Page 19 - Ethiopia in the Bible by Abune Petros 2
P. 19

አንደኛ ፣ ከዶክተር ላጲሶ መጽሐፍ የተወሰነ ሐሳብ በመውሰድ ኢትዮጵያ ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ከታሪክ
        አንጻር በማሳየት ነው ። ዶክተር ኢትዮጵያ ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ሲገልጡ “በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ ጥንታዊና
        በሐውርታዊ  የአክሱም  የብዙ  ሕዝቦች  ቋንቋዎች  ባህሎችና  ሃይማኖቶች  ኅብረተሰብ  አንድ  በተወሰነ  ሥፍራና  ታሪካዊ
        ወቅት  የአንድ  የተወሰነ  መሬት  ሕዝብና  የፖለቲካ  የበላይ  ሥልጣን  ሕጋዊ  ቅንጅትና  ድርጅት  በመሆኑ  አንድ  ሉዐላዊ
        መንግሥት ነው ። እንዲሁም አንድ ባህላዊ የእርሻ የከተማ የንግድ የዕደ ጥበብ የግል ሀብት የሕግ የጽሕፈትና የገንዘብ

        ሥራ ሥልጣኔ ነው ። ስለ ሆነም ኢትዮጵያ ጥንታዊት የአክሱም መንግሥትና ሥልጣኔ ነው የሚለው አባባል ትክክለኛ
        ግንዛቤና አባባል ነው” (የኢትዮጵያዊነት ታሪካዊ መሠረቶችና መሣሪያዎች፣ ገጽ 22)።

              ሁለተኛ ፣ በዚህ የማሳሰቢያ ሐሳብ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በ1977
        እንደ ኢትዮጵያ አቈጣጠር በተጻፈ ደብዳቤ ጉዳዩ ተነሥቶ ከብዙ መጻጻፍ በኋላ ኢትዮጵያን ሱዳን ብለው የተረጎሙ
        ተርጓምያን  መጽሐፍ  ቅዱሳቸው  እንዳይሰራጭ  ወደ  ፊትም  እንዳይታተም  የተደረገ  መሆኑን  የሚዘረዝረው  መጽሔት

        በመረጃነት የዘረዘራቸው ነጥቦች በቅዱስ ሲኖዶሱ ድረ ገጽ ላይ እንደሚገኝ ለመጠቆም እንወድዳለን ።

              የዶ/ር  በንቲ  ሐሳቦችም  ታሪካዊም  ፣  ሥነ  ልሳናዊም  ፣  መጽሐፍ  ቅዱሳዊም  መሠረት  የሌላቸው  መሆናቸው
        እንዲስተዋል እንመክራለን ።

                                                     ወስብሐት ለእግዚአብሔር


                                                           አባ ጴጥሮስ




















































         “.ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።”   መዝሙረ ዳዊት - ም. 68 ቁ. 31                                                            19
   14   15   16   17   18   19