቸው፡፡ የዓይን ሕመም
                                             የጀመራቸው ገና በልጅነታቸው ነበር፡፡ በሂደትም የግራ ዓይናቸው ሙሉ ለሙሉ ማየት አቆመ፡
                                             ፡ ቀኝ ዓይናቸውንም ያስቸግራቸው ጀመር፡፡ ስለዚህም ገና በልጅነት ዕድሜያቸው እየተመሩ
                                             ለመሄድ ተገደዱ፡፡ የቆሎ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ የዓይናቸው
                                             ችግር ተባብሷል፡፡ ዓይናቸው ውስጥ ፀጉር የመሰለ ነገር አበቀለ፡፡ በርካታ የግልና የመንግሥት
                                             የጤና ተቋማትን ጎበኙ፡፡ ነገር ግን መፍትሔ ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡

                                             በሰማኒያዎቹ መጨረሻ ላይ ሐረር በሚገኘው ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ውስጥ የሚሠሩ አንድ
                                             ዶክተር የቀሲስ አንዱዓለም ብሌን መቀየር እንደሚኖርበት ሆኖም ይህ ቴክኖሎጂ ወደ አገር
                                             ውስጥ ስላልገባ ውጭ አገር ካልሆነ በስተቀር ሊታከሙ እንደማይችሉ ይነግሯቸዋል፡፡ ስለዚህም
                                             ቀሲስ አንዱዓለም ይህ ዓይነቱ ሕክምና ወደ አገር ውስጥ እስኪገባ የግድ መጠበቅ ነበረባቸው፡
                                             ፡ በመጨረሻም በኢትዮጵያ የዓይን ባንክ አማካኝነት በ2001 ዓ.ም. የግራ ዓይናቸው
                                             ብሌን ሊቀየርላቸው ቻለ፡፡

                                             ‹‹አሁን ዓይን ሐኪም ቤት ግድግዳ ላይ ያሉትን መፈተኛ ጽሑፎች እስከ ስድስት ሜትር
                                             ርቀት ላይ አያለሁ፡፡ ለማንበብም ምንም አያስቸግረኝም፡፡ ጸሎቴን አደርጋለሁ፡፡ በመሥሪያ
                                             ቤትም ሥራዬን በሚገባ አከናውናለሁ›› ይላሉ አቧራ ለመከላከል መነጽር የሚያደርጉት
                                             ቀሲስ አንዱዓለም፡፡



                                               የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ምንድን ነው?





                                             ይህቺን ጽሑፍ ከማዘጋጀቴ በፊት የዓይን ብሌን ልገሳ ሲባል የማስበው ነገር ሙሉው የዓይናችን
                                             ክፍል ከሰውነታችን ነቅሎ ይወጣል የሚለው የተሳሳተ ግንዛቤ ነበር፡፡  ይህ አስተሳሰብ የበርካታ
                                             ሰዎችም እምነት ነው፡፡ ሆኖም የዓይን ብሌን ልገሳ ሲባል ዓይናችን ከነ ሙሉ አካሉ፤ ከነ
                                             ድቡልቡልነቱ  ይለገሳል  ማለት  አይደለም፡፡  ዓይን  ልዩ  ልዩ  ክፍሎች  ያሉት  ሲሆን  ከእነዚህ
                                             ውስጥ በእግሊዝኛ ኮርኒያ የሚባለው በአማርኛ ደግሞ ብሌን የሚባለው የዓይን ክፍል ብቻ
                                             ነው፡፡ በእርግጥ በተለምዶ ብሌን ብለን የምንጠራው ጥቁሩን የዓይናችን ክፍል ሲሆን ኮርኒያ
                                             ግን ይሄን ጥቁሩን የዓይናችን ክፍል የሚሸፍን መስታዎት መሰል ነገር ነው፡፡ ‹‹ከለጋሽ ላይ
                                                                                                       33
   30   31   32   33   34   35   36   37   38   39   40