Page 84 - DINQ MAGAZINE MARCH 2021 EDITION
P. 84

ሰቆቃዬን....                                      አሁን  ሌጣውን  ቀርቷል፤  ዝምታ  ዳግም    ፈለገ፤  ዳሩ  ግን  ዘበኛው  ብዙም  ከቁብ  ስላልቆጠረው
      ከገጽ 26 የዞረ…                            ጀቡኖት  ብቻውን  አስቀረው…  ለተወሰነ  ጊዜ  ፋታ     ምንም  አስተያየት  አልሰጠውም።  እንዲያውም
                                             ሰጥቶት  የነበረው  ሰቆቃ  ከቀድሞው  ይበልጥ  ዳግም    ብርድልብሱን  ስቦ  ራሱን  ተከናንቦ  ለጥ  ብሎ  ተኛ።
             “ያንተ ውሸት ደግሞ የመሬት ትል ሲያስለው      ተንሰራፋበት…  የዐዩና  የተሸበሩና  የተሰቃዩ  ዓይኖች   ሽማግሌው  ባለ  ጋሪ  በረጅሙ  ተንፍሶ  የራሱን  መተኛ
      ሰማሁ ከማለት የባሰ ነው።”                      ከግራና  ከቀኝ  የሚንጠራወዙትን  ሰዎች  እየቃኘ       ጥጋት አመቻቸ። ወጣቱ ጥበቃ የውሃ ጥሙን ለመቁረጥ
                                             ምናልባትም  ከነዚህ  ሁሉ  ሰዎች  መሃል  ጊዜ  ወስዶና   እንደጓጓ  ሁሉ  ሽማግሌው  ወሬ  ለማውራት  ጉዋጉቶ
             አዩና በሹፈት መልክ ፈገግ እያለ “አይ እናንተ   ቆም ብሎ የሚሰማው አንድ ሰው ሊኖር እንደሚችል         ነበር።  እንግዲህ  ልጁ  ከሞተ  አንድ  ሳምንት  ሆነው።
      ወጣቶች” አላቸው።
                                             ተስፋ  አደረገ።  ዳሩ  ግን  ሁሉም  ወደ  ራሱ  ጉዳይ   ስለሁኔታው  ከማንም  ጋር  አውርቶ  ውስጣዊ  ሰቆቃውን
             “ኧረ  ባክህ  አንተ  ሰው  ንዳው  እንጂ!    የሚቻኮል እንጂ አዩናንና የአዩናን ሰቆቃ የሚያዳምጥ      ለማካፈል  አልተቻለውም።  ሠከን  ያለ  ረጅም  ወሬ
      አትነዳውም?”  ሲል  መፃጉዑ  በንዴት  ጦፈ።  ቀጠለ     አልነበረም…  ሰቆቃው  ግዙፍና  ድንበር  የለሽ  ነው።   ለማውራት ፈልጓል፤ እንዴት ልጁ እንደታመመ፣ እንዴት
      “እንዲህ  ነው  የምትነዳው?  አለንጋህን  ተጠቀምበት     የዐዩና ደረት ተከፍቶ ቢታይ የታፈነው ሰቆቃ ፈንድቶ      በህመሙ እንደተሰቃየ፣ በመጨረሻም ምን እንደተናገረና
      እንጂ፣ አንተ አስፈሪ ቁራ! ፍጠን አንተ ሰይጣን! በደንብ   ወጥቶ  ዓለምን  ያጥለቀልቃት  ነበረ፤  ዳሩ  ግን  ማንም   ህይወቱ  እንዳለፈች…ስለ  አቀባበሩ  ሁኔታ፣  ወደ
      ግረፍ ፈረስህን!” ሲል ወረደበት።                  ቁብ  የሰጠው  አልነበረም።  በውስጡ  ያመቀው  ሰቆቃ    ሆስፒታል  ሄዶ  ልብሶቹን  እንደሰበሰበ  በዝርዝር
                                             ግን ለማንም የሚታይ አልሆነም።                   ለማውራት ፈልጓል። እገጠር ቤቱ ልጁ አኒስያን ትቶ ነው
             ከኋላው አዩና የመፃጉዑውን ወጣት ንቅናቄና                                            የመጣው…  ስለ  አኒስያም  ማውራት  የግድ  ይለዋል።
      የሚንተባተብ  ድምፅ  ሰማ።  አዩና  የሚወርድበትን               አዩና እግረ መንገዱን አንድ የመንገድ ፅዳት   ብዙ ነገሮችን አያይዞ ማውራትና የውስጡን መተርተር።
      ዕርግማን  እያዳመጠና  ብቸኝነት  ውስጡን  ሰቅዞ  ይዞ    ሠራተኛ አግኝቶ ከእሱ ጋር ወሬ ጀመረ።              አድማጩ ታዳሚ በሀዘን እየቃተተ፣ በሀዘን ሲያንጎራጉር
      አንገላታው።  መፃጉዑ  ስድብና  ጩኸቱን  እያከታተለ              “እኔ  የምልህ፣  ስንት  ሰዓት  ሆነ!?”  ሲል   በእዝነ  ሂሊናው  ታየው።  ሌላም  ነገር  ታየው፣  ከሴቶች
      ወረደበትና ማሳሉን ጀመረ። ሁለቱ ወጣቶች ስለ አንዲት      ጠየቀ።                                  ጋር  የውስጡን  ማውራት። “ ሴቶች  ምስኪን  ቡቡዎች

      ናዴ»ዳ  ፔትሮቭና  ስለ  ተባለች  ወይም  ስለሌላ                                             ናቸው” አለ ለራሱ፤ “ የተወሰኑ ቃላት ብቻ ይበቃቸዋል

      ማውራታቸውን  ቀጥለዋል፤  ዐዩና  ዞር  ብሎ                   “ሦስት  ሰዓት  አልፏል።  እዚህ  መቆም    በእኔ  ሰቆቃ  ዕንባ  በዕንባ  ሲሆኑ  መመልከት”  የሚል
      ተመለከታቸው፤  ወሬያቸው  በመሃል  ፋታ  ሲያገኝ        አይቻልም፣ ቀጥል ወደፊት!”                     ምስል በአእምሮው ተከሰተ።
      እንደገና አዩና ወደኋላ ዞር ብሎ፡-
                                                     አዩና ወደፊት ጋሪውን አነቃነቀ፣ እጥፍጥፍ           ከዚያም “እስቲ ሄጄ ፈረሴን ልመልከት” ሲል
             “ ታ ው ቃ ላ ቸ ሁ …       ል  ጄ  …   ብሎ  ጎብጦ  ውስጣዊ  ሰቆቃውን  ማዳመጥ  ጀመረ…      አዩና  አሰበ። “ መኝታ    እንደሆን  ይደርሳል  …”  አለ

      ታውቃላችሁ፣የወለድኩት  ልጄ  ከሶስት  ቀን  በፊት  ነው   ለሰዎች ሁኔታውን  ማመልከት እርባና ቢስ ነው  ሲል      ለራሱ።
      የሞተው”።                                 አሰበ…  ከገባበት  ኃይለኛ  የውስጥ  ህመም  በመንቃት
                                             አምስት ደቂቃ ከማለፉ በፊት ጋሪው ላይ ቀጥ ብሎና              ወዲያው ኮቱን ላዩ ላይ ደርቦ ፈረሱ ወዳለበት
             “እባክህ    ሁላችንም  ሙዋቾች  ነን፣       አንገቱን አቅንቶ ልጉዋሙን ነቀነቀ።                አመራ።  ስለ  ልጁ  ጉዳይ  ለአንድ  ሰው  የሆዱን  ዘርግፎ
      አታካብድ! “አለ መፃጉዑ ሳሉን ከጨረሰ በኋላ ከንፈሩን                                           ቢናገር  ደስ  ይለው  ነበር፡፡  ስለ  ልጁ  ባሰበ  ቁጥርና  ያ
      እያሞጠሞጠ።                                        “ወደ  ጋሪዎች  ማሳደሪያየ  ልመለስ”  ሲል   መልኩ ሲከሰትበት ሊቁዋቁዋመው የማይችለው አሰቃቂ
                                             ለራሱ ተናገረ። “ወደ ጋሪዎች ማደሪያ፣ መጭ!”
             “አፍጥነው  እንጂ!  እስከመቼ  ነው  እንዲህ                                         ህመም ይሰማዋል።
      የምንጉዋተተው። መቼ ይሆን እዚያ የምንደርሰው?”                 አሮጌዋ  ባዝራ  ስሜቱን  ያገኘች  ይመስል
                                             እያነከሰች ጉፍ ጉፍ ማለትዋን ጀመረች። ከአንድ ሰዓት            “እያመነዠክሽ ነው?” ሲል ፈረሱን እየጠየቀ
             “ጆሮው ላይ አንድ ማበረታቻ ስጠው!” አለ      ተኩል  በኋላ፣  ዐዩና  ከአንድ  ትልቅ  ቆሻሻ  ምድጃ   የሚያበሩትን የፈረሱን ዓይኖች ተመለከተ። “በይ ቀጥይ!
      አንድ ሌላ ድምፅ።
                                             አጠገብ  ራሱን  አገኘ።  ሰዎች  በምድጃው  ቆጥ፣      አመንዥጊ… ለአጃ የሚሆን ገንዘብ ስላልሰራን ድርቆሹን
             “ትሰማለህ  አንተ  አሮጌ  ቁራ!  የምንልህን   በወለሉና  ጠረዼዛዎቹ  ላይ  ተጋድመው  ያንኮራፋሉ።     ነው  የምንበላው…  አሁንስ  አንቺን  መንዳት  ዕድሜዬ
      ካልሰማህ አንገትህን ነው የማበርልህ! ካንተ ዐይነቱ ጋር    ሥፍራው  ተጨናንቆ  በሚያስጠላ  ሽታ  ታውዶአል።       አልፈቀደልኝም፣  አርጅቼያለሁ…እኔ  ሳልሆን  ልጄ  ነበር
      ከምንጉዋተት  በእግራችን  በሄድን  ይሻለን  ነበር!      ዐዩና  ያንቀላፉትን  ሰዎች  ከተመለከተ  በኋላ  የራሱን   መንዳት  የነበረበት…  አሁን  እሱ    ትክክለኛው  ነጂሽ
      እየሰማኸኝ  ነው  አንተ  አሮጌ  አውሬ?  ለምንልህ  ነገር   የመኝታ  ሥፍራ  አደላድሎ  በጊዜ  ወደ  ቤት  መመለሱ   መሆን የነበረበት  እሱ ነበር… በህይወት ቢኖር ኖሮ…”
      ቁብም አትሰጥ አይደል?”                        እየቆጨው ጋደም አለ።
             “እንዴት  ያላችሁ  መልካም  ልጆች  ናችሁ!”           “የአጃየን  ወጪ  እንኳ  የሚሸፍን  ገንዘብ         አዩና ለጥቂት ጊዜ በዝምታ ቆዝሞ- “ውድዋ

      አላቸው ዐዩና። “እግዚአብሐር ይባርካችሁ!”            አላገኘሁ”  ሲል  በሃሳብ  ተብሰለሰለ። “ ለዚህ  ነው   ፈረሴ፣ ዐየሽ እንዴት መሆን እንደነበረበት… ከእንግዲህ
                                             ማንነቴ እንዲህ  ዝቅ ያለው። ለማንኛውም ሥራውን        ልጄ  ከዝማ  ኤይኒች  የለም…  መላከሞት  ቀደመው
             “ጋሪ  ነጂው!  ለመሆኑ  አግብተሃል?  “ሲል   የሚያውቅ  ሰው…  በቂ  ምግብ  ያለው  ሰውና  ፈረሱ    ልጄን። እንዲያው ለነገሩ ውርንጭላ ቢኖርሽ፣ ያው አንቺ
      ጠየቀው ከሁለቱ ቀጫጭን ልጆች አንዱ።                የሚቆረጥመው በቂ እህል ካለው ምንጊዜም መልካም         የወለድሽው  ውርንጭላ  መሆን  አለበት።  ግን  በድንገት
             “ማን እኔ! ምን አይነት ልጆች ናችሁ?” ብሎ    ነው።”                                  ይህ  ውርንጭላ  ሄዶ  ሞተ  እንበል  ማዘንሽስ  ይቀራል?
                                                                                   አታዝኝም?” ሲል ፈረሱን እያስተዛዘነ ዳሰሰ።
      አዩና ሳቁን ለቀቀ። “እናት መሬት ብቻ ናት የእኔ ሚስት            በአንዱ ጥጋት የተኛው ዋርዲያ ከመኝታው
      ለአሁኑ… የቀብሬ ሥፍራ ማለቴ ነው። የእኔ ልጅ ሄደ፣      እየተንጎላጀጀ ተነስቶ ውሃ ወደ ያዘው ማድጋ ሄደ።              አሮጌዋ  ፈረስ  እያመነዠከች፣  የሚለውን
      ሞተ…አያችሁ…  እኔ  ግን  ይሄው  አለሁ…የሚገርም                                             እያዳመጠች፣  በጌታዋ  እጅ  ላይ  ረጅም  ትንፋሽዋን

      ነገር ነው፣ መላከሞት በስህተት ሌላ በር አንኳኳ… ወደ             አዩና  ቀና  ብሎ “ ጠማህ  እንዴ|?”  ሲል   ለቀቀች።
                                             ጠየቀው።
                                                                                          አዩና በውስጡ ያለውን ሁሉ ዘርግፎ ለፈረሷ
      እኔ ከመምጣት ይልቅ ወደ ልጄ ሄደ…”
                                                     “የጠማኝ ይመስላል አይደል?”

                                                                                   ነገራት።
             ልጁ  እንዴት  እንደሞተበት  ለመናገር  ወደ            “ይሁን  እሰቲ…  ጥምህን  ያርካልህ…
      ተጉዋዞቹ ወደ ኋላ ዞረ። በድንገት ግን መፃጉዑ በረጅሙ     አውቀሃል እንዴ? ልጄ እኮ ሞተ። በዚህ ሳምንት ነው         (ይህ አጭር ልብ ወለድ ለመጀመሪያ ጊዜ የታተመው
      ተንፍሶ መውረጃቸው ላይ መድረሳቸውን ተናገረ። ዐዩና       መሞቱን  የሰማሁት፣  ሆስፒታል  ገብቶ…  ወይኔ  የኔ    በፒተርስበርግስካያ ጋዜጣ ላይ በጥር 25፣ 1886 እ.ኤ.አ
      ሃያ ሳንቲም በእጁ ላይ እያንቃጨለ ጅራሬዎቹን ወጣቶች      ውድ ሞቶ አረፈው!”                          የገና ታሪኮች በሚለው ዓምድ ስር ነበር። ሌቭ ቶልስቶይ
      በትኩረት  መመልከት  ቀጠለ።  በጨለማው  መንገድ
      ገብተው  ከዓይኑ  እስከሚሰወሩ  ድረስ  ቡዝዝ  ብሎ              ወደ  ወጣቱ  ጥበቃ  ሠራተኛ  እየተመለከተ       አንብቦት ቼኾቭ የፃፈው ድንቅ ታሪክ ብሎ
      ተከታተላቸው።                               ስለነገረው የልጁ ዜና እንዴት እንደተሰማው ለማወቅ                   አሞካሽቶታል።)




       84                                                                               “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ”                                                          ድንቅ   መጽሔት           መጋቢት 2013
   79   80   81   82   83   84   85   86   87   88   89