Page 14 - Ethiopia in the Bible by Abune Petros 2
P. 14
ይህ ጽሑፍ ስለ ኢትዮጵያውኑ ሲናገር ምግባቸው ዳቦና ወተት የሆነ ፥ እስከ መቶ ሃያ ዓመት የሚደርስ ዕድሜ
ያላቸው ፥ ንጉሣቸውንም አክባሪ ፥ መልከ መልካሞችና ቁመተ ሎጋዎች እንደ ሆኑ አብራርቷል ። መጨረሻ ጦረኛውና
ወራሪው ኃይል በኢትዮጵያውያኑ ተሸንፎ ደብዛው እንደ ጠፋ ይኸው ጽሑፍ ይገልጣል (ገጽ 216- 219) ።
ከዚሁ ከግሪኮቹ ጸሐፍያን ሳንወጣ በዚሁ ተቀራራቢ ዓመት የነበረ ገጣሚ ሆሜር ስለ ኢትዮጵያ የጻፈውን ቅዱስ
ሲኖዶስ ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ወደ ሱዳንነት በለወጡት ጊዜ ለማስረጃ ከቀረበው ጽሑፍ እንደ ተገለጠው ኢትዮጵያ
አቀማመጧ በምድር ዳርቻ ፥ ሕዝቦቿ ገሮችና ደጎች ፥ መልከ መልካሞች፣ በጠቅላላ ከኢትዮጵያኑ የታሪክ ተመራማሪዎች
እስከ ግሪካውያኑ የታሪክና የጥበብ ሰዎች ድረስ የተዘገበው ኢትዮጵያ የተባለ ሀገር መጽሐፍ ቅዱስ ከመጻፉ በፊት
የነበረና ያለ ከዚህም የተነሣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፍያን ያነኑ ከፍጥረት ጀምሮ የነበረን አገር ሕዝብና መንግሥት መንፈስ
ቅዱስን አጋዥ አድርገው ጽፈዋል ። ለዚህ ምን ማስተባበያ ሊኖር ይችላል ? አንድም ድንቁርና ፥ ሁለትም ምቀኝነት ፥
ሦስትም ዘረኝነትና ንቀት ካልሆነ በቀር ።
ዘረኛ ነጮች የሚሉትን በማስተጋባት የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ፖለቲካ ለመጠቀም የሚከጅሉት ምሁራን ነን
ባዮች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኩሽ የሚለው ቃል ወደ ኢትዮጵያነት ሲተረጎም የተቃጠለ ፊት የሚል ነው የሚለው
ትርጉም መጀመሪያውንም ትክክል አይደለም ። ኩሽ የሚለው ቃል ኢትዮጵያ ተብሎ ከተተረጎመ የሚሰጠው ትርጉም
የተቃጠለ ፊት ሳይሆን አገር ፥ መንግሥት ፥ የተደባለቀ ሕዝብ ማለት ይሆናል ።
ኢትዮጵያ የሚባለው አገር ሕዝብና መንግሥት ቁንጽል የታሪክ አጋጣሚ ሳይሆን ከጥንት ከዚያ ሲያልፍም የሰው
ዘር መገኛ የሆነው አገር መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ። ከዚያ ካለፈ ዶክተር ላጲሶ እንዳሉት ዘረኛ ነጮች በፈጠሩት
ሌላውን የሰውን ልጅ አሳንሶ ራስን በማግዘፍ ሰው እኩል አይደለም ወደሚለው ወደ ሒትለር የዘረኝነት ጦስ
ስላወረዳቸው እርሱ ደግሞ የጀርመንን የበላይነት በማምጣት ፥ ውድቀት ውስጥ ያደረሳቸውን የናዚን ፍልስፍና
ለማራመድ አሁንም ከራሳቸው ጋር ፊት ለፊት ስላጋጫቸው ነው ይህን በሊቅ ስም የአንድን ሕዝብ ማንነት ስም ከምድረ
ገጽ ላይ ለማጥፋት እየጣሩ ያሉት ። ግን አይቻልም ምክንያት ይህ ኢትዮጵያ የሚለው ስም መቸም ቢሆን አይጠፋም ።
“ኢትዮጵያ” የተደራጀ መንግሥት ሁኖ ተገልጧል ፦
ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ በመጀሪያ የተጠቀሰው የፍጥረት ሁኔታ ሥርዐት ሲይዝ ነው ። ታሪኩን የዘገበው ኦሪት
ዘፍጥረት ወንዞች ከገነት ወጡ ከዚያም ከአራት ተከፈሉ ይልና እያንዳንዳቸው ምን አይነት ወንዞች እንደ ሆኑ መለኪያ
እየሰጠ ይገልጣል ። ከዚህ ላይ ጥርት ያለ ሐሳብ እንዲኖረን ሁሉንም ወንዞች እንመልከታቸው «ወንዝም ገነትን ያጠጣ
ዘንድ ከዔድን ይወጣ ነበር ፤ ከዚያም ለአራት ክፍል ይከፈል ነበር ። የአንደኛው ወንዝ ስም ፊሶን ነው ፤ እርሱም ወርቅ
የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል ፤ የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው ፤ ከዚያም ሉልና የከበረ ድንጋይ ይገኛል ።
የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው ፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል ። የሦስተኛውም ወንዝ ስም
ጤግሮስ ነው ፤ እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው ። አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው» (ዘፍ 2 ፥ 10-15) ።
ወንዝ ገነትን ያጠጣ ዘንድ የሚለው ቃል እንደሚመስለኝ በዚያ ጊዜ ምድር ሁሉ ገነት ነበር ። ምክንያቱም በዚህ
ሐሳብ መሠረት ወንዞቹ በአራቱ ማእዘን ነው የተበተኑት ፥ ሁሉም የሄዱበት ቦታ ምን አይነት እንደ ሆነ አካባቢያዊ
ማብራሪያ ተደርጎባቸዋል ። አንዱ ብቻ ምንም አይነት አካባቢያዊ ገለጻ አልተደረገበትም ። ኤፌሶን የተባለ
የመጀመሪያው ወንዝ የሚፈስበት ኤውላጥ የሚባለው ቦታ የማዕድን ክምችት ያለበት መሆኑን ይገልጣል ።
ሁለተኛው ደግሞ ግዮን ሲሆን ፥ የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከባል ይላል ። ሦስተኛውም ጤግሮስ የተባለው
ደግሞ በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው ይላል ። አራተኛው ግን ኤፍራጥስ ተብሎ ስሙ ብቻ የተተጠራ ሲሆን ምንም
አይነት ምልክት ወይም መለያ አልተሰጠውም ። የት እንደ ሆነ ወዴት እንደሚሄድ አልተገለጠም ። ይህ ሁሉ አስደናቂ
አይደለም ። አስደናቂውና አስገራሚው ግን የሦስቱ ስምና የሚከቡት ወይም የሚሄዱበት የተገኙበት አገርና ስም ጥያቄ
“.ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።” መዝሙረ ዳዊት - ም. 68 ቁ. 31 14