Page 9 - Ethiopia in the Bible by Abune Petros 2
P. 9

እኅቶቹ ሃያ ስምንት ልጆች ወልዷል ። ዕድሜውም አራት መቶ ሰባ ስምንት ነው ። መዲናውና መቃብሩ አኩስም ናት
           ይላል ። ሃያ ስምንት ያላቸውንም በየስማቸው እንደ ተጻፉ በማስረጃ አቅርበዋል ። ዘፍ 10 ፥ 7 ፥ 8 ።

                 ከዚህ  በተጨማሪ  የተጠቀሰው  ነገድ  አቢስ  እንጂ  ኢትዮጲስ  የተባለ  ነገድ  የለም  ፣  ይላሉ  አለቃ  ።  አለቃ
           ሐተታቸውን በዚህ አያቆሙም። ኢትዎፕስ የሚለው በጽርዕ ሁለት ትርጉም እንዳለው ነው የሚነግሩን ። ይኸውም
           አንደኛው የሰው ስም ፥ ሁለተኛው የአገር ስም ። ሐሳባቸውን ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ ፦

                 የሰው ስም ሲኾን ጥቍር ጠቋራ ክሰልማ ። የሀገር ስም ሲኾን ፥ ቈላ ፥ በረሓ ፥ ምድረ በዳ ። ስምነቱ ከኩሽ
           ሞት በኋላ በሁለት ሽሕ አራት መቶ ሃምሳ ዓመት ሰብአ ሊቃናት ያወጡት ከ፸ ሊቃናት የተገኘ ሐዲስ እንግዳ ደኃራዊ
           ስም ነው ። በሱዳን ዙሪያ ያለችውም መላይቱ አፍሪቃ ይልቁንም ከነጭ ዓባይ ወዲህ ያለችው ክፍል ፣ የጥቍሮች
           የኩሽ ልጆች አገር ስለ ሆነች በዚህ በአዲሱ ስም ኢትዮጵያ ትባላለች ። ዘፍ 2 ፥ 13 ።

                 በብሉይ በሐዲስ የተጻፈው ዋነኛውና መደበኛው “ኢትዮጵያ” ግን ታላቁን በረሓ ሰሐራን ጨምሮ የኖባ ክፍል
           ነው ይላሉ ። 2ዜና 14 ፡9 ፡12:13 ። 16 : 8 ። 4ነገ 19 ፥ 9 ። ኢሳ 37 ፥ 9 ። ሕዝ 30 ፥ 5 ። ግብ 8 ፥ 27-39 ። (ገጽ
           248)

                 በዚህ የመዘገበ ቃላት ማስረጃ መሠረት ኢትዮጵያ የሚለው ስም ሁለት ትልልቅ ክፍል ያለው ነው። የሰው ስም
           ሲሆን ኩሽ የሚለውንና ጥቍር የሚለውን ያመለክታል ። የሀገር ስም ሲሆን ደግሞ ቆላ ከነጭ ዓባይ በመለስ ኑብያን
           ይዞ  ያለውን  አገር  ያሳያል  ።  የሰሓራን  በርሓ  የሚያካትት  ስለ  ሆነ  ምን  አልባትም  እስክ  ሕንድ  ውቅያኖስ  ያለውን
           መልክዐ ምድር ያጠቃልላል ማለት ነው ።

                 ከዚህ  በተጨማሪ  የሰብአ  ሊቃናት  ትርጉም  ዕብራይስጡ  ኩሽ  ያለውን  ኢትዮጵያ  ብለው  መተርጎማቸው
           ትክክለኛ  የመንፈስ  ቅዱስ  እጅ  ያለበት  አሠራር  ነው  እንጂ  የተሳሳተ  ትርጉም  ሊባል  አይቻልም  ።  ምክንያት  ኩሽ
           የሚለው የዕብራይስጥ ቃል በግሪኩ የተገኘለት አቻ ቃል ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ነውና ። የሰባ ሊቃናቱ ትርጉም
           ይህንን ቃል ሲሰጥ እንደ አሁኑ የፖለቲካ ንትርክ በሌለበትና በእግዚእብሔር መንፈስ መሪነት በሆነ ሥራ ብቻ እንጂ
           አሁን  የሕሊና  ቀውስ  ውስጥ  በገቡ  የተገንጣይ  ፖለቲካ  አቀንቃኞች  ገፋፍተዋቸው  ፥  በሊቅ  ስም  የሚነግዱ  ፊደል
           የቆጠሩ ፥ ግን ደግሞ አመዛዛኝ አእምሮ የሌላቸው ሰዎች አልነበሩም ።

                 ምንስ ጥቅም ሊያገኙ ይህን ታላቅ ነገር ለዘር ወይስ ለስድብ ወይም አንድን ማኅበረ ሰብ ለማዋረድ ሌላውን
           ለማንገሥ  ሊያደርጉት  ይችላሉ  ?  የአንድን  ቃል  ትርጉም  አቻ  ቃል  ከማግኘት  ያለፈ  ጉዳይ  አላቸው  ብሎ  ማመን
           የእግዚብሔርን ቃል መቃረን ይሆናል ።

                 አርባ  አምስት  ጊዜ  የተጠቀሰው  ኢትዮጵያ  የሚለው  ቃል  የጥቁር  ሰው  ስም  ወይም  ኩሽ  ብቻ  አይደለም  ።
           ኢትዮጵያ የሚለው ስም የተደራጀ መንግሥት ያለው አገርና ሕዝብ ማለት ነው ።

                 ዶክተር በንቲ ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ስድብ ነው ፥ በጣም ያናድደኛል ነው የሚሉት ። የተናደዱበትን ሐሳብ
           እንዲህ ነው የሚገልጡት ፦

                 ማናቸውም ቤተ ክርስቲያን እኔን ቢሰድበኝ ቤተ ክርስቲያኔ አልለውም ። ይህ የማንነት ጉዳይ ነው ። አባትህ
           ያወጣልህ ስም በባዕዳን ቢለወጥ ያናድድሀል ። ማንነትህን ባህልህን ሁሉ ያወድመዋል ። እዚህ የሆነው ነገር በትክክል

           ይህ ነው ። የኩሽ ሕዝቦች ራሳቸውን የተቃጠለ ፊት ብለው አይጠሩም ። ኦሮሞ ፥ ሶማሌ ፥ አፋር ፥ እና ሌሎችም
           የኩሽ ሕዝቦች መሆናቸውን ታሪክ ይነግረናል ። አንድም የገባው የተገለጠለት የኩሽ  ሰው ፥ ግሪኮች ለኛ በሰጡን
           ክብረነክ አዋራጅ ስም ደስተኛ አይደለም ። የመጀመሪያው ስማችን ኩሽ መጠሪያችን እንዲሆን መልሰን ለመጠየቅ
           ደስተኞች ነን ። ስለዚህ ለውጡ ይህ ነው ። እንዳለ የኩሽ ሕዝቦችን ታሪክ በትክክል ሊቀይረው ይችላል ። የኩሽ
           ሰዎች ቋንቋዎች አሏቸው እና የሚኖሩበት መልክአ ምድራቸውም በደንብ የታወቀ ነው ። ግን ኢትዮጵያ ከሚለው ቃል
           ጋር የሚዛመድ ሕዝብም ፥ ቦታም ፥ ቋንቋም የለም ። ባንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የኢትዮጵያ ጥናት እንዳለ እሰማለሁ ።
           መጨረሻ ላይ ይሄም ይቀየራል ። ምክንያቱም ጥያቄ ያስነሣል ። ኢትዮጵያ ማነው ?ኢትዮጵያ ምንድነው ?


                 ከላይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከአርባ አምስት ጊዜ በላይ ተጠቅሶ አገኘሁ ብለው ፥ ያንን ለማስወጣት ትልቅ





         “.ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።”   መዝሙረ ዳዊት - ም. 68 ቁ. 31                                                            9
   4   5   6   7   8   9   10   11   12   13   14