Page 144 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 144
134
8.5. በምግብ ዝግጅት ሂደቶ ች ወቅት ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች
8.5. በምግብ ዝግጅት ሂደቶች ወቅት ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች
• የምግብ ሲናርን እንደ ግብዓት በመጠቀም የተለያዩ የምግብ አይነቶች ሲዘጋጁ
የምግቡን ጥራትና ደህንነት ለመጠበቅ ንፅህናን መጠበቅ መሰረታዊ እና ቁልፍ
ተግባር ነው፡፡ ምግቡ ከሚበስልበት ወይም ከማድቤት ንፅህና አጠባበቅ ጀምሮ፣
የምግቡ ማዘጋጃ ቁስ ንጽህናን መጠበቅ እና የምግብ አዘጋጅ ግለሰብ የግል ንፅህናን
መጠበቅን የሚያጠቃልል ተግባር ነው፡፡ በዚህ መሰረት ለምግብነት የሚውሉ
የምግብ አይነቶችን የምናዘጋጅ ከሆነ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መርህዎች
ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
• የምግብ ማብሰያ ቦታን /ኩሽናን/ ንፅህናውን በመጠበቅና የሚበስለውንም ምግብ
ከተለያዩ ባካይ ተባዮች መከላከል፣
• ምግብን የሚያበስሉ ከሆነ የእጆን ጥፍር ማሳጠርና ንጽህናውን በአግባቡ መጠበቅ
ያስፈልጋል፣
• ምግብን ከማዘጋጀት በፊትም ሆነ በዝግጅት ሂደቱ ረዘም በሚልበት ወቅት
በምግቡ ዝግጅት ሂደቱ መካከል እጆን በደንብ በሳሙናና በሞቀ ውሃ መታጠብ፣
• ምግብን ለማዘጋጀት የምንገለገልባቸውን ቁሳቁሶች በፈላ ውሃ እና በሳሙና በደንብ
ካጠብናቸው በኋላ በንፁህ ውሃ በማለቅለቅ በፈላ ውሃ ውስጥ በመቀቀል /ster-
ilize/ በአግባቡ ማድረቅ፣
• በማንኛውም መልኩ ምግብን በሚያዘጋጁበት ወቅት ምግቡን በእጅ በቀጥታ
ከመንካት ይልቅ እንደ ማማሰያና ማንኪያ ያሉ ቁሶችን መጠቀም፤
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል