Page 17 - Ethiopia in the Bible by Abune Petros 2
P. 17
ኢትዮጵያ በአንድ አገር ለሚኖሩ የዜግነት ሁኔታን የሚያመለክት ሁኖም ተገልጧል ።
መጽሐፍ ቅዱስ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም የሀገር ስም እንጂ የሰው ወይም የሕዝብ ስም አድርጎ አይገልጠውም ። ይህም
ሊታወቅ በላይኛው ክፍል የተመለከትነው የአንድ ሀገር መንግሥትና ሕዝብን የሚመለከተውን ክፍል ነው ። ይኸ ደግሞ
በምንም መልኩ የፊት መልክን ወይም ደግሞ የአንድን የተወሰነ ሕዝብን አይደለም ፥ አንድ አገርን የሚመለከት ነው ። በአንድ
አገር ደግሞ የተለያየ ቀለምና ቋንቋ ያላቸው ሕዝቦች የሚኖሩበት ቦታ ማለት ነው።
ለምሳሌ ፦ በአንድ ወቅት የእግዚአብሔር ሰው ኤርምያስ በፖለቲከኞች የተጠላ ሰው ሁኖ ነበር ፣ በዚህም ምክንያት
የንጉሡ ካድሬዎች በጉድጓድ ውስጥ ከተቱት ፣ በዚህ ጊዜ የንጉሡ ጃንደረባ የነበረ አቤሜሌክ የተባለ ኢትዮጵያዊ ነቢዩ
ኤርምያስን ከጉድጓድ እንዴት እንዳወጣው በራሱ በትንቢተ ኤርምያስ ይህ እውነት እንዲህ ተጽፎአል «በንጉሡም ቤት
የነበረው ጃንደረባ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ ኤርምያስን በጕድጓዱ ውስጥ እንዳኖሩት ሰማ ። ንጉሡም በብንያም በር
ተቀምጦ ነበር ። አቤሜሌክም ከንጉሡ ቤት ወጥቶ ንጉሡን እንዲህ አለው ። ጌታዬ ንጉሥ ሆይ ፥ እነዚህ ሰዎች ነቢዩን
ኤርምያስን በጕድጓድ ውስጥ በመጣላቸው በእርሱ ላይ በማድረጋቸው ሁሉ ክፉ አድርገዋል ፤ በከተማይቱም ውስጥ እንጀራ
ስለሌለ በዚያ በራብ ይሞታል ። ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን አቤሜሌክን ፦ ከአንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ ፥ ነቢዩም
ኤርምያስ ሳይሞት ከጕድጓድ አውጣው ብሎ አዘዘው ። አቤሜሌክም ከእርሱ ጋር ሰዎችን ይዞ ሄደ፥ ከቤተ መዛግብቱም
በታች ወደ ነበረው ወደ ንጉሥ ቤት ገባ ፥ ከዚያም አሮጌ ጨርቅና እላቂ ልብስ ወሰደ ፥ ወደ ኤርምያስም ወደ ጉድጓዱ ውስጥ
በገመድ አወረደው ። ኢትዮጵያዊውም አቤሜሌክ ኤርምያስን ፦ ይህን አሮጌ ጨርቅና እላቂውን ልብስ በብብትህ ከገመዱ
በታች አድርግ አለው ፤ ኤርምያስም እንዲሁ አደረገ» (ኤር 38 ፥ 7-12) ።
ኢትዮጵያዊው የሚል ቃል ዘርን ወይም ቀለምን አያመለክትም የሚያመለክተው አገርን ብቻ ነው ። ሰውየው
ኢትዮጵያዊ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ለሰው አዛኝ መሆኑም የሚያስገርም ሰው ነው ። ምን አልባት ከባለ ሥልጣንነቱም በላይ
የሰው አገር ሰው መሆኑ ተደማጭነት ሳያሰጠው አይቀርም ። ይህ ማለት ኢትዮጵያውያን ለሰው አዛኝ መሆናቸውንም
የሚያሳይ ነው ። ይኸው ሰው በዚህ ደኅና ሰውነቱ በኢየሩሳሌም ጥፋት ጊዜ መከራውን እንደሚያልፍ እግዚአብሔር
በኤርምያስ በኩል መልእክቱን አስተላልፎለታል ። «ሂድ ለኢትዮጵያዊውም ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው ፦ የእስራኤል
አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ እነሆ ፥ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ፤
በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል ። በዚያ ቀን አድንሃለሁ ፥ ይላል እግዚአብሔር ፤ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም ።
ፈጽሜ አድንሃለሁ ነፍስህም እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም ፥ በእኔ ታምነሃልና ፥ ይላል እግዚአብሔር»
። (ኤር 39 ፥ 16-18) ።
ይህ ሰው በመልካም ሥራው ከዚያ መአት እግዚአብሔር እንደ ጠበቀው በኤርምያስ በኩል ተነገረው። በነሞዓብ
በነአሞን የጥፋት አዋጅ ሲታወጅ ኢትዮጵያውያንም አብረው በሰይፍ እንደሚቀጡ የእግዚአብሔር ቃል እውነቱን ያውጃል
«እናንተም ኢትዮጵያውያን ደግሞ ፥ በሰይፌ ትገደላላችሁ» ። እንዲል ። ሶፎ 2 ፥ 12 ።
ኢትዮጵያውያን በቡድን በዜግነታቸው ስም ሲጠሩ ፦
ይህ ከዚህ በታች የምንመለከታቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አሁንም እንደ ገና በጥልቀት መመልከት ያለብን ከሰው
መልክ ወይም ከለር ወይም ዘር ምንም የማይገናኝ መሆኑን ነው ። አብረው የተጠቀሱትም አገሮችና ቦታዎች ናቸው ።
«ፋርስንና ኢትዮጵያን ፉጥንም ከእነርሱ ጋር ጋሻና የራስ ቍርን የለበሱትን ሁሉ» ሕዝ 38 ፥ 5 ።
ፉጥ ፋርስ ለምን በዚያ ያሉ ሰዎችን አይደለም የሚጠራው ፣ ፉጥ በዚሁ በአፍሪካ የሚገኝ አገር ነው። ምንአልባትም
ግብጽ ሊሆን ይችላል ፣ ይሁን እጂ ቃሉ የግለ ሰብን ወይም የቡድንን መልክ የሚያመለከት አይደልም ። ቀጥሎ የሚታየው
ደግሞ አሁን አገሪቱን የሚመለከት ነው ። የሚያየው አገሩን ወክሎ ወይም የጠቅላላው ሕዝብ ድምጽ ወይም የመሪው ውሳኔን
የሚመለከት ቃል ነው ።
«መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች» ። መዝ 67 ፥ 31 ።
እነዶክተር በንቲ በጣም የተናድዱበት አንደኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይህ ነው ። አንዳንዶች ይህንን ቃል አንድ
የተወሰነ ቦታ አይደለም ጠቅላላ የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚመለከት ነው የሚሉ አሉ ። ይህም ከነዶክተር በንቲ የተለየ
አይደለም ። «የሚያውቁኝን ረዓብንና ባቢሎንን አስባቸዋለሁ ፤ እነሆ ፥ ፍልስጥኤማውያን ጢሮስም የኢትዮጵያም ሕዝብ ፥
“.ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።” መዝሙረ ዳዊት - ም. 68 ቁ. 31 17