Page 74 - DINQ Magazine June 2020 Edition
P. 74

አሻራ












                አምስት ቢሊዮን ችግኞች                                የሰው ሀብት ልማት ታሳቢ መደረግ እንዳለባቸው ከኮሚሽኑ ያገኘነው


         በሁለተኛው ዙር አረንጓዴ አሻራ                                  መረጃ ያሳያል፡፡
                                                                የደን ሀብት ኢትዮጵያ ካሏት እምቅ ሀብቶች አንዱ ሲሆን፣ ደንን
                                                              ማልማትና ጥቅም ላይ ማዋል ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሥነ ምኅዳራዊ
         ምሕረት ሞገስ                                             ጥቅም  እንዳለው  ይታወቃል፡፡  የደን  ሀብት  የኢትዮጵያን  ኢኮኖሚ
         በኢትዮጵያ 80 በመቶ ያህሉ ሕዝቦች በተለይም በገጠር የሚኖሩ  ለማሳደግም  ሆነ  የአየር  ንብረት  ለውጡ  የሚያስከትለውን  ችግር
       ቤተሰቦች  ለኃይል  አቅርቦት  የሚጠቀሙት  ከማገዶ  እንጨት  ነው፡፡  ለመቅረፍ ያለውን ጉልህ ጠቀሜታ ተከትሎ፣ ዓምና በአዲስ መነሳሳት
       ከአገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት አራት በመቶ ያህሉን የሚይዙት ማር፣  የተጀመረው  ‹‹አረንጓዴ  አሻራ››  በኢትዮጵያ  የደን  ሀብትን
       የጫካ ቡናና የጣውላ እንጨትም የደን ትሩፋቶች ናቸው፡፡                     በማበልፀግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ተስፋ የተጣለበት
         ለአፈርና  ውኃ  ጥበቃ፣  የካርበን  ልቀትን  ለመምጠጥ፣  ለብዝኃ  ነው፡፡
       ሕይወት፣  ለመሬት  ምርታማነትና  ለሰው  ልጅ  ጤንነት፣  ለማኅበራዊ             በ2011 ዓ.ም. በመላ ኢትዮጵያ ለደን አመቺ ናቸው በተባሉ
       ኢኮኖሚው  ከፍተኛ  አበርክቶ                                                                 ሥፍራዎች አራት ቢሊዮን ችግኞች
       ያላቸው  የኢትዮጵያ  ደኖች  ግን                                                              ተተክለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ሕዝቡ
       ለበርካታ  ዓመታት  በመኖርና                                                                 በራሱና  በየአካባቢው  በሚኖሩ
       በመጥፋት  ውስጥ  ሲመላለሱ                                                                  መንግሥታዊና         መንግሥታዊ
       ኖረዋል፡፡  የሕዝቡ  የቅደመ                                                                 ባልሆኑ     የግብርና     ተቋማት
       ዛፍ  የመትከል  ባህል  ላይ                                                                 አማካይነት  የክረምትን  ወቅት
       መንግሥታት         በየዘመናቸው                                                             ተከትሎ ችግኝ የመትከል ልማድ
       ደኖች  እንዳይመናመኑ  ጥረት                                                                 የነበረው  ቢሆንም፣  በጠቅላይ
       ሲያደርጉ  ቢቆዩም፣  የኢትዮጵያ                                                               ሚኒስትር      ዓብይ     አህመድ
       ደኖች ከመራቆት አልዳኑም፡፡                                                                  (ዶ/ር)  አነሳሽነት  አምና
         እያደገ የመጣው የኢትዮጵያ                                                                 እንደተተከለው          በቢሊዮን
       ሕዝብ       ቁጥር     ተጨማሪ                                                             የሚቆጠሩ የተለያዩ የዛፍ ችግኞች
       ማገዶና  የእርሻ  ቦታ  የሚፈልግ                                                              ሶስት  ወር  ባልሞላ  ጊዜ  ውስጥ
       ነው፡፡    የደን     ጭፍጨፋንና                                                             ስለመተከላቸው  ከዚህ  ቀደም
       መመናመንን           አባብሷል፡፡                                                           አልተነገረም፡፡
       በመሆኑም  የኢትዮጵያ  ደኖች                                                                   በተለይ  ሐምሌ  22  ቀን
       መልሰው  እንዲያገግሙ  ብሎም                                                                 2011  ዓ.ም.  በአገር  አቀፍ
       እንዲጨምሩ  ማድረግና  ባህላዊውን  የደን  ልማት  አሠራር  መቀየር  ደረጃ  የተከናወነው  ‹‹የአረንጓዴ  አሻራ  ቀን››  ኢትዮጵያ  በጊነስ
       ካልተቻለ፣ ኢትዮጵያ እስከ 2030 ድረስ ዘጠኝ ሚሊዮን ሔክታር  ታሪክ መዝገብ እንድትሰፍር ያደረገም ነበር፡፡
       መሬቷ  ይመነጠራል፣  ዓመታዊ  የማገዶ  ፍጆታዋም  በ65  በመቶ                ርዕሰ ብሔር ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድንና
       ይጨምረዋል፡፡                                               የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ ከላይ እስከ ታች 23 ሚሊዮን ሕዝብ
         የኢትዮጵያ 15.7 በመቶ ያህል መሬት ማለትም 17.35 ሚሊዮን  በተሳተፈበት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም 353‚633‚660 ችግኞች
       ሔክታር በደን የተሸፈነ፣ ሰፊው መሬቷ ደግሞ የተራቆተ ነው፡፡ ኢትዮጵያ  በአንድ ቀን መተከላቸውን ሥራውን የሚያስተባብረው ብሔራዊ ኮሚቴ
       በኮሚሽኑ ዕቅድና ስትራቴጂ መሠረት ይህንን መልሶ ለማልማት አቅሙ  በወቅቱ አስታውቆ ነበር፡፡
       አላት፡፡                                                    በወቅቱ 200‚000‚000 ችግኞችን ለመትከል ቢታቀድም፣ 75
         ደኖች በኢትዮጵያ አጠቃላይ ኢኮኖሚ ላይ ያላቸውን ጠቀሜታ ዕውን  በመቶ ብልጫ በማድረግ የተከናወነው የችግኝ ተክላ፣ ህንድ እ.ኤ.አ.
       ለማድረግ የተቀረፀው ብሔራዊ የደን ዘርፍ ልማት ፕሮግራምም፣ ደኖችን  በ2017፣  1.5  ሚሊዮን  ዜጎቿን  በማስተባበር  በአንድ  ቀን  66
       መልሶ በማልማትና በማስፋፋት የአየር ንብረት ለውጡን ከመቋቋም ጎን  ሚሊዮን  ችግኞችን  በመትከል  በጊነስ  ወርልድ  ቡክ  ያስመዘገበችው
       ለጎን የሕዝቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጥ  ክብረ ወሰን በኢትዮጵያ እንዲሰበር ያደረገ አሻራ መሆኑ ይታወሳል፡፡
       የታመነበት ነው፡፡                                              ካለው  17  ሚሊዮን  ሔክታር  መሬት  ደን  ውስጥ  በየዓመቱ
         ኢትዮጵያም የኢኮኖሚ ዕድገቷን በዘላቂነት ለማስቀጠል የምታደርገው  92‚000 ሔክታር በምንጣሮ የምታጣው ኢትዮጵያ፣ ዘንድሮ ደግሞ
       ግብ ግብ የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ ጥቅም ላይ ከማዋል ጋር የተዛመደ  አምስት ቢሊዮን የዛፍ ችግኞች ለመትከል ቅድመ ዝግጅት እያደረገች
       ነው፡፡  ካሉት  እምቅ  የተፈጥሮ  ሀብቶች  መካከል  በግብርናው  የደን፣  ነው፡፡
       የሰብል ምርት፣ የእንስሳት ሀብት ሲኖሩ ከዚሁ ጎን ለጎን ታዳሽ ኃይልና
                                                                                               ወደ ገፅ 90 ዞሯል
                                                                                                                 7
             Page 74                                                           “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር“                ድንቅ መጽሔት -  ሰኔ 2012
   69   70   71   72   73   74   75   76   77   78   79