Page 37 - Ayinie Magazine
P. 37
፡ በተጨማሪም በከተማው አንዳንድ ቦታዎች ላይ ካስቀመጥናቸው የእርዳታ
ማሰባሰቢያ ሳጥኖች ከሚገኘው ገንዘብ የተወሰነውን በመውሰድ ለዚህ ዓይነት
አገልግሎት እንዲውል ይደረጋል››፡፡
ዋናው ጠቃሚ ብርሃን ለምን ይቀበር!
ጉዳይ ለጋሾች የዓይን ብሌን ለመለገስ በርካቶች በደስታ ቃል የሚገቡ ቢሆንም ሌሎች
ለቤተሰብ በርካቶች ደግሞ አሁንም ፈቃደኞች አይሆኑም፡፡ ከሕልፈታቸውም በኋላ
ቢሆን ከሰውነት አካል ውስጥ የአንዱን መጉደል ሲያስቡት የሚያስፈራቸው
ብዙዎች ናቸው፡፡ እንደ ቀሲስ አንዱዓለም በሌሎች ልገሳ ተጠቃሚ የሆኑ
ማሳወቃቸው ሰዎች ደግሞ ‹‹ለሌላ ሰው የሚያገለግል ከሆነ እኔ የራሴንም መልሼ መናዘዝ
እፈልጋለሁ›› ይላሉ፡፡ ከዚህም በላይ ‹‹ጤናማ የሆናችሁም ሰዎች ይሄን
ነው፡፡ ብታደርጉ መልካም ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ አፈር ነው የሚበላው፡፡ ከሞትን ወዲያ ምን
ያደርግልናል?›› ሲሉ ብርሃን እንዳንቀብር ይጠይቃሉ፡፡
ምክንያቱም ብሌን መለገስ ለሌላው ሰው ሕይወት እንደመስጠት መሆኑን የሚስረዱት
ቀሲስ አንዱዓለም በሞቱ ሌሎችን ያዳነውን ክርስቶስን እንደ አብነት ያነሳሉ፡
ለጋሹ ከሞተ ፡ ‹‹ይሄን ትምህርት የምናገኘው እየሱስ ክርስቶስ ደሙን አፍስሶ እኛን
እንዳዳነን ሁሉ እኛም ብሌናችንን ብንለግስ ሌላ ሰው አዳንን ማለት ነው፡፡
እሱ እንዲያውም ዓለምን ነው ያዳነው በደሙ፡፡ እኛ ደግሞ ሁለት ሰው ብርሃን
በኋላ ሀላፊነቱን ስንሰጥ ያው አዳንነው ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ሰውየው ከሞተ በኋላ ነው
የሚሰጠው››፡፡
ሊወስዱለት የብሌን ልገሳን ከሌሎች ዓይነት የሰውነት ክፍሎች ልገሳ (ለምሳሌ ከኩላሊት
ልገሳ) ከሚለዩት ነገሮች አንዱ ከሞት በኋላ የሚደረግ መሆኑ ነው፡፡
የሚችሉት እነሱ ስለዚህም ለጋሹ በዙሪያው ላሉት ሰዎች ማለትም ለቤተሰቦቹና ለቅርብ ወዳጆቹ
ጥብቅ የአደራ ቃል ማስተላለፍ ይጠበቅበታል፡፡ ከሕልፈታቸው ሦስት ቀን
ስለሆኑ፡፡ አስቀድመው ለዓይን ባንኩ በመደወል ስለ ልገሳው ጉዳይ በድፍረት ሊወያዩ
የሞከሩት መ/ር መብዐፅዮን ያደረጉትም እንደዚያ ነው፡፡ ቤተሰቦቻቸውን፣
ጎረቤቶቻቸውንና የንስሃ አባታቸውን በተናጠል እያናገሩ የብሌናቸው ልገሳ
ጉዳይ በመደናገጥ እንዳይረሳ አደራ የማስቀመጡን ድርሻ ሳይረፍድ ሊወስዱ
በመቻላቸው የገቡት የልገሳ ቃል ሊፈፀምላቸው ችሏል፡፡ ይህንን ጉዳይ ዶ/ር
መነንም አስረግጠው ያስረዳሉ፡ ‹‹ዋናው ጠቃሚ ጉዳይ ለጋሾች ለቤተሰብ
ማሳወቃቸው ነው፡፡ ምክንያቱም ለጋሹ ከሞተ በኋላ ሀላፊነቱን ሊወስዱለት
የሚችሉት እነሱ ስለሆኑ››፡፡
35