Page 8 - Ethiopia in the Bible by Abune Petros 2
P. 8
“የሀገሪቱ ስም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ Abyssinia ነበር ፤ ወደ ኢትዮጵያ የተለወጠው አሁን በቀዳማዊ ኃይለ
ሥላሴ ዘመን ነው ይላል ፓስቶሩ ። አለማወቅ ካልቀረ እንደዚህ ነው ። በየትኛው ዘመን ነው ኢትዮጵያ ራሷን
በእንግሊዝኛ Abyssinia ትል የነበረው ? የትኛው ንጉሥ ነው “እኔ እገሌ ንጉሠ ነገሥት ዘብሔረ Abyssinia”
ያለ ? ከ1307 እስከ 1336 ዓ.ም በነገሠው በአፄ ዓምደ ጽዮን እንኳ ብንጀምር ፥ ራሱን የሚጠራው “ንጉሠ ጽዮን ፥
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ” እያለ ነበር ። የውጭ አገር ጸሐፊዎች አገራችንን Abyssinia ይሏት ነበረ ። በእኛ በኩል
ግን አገራችን መንግሥት ከሆነችበት ጊዜ ጀምሮ ያለው ሰነድ የሚያመለክተው ኢትዮጵያ መባሏን ነው ። ሰነዶቹ ሜዳው
ሁሉ ናቸው ። አነጋግሯቸው አታኵርፏቸው” ።
እንደሚመስለኝ ዶክተር በንቲ በግላቸው በጣም የተጎዱበት ነገር አለ ። ኢትዮጵያዊነት ስድብ ነው ብለው ሰዎች
ደጋግመው በማስጨነቅ አስተምረዋቸው ወይም በከፋ ስቃይ ይህ ደግሞ ወደ ሥነ ልቡናዊ ትራውማነት
(psychological trauma) ተቀይሯባቸዋል እንጂ በምንም አይነት ያለ አንዳች ታሪካዊ ጭብጥ እንደዚህ ጭልጥ
ብለው በስሕተት የሚሄዱበት ምክንያት አይኖርም ነበር ።
በአንድ ወቅት ኒውዮርክ ሲቲ አንድ የታመመ ወንድም ለመጠየቅ ሆስፒታል ሄድን ። ከቦታው ስንደርስ
ሰውየውን አገኘነው ። እንደምነህ ጤንነትህስ እንዴት ነው ? አልነው ። ሰውየው በሞቅታ “በጣም ደኅና ነኝ!” አለ ።
“ከየት መጣህ” የሚል ሁለተኛ ጥያቄ ጠየቅን ። “ከኢትዮጵያ” አለ ። “መቼ ? ” ብለን መልሰን ጠየቅን ። “የዛሬ ዓመት”
አለ ። “እንዴት መጣህ?” አልነው ። “በባቡር” አለ ። “በምን አይነት ባቡር?” አልን ከኢትዮጵያ አሜሪካ የሚያደርስ
ባቡር አለመኖሩን አስበን ። “በኪው ባቡር” አለን ። በኋላ ስሰማ ሰውየው በኪው ቍጥር ባቡር ሲሄድ አደጋ ደርሶበት
ኖሯል ። የአደጋው ሥቃይ በአእምሮው ተቀርጾ በመቅረቱ ምክንያት አእምሮው የሚያስታውሰው ያን ባቡር ብቻ ነው ።
የዶ/ር በንቲ ሁኔታም ይህን ይመስላል ።ዶክተር ጌታቸው እንዳሉ ኢትዮጵያ የሜለውን ስም የሚያሰረዱ ስነዶች ሚዳ
ሙሉ ናቸው ችግሩ የማሰተዋልና በጤናማ አእምሮ መመልከት ከተቻለ።
በተለያዩ የቃላት መፍቻ መጻሕፍት ሲጠና “ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል ሥር መሠረቱ ኩሽ የሚለው ሲሆን
ኢትዮጵያ የሚለው ሲተረጎም ግን አንድ አይነት ትርጉም ብቻ ያለው ቃል ሁኖ አልተገኘም ። የሀገር ስም ፥ የግለሰብ
ስም ፥ የአካባቢ ስም ሁኖ በመጠራት በተለያዩ ሁኔታዎችና ክንውኖች ትርጉሞች ተሰጥተውት ነው የሚገኘው ።
ከእነዚህ ውስጥ የአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋስው ወግሥ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ በሚለው
መጽሐፋቸው “ኢትዮጵያ” የሚለውን ስም ሁለት ዓይነት ትርጉም ሰጥተውታል ። አለቃ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም (ጽር
ኢቲዖፒኣ ። ዐረ ሱዳን ። ዕብ ኩሽ ፤ ስመ ነገድ) ግሪኩ ኢትዮጵያ ፥ ይለዋል ካሉ በኋላ ይህንኑ ጥሬ ቃል ሲተረጉሙት
= የመልክና የኅብር የሀገር ስም ፤ የሱዳኖች አገር መላው ጠቅላላው ፣ ከግብጽ ቀጥሎ ያለው ። ጥቍር ጠቋራ ክሰልማ ፣
የጥቍሮች አገር ማለት ነው ። ከዚያ ማብራሪያቸውን ይቀጥላሉ ፦
ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር ። ኵሎሙ ኢትዮጵያ ዘጸሊም ሥጋሆሙ ። ወቦ ዘትከውን ኀሳረ
በኀበ ካልኣኒሃ ከመ ቀሪጸ ገጽ በኀበ ኢትጵዮጵያ ወኖባ ። የሚለውን ማስረጃ በማቅረብ ። ኖባ የነገድ የሀገር ፣
ኢትዮጵያ የመልክ የኅብር ስም (መዝ ፷፯ ። ቀሌ ፣ ፍ.ነ ፶፩) ።
ይቀጥሉና የተለመደውን ታሪክ ወደ ጎን በማድረግ ለየት ያለ ታሪክ ይተርኩልናል ። እርሳቸው እንደሚሉት
ኢትዮጲስ የሚለው አንደኛው የኩሽ ልጅ ነው የሚለውን አይቀበሉትም ። ይህ አባባል ዕብራይስጡንና ግሪኩን
ካለማወቅ የመጣ ነው ፣ ከዚያ ሲያልፍ የመላ የግምት አነጋገር ነው ብለዋል ።
በአለቃ ገለጻ መሠረት ፦በጽርዕ ቋንቋ ኢትዮጵያ የተባለው ያው በዕብራይስጡ ኩሽ የተባለው ነው ፣ ዋነኛውና
መደበኛው እርሱው ራሱ በኵሩ የካም ልጅ ነው ፣ ሌላ ሁለተኛ አካል የኩሽ ልጅ አይደለም ። ለኩሽ በኦሪትና በዜና
መዋዕል ከተጻፉት ሳባ ፥ ሐዊላ ፥ ሰብታ ፥ ረዕማ ፥ ሰብተቃ ፥ ናምሩድ ከሚባሉት ከ፮ቱ ሌላ ሃያ ሁለት ልጆች
እንዳሉት ዮናናዊ ታሪክ ይናገራል ።
ከዚሁ ከዮናን የተቀዳው የሞርዬም ታሪክ ፤ የካም ልጅ ኩሽ ፥ አርባ ፥ አልቤዎን ፥ ኪሬኔ ከሚባሉ ከሦስቱ
“.ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።” መዝሙረ ዳዊት - ም. 68 ቁ. 31 8