Page 88 - DINQ Magazine June 2020 Edition
P. 88
ፊቼ ጫምባላላ... ሥርዓቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች በሚከናወኑበት ወቅት ሴቶችም
እኩል ተሳታፊ መሆናቸውን ያስረዳል፡፡ የሻሺጋ መደምደሚያ
ከገፅ 56 የዞረ ላይ ፊቺ ፋሎ ወይም የፊቼ መጠናቀቅ የሚያመላክት ቄጣላ
የደረጋል፡፡ በዚህም ወቅት ኅብረተሰቡ በየጎሳውና በየጉዱማሌው
ሲዳማ ለከብት ከፍተኛ ግምት ያለው በመሆኑ ነው፡፡ የሚጨፍር ሲሆን፣ በጎሳው አዛውንቶች ፊቼ ጄጂ (ፊቼ ለዘለላም
ቀደም ሲል ታርዶ ሲበላ የተረፈ ሥጋ እቤት ውስጥ ካለ ትኑር) በማለት አዛውንቶች ለማሳረጊያ በሚሰጡት ቡራኬ የፍቼ
በዕለቱ ሥጋው ከቤት ውጪ እንያዲያድር ይደረጋል፡፡ አባወራ በዓል ማጠቃለያ ይሆናል፡፡
(የቤቱ ባለቤት) በፊቼ ዕለት ከቤቱና ከቤተሰቡ ተለይቶ ሌላ ጋር
አያድርም፡፡ በዚህ ዕለት በየደጁ ከእርጥብ እንጨት ‹‹ሁሉቃ›› ፊቼ ፋሎ
የተሰኘ መሹለኪያ ተዘጋጅቶ አስቀድሞ አባወራው በሁሉቃው ውስጥ ‹‹ፊቼ ፋሎ›› የፊቼን በዓል በጋራ በባህላዊ አደባባይ
ከሾለከ በኋላ ቤተሰቡንና ከብቱን ያሾልካል፤ ይህም በሰላም ከዘመን በድምቀት የማክበር ሥነ ሥርዓት ነው፡፡ ስለሆነም በአመዛኙ
ዘመን የመሸጋገር ተምሳሌት ነው፡፡ የፍቼ ዕለተ ቀን በተከበረ በሦስተኛው ቀን ወይም አንደ አካባቢው
በተመረጡ ቀጣይ ቀናት ‹‹ፊቼ ፋሎ›› ወይም (ሻሻጋ) በባህላዊ
የጫምባላላ አከባበር አደባባይ በጋራ ይከበራል፡፡ አደባባዩ ‹‹ጉዱማሌ›› ይባላል፡
‹‹ጫምባላላ›› በፊቼ ማግሥት በዕለተ ቃዋለንካ የሚከበር ፡ ‹‹ጉዱማሌ›› የፍቼ በዓል በጋራ የሚከበርበትና እንዲሁም
ሲሆን፣ የፊቼ ዕለት በጋራ በተበላበት ‹‹ሻፌታ›› (ባህላዊ በሌላ ጊዜ የጎሳ መሪዎችና ‹‹ጭሜሳዎች›› (ብቁ አረጋውያን)
ገበታ) ውኃ ተሞልቶ ጠዋት ላይ አባወራውና ቤተሰቡ በውኃው ልዩ ልዩ ባህላዊ ሥርዓት የሚያከናውኑበት የተከበረ ባህላዊ ሥፍራ
ፊታቸውን በማስነካትና ከዚሁ ጋር የቀረበውን ቅቤ አባወራው ነው፡፡ ኅብረተሰብ በዓሉን ለማክበር በጎሳ በጎሳ በመሆን በተለያየ
እየቆነጠረ የራሱንና የቤተሰቡን አናት በማስነካት ወደ አዲሱ ባህላዊ ጭፈራና ባህላዊ አልባሳት አጊጠው ወደ ‹‹ጉዱማሌ››
ዘመን የመሸጋገር ተምሳሌት ይከናወናል፡፡ የ‹‹ጫንባላላ›› ይጓዛሉ፡፡ ሁሉም በጋራ በየጎሳው ወደ ‹‹ጉዱማሌ›› ከገቡ በኋላ
ዕለት መሬት የማረስ እንጨት የመስበር የመሳሰለውን ተግባር የባህላዊው ሃይማኖት አባቶችና የጎሳ መሪዎች እንደ ማኅበራዊ
ስለማይከናወን ለማገዶም ቢሆን አስፈላጊው እንጨት አስቀድሞ ደረጃቸው በየተራ ንግግር ያደርጋሉ፣ ይመርቃሉ፣ ባሮጌው ዘመንና
ይዘጋጃል፡፡ በዕለቱ አባወራው ከብቶቹን ማለፊያ ‹‹ካሎ›› በአዲሱ ዘመን ላይ ያተኮሩ መልዕክቶው እንዲጎለብት አስከፊው
(የግጦሽ ሳር) ውስጥ አሰማርቶ ለከብቱ ቦሌ ነስንሶ እያበላ እንዳይደገም ምክር አዘል መልዕክት ያስተላልፋሉ፤ ዘመኑ የሰላም፣
ከብቱን አጥግቦ ያውላል፡፡ በዚህ ዕለት ልጆች ተሰባስበው በየቤቱ የብልጽግና የልማት ይሆን ዘንድ ቃል ቡራኬ ያደርሳሉ፡፡
በመሄድ “አይዴ ጫምባላላ” እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ የቤቱ
ባለቤቶች ምላሹን ‹‹ኢሌ ኢሌ›› ከዘመን ዘመን ያድርሳችሁ
በማለት ልጆቹን አጥግበው ያበሏቸዋል፡፡ አናታቸውን ቅቤ
ይቀቧቸዋል፡፡ በዚህ ዕለት ልጆችንም ሆነ ከብትን በአርጩሜ
መምታት ነውርና አይደረጌ ነው፡፡
ከጫምባላላ ቀጥሎ ያለው የአከባበር ሒደት በጥቅሉ ሻሺጋ
ሲሆን፣ ሻሺጋ በዓሉን በጋራ በገበያ እንዲሁም በጉዱማሌ (ባህላዊ
አደባባይ) በድምቀት የማክበር ሒደት ነው፡፡ በአከባበሩ ከታዳጊ
ወጣቶች ጀምሮ እስከ አረጋውያን ያለው የኅብረተሰብ ክፍል
በጎሳ በጎሳ ሆኖ ቄጣላ (ባህላዊ ጭፈራ) ከጫምባላላ ማግሥት
(ዴላ) ጀምር እስከ ቀዋላንካ ድረስ ማለትም ለተከታታይ አራት
ቀናት በጋራ በመሆንና ጦርና ጋሻ በመያዝ ይጨፍራሉ፡፡ የቄጣላ
ዘፈን የውዳሴና የተቃውሞ ስሜቶች ይንፀባቀሩበታል፡፡ መሪዎች
እንደ ሥራቸው ይወደሱበታል ወይም ይወቀሱበታል፡፡ የቄጣላ
ጨፋሪዎች በየተራ ወደ ጉዱማሌ ገብተው በመቀመጥ በጎሳ
መሪው ምረቃት ከተካሄደ በኋላ በአሮጌው ዘመን በኅብረተሰቡ
ዘንድ የታዩ በጎ ነገሮች እንዲጎለብቱ አስከፊ የሆኑት እንዳይደገሙ
ምክር አዘል መልዕክት ይተላለፋል፡፡ ዘመኑ የሰላም የብልፅግና
የልማት ይሆን ዘንድ ቃለ ቡራኬ ይሰጣል፡፡ ከቄጣላ ጭፈራ ጎን
ለጎን ሆሬ (የልጃገረዶች ጭፈራ)፣ ወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች
ተመራርጠው በጋራ የሚጨፍሩት ባህላዊ ጭፈራ (ፋሮ) ለወራት
ይቀጥላሉ፡፡ ያላገቡ ወጣቶች በተለይ በፋሮ ጭፈራ አጋጣሚ እርስ
በርስ የመተዋወቂያ መድረክ ያገኛሉ፡፡ ይህ ወቅት ተሞሽረው
የቆዩ ሴቶች አምረውና በአማቾቻቸውና በጎረቤቶቻቸው ታጅበው
ወደ አደባባይ የሚወጡበትና ከዘመድ አዝማድ የሚገናኙበት
እንዲሁም ሙሽርንታቸው የሚያበቃበት ወቅት ነው፡፡ የቄጣላ
ጭፈራ የፈረስ ግልቢያ የጉግሳ ውድድር የሚታይበት ነው፡፡
በዚሁ ወቅት ያገቡ ሴቶችና ወንዶች የሚጨፍሩት ባህላዊ ጭፈራ
ሐኖ የሚሰኝ ሲሆን፣ ይህም በሲዳማ ብሔር ዘንድ ባህላዊ ሥነ
Page 88 “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር“ ድንቅ መጽሔት - ሰኔ 2012