Page 80 - DINQ Magazine June 2020 Edition
P. 80

ቅኝት







             ነገረ ወረርሽኝ                                 (በዳንኤል ክብረት)


                                                    www.danielkibret.com
          በኢትዮጵያ ታሪክ







           የዓረብ  ታሪክ  ጸሐፊዎች  በ1215  ‘’አሳሕ’’፣  በ1251  ደግሞ  ‘’ፋሳሕ’’  የተባሉ  ወረርሽኞች
      በኢትዮጵያ  ተከሥተው  እንደነበር  ጽፈዋል።  በዐፄ  ሰይፈ  አርዕድ  ዘመን  በደብረ  ሊባኖስ  ተከሥቶ  የነበረ
      ሕማመ  ብድብድ(ቸነፈር)  53  መነኮሳት  መፍጀቱን  ገድለ  አቡነ  ፊልጶስ(ዘደብረ  ሊባኖስ)  ይናገራል።

      በገድለ ዜና ማርያም በእንፍራንዝ(ማዕከላዊ ጎንደር) አካባቢ በ14ኛው መክዘ በተከሠተ ወረርሽኝ ብዙ ሕዝብ እንዳለቀ ተጽፏል ።
      ከ1361-1441 በነበሩት አቡነ ዮሐንስ ዘደብረ ቢዘን ጊዜ ከባድ ወረርሽኝ በኤርትራ አካባቢ ተከሥቶ 61 ገዳማውያን ሞተዋል
      ። ዓረባዊው ታሪክ ጸሐፊ መቅሪዚ በ1428 አካባቢ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ከመንገሣቸው ጥቂት ቀደም ብሎ ወደ ኢትዮጵያ የገባው

      ከባድ ወረርሽኝ ብዙ ኢትዮጵያውያንን ፈጅቷል።


           የዐፄ  ዘርዐ  ያዕቆብ  ዜና  መዋዕል  እንደሚነግረን  በእርሳቸው  ዘመን  የመጣው  ወረርሽኝ  (ሕማመ
      ብድብድ)  ብዙ  ኢትዮጵያውያንን  ከመጨረሱ  የተነሣ  ሟቾች  ቀባሪ  አጥተው  ነበር  ይላል።  የቅዱስ  ቂርቆስ  ቤተ

      ክርስቲያን  በደብረ  ብርሃን  የተተከለው  ቅዱስ  ቂርቆስ  ሕማመ  ብድብድን  የማስቀረት  ቃል  ኪዳን  ስላለው  ነው።
      እንዲህ ባለ ጊዜ አበው ሁለት ዓይነት መፍትሔ ይወስዳሉ። በሽታው ከበረታበት ቦታ መራቅ፣ እና መንፈሳዊ መፍትሔ
      መፈለግ።



           ገዳማውያንና ደቀ መዛሙርት ወይ በበኣታቸው ተወስነው ይቆያሉ። ወይም መዓቱ እስኪያልፍ ዘወር ይላሉ። በዚያው
      ሆነውም በጸሎት ይተጋሉ።
           ብዙው ወረርሽኝ ከሰው ወደ ሰው ስለሚተላለፍ የተያዘውን ሰው ለይቶ መከባከብ፤ ያልተያዙት ከአካባቢው ዘወር

      ብለው መቆየት ወይም ከቤትና ከበኣት ሳይወጡ መሰንበት የተለመደ ነው። በዚያው ሆነው በጸሎት ይበረታሉ። አንዳንዴ
      ነገሩ ከከፋ ገዳማቱ ይዘጋሉ። በገድለ አሮንና በገድለ ወለተ ጴጥሮስ ያየነው ይሄንን ነው።
           በቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ዘመን የመጣው ወረርሽኝ ገዳማውያኑን ከመፍጀቱ የተነሣ መቃብር ቆፋሪ አሳጥቷቸዋል።

      ቀሪዎቹ የተረፉትም ቦታውን ለቅቀው ደሴተ አንግራ ገብተው ነው።
           የቅዱስ ቂርቆስ ደብር በደብረ ብርሃን፣ በጎንደርና በአዲስ አበባ የተተከለው ቅዱሱ በወረርሽኝ ላይ የተቀበለው ቃል

      ኪዳን ስላለው ነው።
           በ1777 ጎንደር የገባው ወረርሽኝ በከብት ጀምሮ ወደ ሰው ተዛመተ። ሕዝቡ ከተማውን ጥሎ ወጣ። ገጠሩም በዚያው
      ቀረ። ነገሩም ከቦታ ቦታ በሚዘዋወረው ሰው ምክንያት ተባባሰ። መናኔ መንግሥት ተክለ ሃይማኖት በር ዘግተው ሱባኤ ገቡ።

      ያኔ ነው የቅዱስ ቂርቆስን ታቦት እንዲተክሉ የተነገራቸው።
           ከትናንት እንማር። ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶችን እንጠብቅ።

           ርቀታችንን እንጠብቅ፤ እጃችንን እንታጠብ በርትተንም እንጸልይ።

            Page 80                                                           “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር“                ድንቅ መጽሔት -  ሰኔ 2012
   75   76   77   78   79   80   81   82   83   84   85