Page 147 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 147
137
• የሰብሉን ከማምረት እስከ መመገብ ያለውን ሰንሰለት ለማሳለጥና ለማስረፅ በትላልቅ
ሆቴሎች የማላመድ ስራ መስራት
• የገበያ ትስስር ከሚመለከተው ጋር መፍጠር፣
• የተለያዩ የመልዕክት የማስተላለፊያ ዘዴዎችን ተጠቅሞ ሰብሉንና ከሰብሉ የሚዘጋጁ
ምግቦቸን በሚከተሉት የግንኙነት ዘዴዎች በመጠቀም ማስተዋወቅ፣
o ግላዊ መልዕክት ማስተላለፊያ ዘዴ፣
o ቡድናዊ የመልእክት ማስተላለፊያ ዘዴ (Group extension method)
o የመስክ በዓል ማዘጋጀት፣
o የመገናኛ ብዙሀን ዘዴዎች፣
የህትመት ውጤቶች (ፖሰተር፣በራሪ ፅሁፎችን፣ጋዜጣ…)፤
ዲጂታል የብዙሀን መገናኛ ዘዴዎች (የማህበረሰብ ሬድዮ፣ ኤፍኤም
ሬድዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ማህበራዊ ትስስር፣ ድህረ ገፆች…)፣
• የዘር አምራች አርሶ አደሮችን መፍጠርና የዘር አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ጥረት
ማድረግ፣
• በአርሶ/አርብቶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላት የሰብሉን ሰርቶ ማሳያ ማካሄድና ባለድርሻ
አካላት በተገኙበት የልምድ ልውውጥ ማድረግ፣
• የሰብሉን ከማምረት እስከ መመገብ ያለውን ሰንሰለት ለማሳለጥና ለማስረፅ አጋር
አካላት ከሞዴል አርሶ አደሮች እና ከግበርና ምርምር ማዕከላት ጋር ተቀናጅተው
እንዲሠሩ በማድረግ፤
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል