Page 145 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 145
135
• ፀጉር በተለይ ለሴቶች ረዥም ከሆነ ጠቅልለው በማሰር በሻሽ መሸፈን ይኖርበታል፣
• ምግብ በሚበስልበት ጊዜና ቦታ ትንባሆ አለማጤስ፤ የሚያስነጥስና የሚያስል
ከሆነም አፍና አፍንጫን በክንዳችን በመሸፈንና ከምግቡ ላይ ፊትን ዘወር በማድረግ
ማሳል ወይም ማስነጠስ ምግቡን ከብክለት መከላከል ያስችላል፣
• ለምግብ ማብሰያ እቃ ማጠቢያ የሚያገለግሉ የተለያዩ ሳሙናዎች በተቻለ መጠን
ከመጠቀማችን በፊት የምግብ ደረጃ እንዳላቸው ማረጋገጥ፤ ከተጠቀምን በኋላ
በአግባቡ ማለቅለቅ የማጠቢያው ኬሚካል ቅሪት በእቃው ላይ እንዳይቀር በማድረግ
ከምግብ ወለድ በሽታዎች ለመከላከል የሚጠቅሙ መርህዎች በመሆናቸው
ተግባራዊ ማድረግ ይመከራል፡፡
• የምግብ ማጓጓዣ፣ መያዣ፣ ማከማቻ፣ ማብሰያ ቦታዎችን እና ቁሶችን በአግባቡ
በሞቀ ውሃና የምግብ ደረጃ በያዙ ማጽጃ ኬሚካሎችና ሳኒታይዘሮች ማጠብና
በአግባቡ ማለቅለቅ ይመከራል፣
• የማከማቻ፣ መያዥና ማብሰያ ቁሶች አፅድተን ከመጠቀማችን በፊት መድረቃቸውን
ማረጋገጥ፣
• ምግብ የሚበስልበትን አካባቢና ኩሽና ቶሎ ቶሎ ማጽዳት፣
• ለማጽዳት የምንጠቀምባቸውን እንደ ፎጣና ስፖንጅ ያሉ ቁሶችን ለምግብ ማብሰያም
ሆነ ምግብ ማቅረቢያ ለማጠብ ከመጠቀማችን በፊት በአግባቡ ማጽዳትና ማድረቅ
ይመከራል፣
• በምግብ ማብሰያ ቦታዎችና ምድጃ ውስጥ የምግብ ተረፈ ምርት/ቅሪት እንዳይቀር
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል