Page 5 - Ethiopia in the Bible by Abune Petros 2
P. 5

ዶ/ር  በንቲም  ሆነ  የቤተ  ክርስቲያናቸው  የሥነ  መለኮት  ቅኝት  ይህ  ለዘብተኝነት  ነው  ።  ይህ  ሰዎችን  ክርስቲያን
        ከማድረግ ይልቅ ለሰዎች ፍላጎት የሚስማማ ክርስቶስን መፍጠር ዓላማው ያደረገን የሥነ መለኮት አካሄድ ነው ዶ/ር በንቲ
        የፖለቲካ  አጀንዳ  ለማራመድ  የሚጠቀሙበት  ።  ይህንኑ  የተገለልን  ትርክት  ተከትለው  ኢትዮጵያ  የሚለው  ቃል  ጥቁር

        ሕዝቦችን “ያገልላል ፥ ይሰድባል” የሚሉን ። ለምሳሌ ፦ የዶክትሬት  ጥናታቸው  (ለማስተርስ ከሠሩት ጥናት ያን ያህል

        የሚለይ ሁኖ  ባይታይም) የኦሮሞ  ሕዝብ  እምነት ከክርስትናና ከእስልምና በፊት የነበረ መሆኑን  ማመዛዘንና ማወዳደር
        የሚል ነው ።

              “ከዚህ ፕሮጀክት ጀርባ ያለው ምክንያት ብዙ ክርስቲያን ሚሽነሪዎች ፤ ኢቫንጀሊካኖች እና ፓስተሮች የኦሮሞ ሕዝብ

        ስለ እግዚአብሔር ሐሳቡ ፥ ዕውቀቱ የለውም እና ሃይማኖታቸውም በጣዖት ማምለክ ወይም በሰይጣን ማመን ነው ብለው
        ይገምቱ ነበር ። በአካባቢ አህጉራችን የክርስትናና እስልምና ሃይማኖት ከመምጣቱ በፊት የነበረውን የኦሮሞን ሀገር በቀል
        ሃይማኖት  መመርመር  መመልከት  ጀመርኩ  ።  ስለዚህ  ከሥነ  መለኮት  እይታ  አኳያ  የመመረቂያ  ጽሑፌ  የማነጻጸር
        ሃይማኖታዊ ጥናት ነው ። እመለከት የነበረውም ነገር የኦሮሞ ነባር ሃይማኖት ከክርስትና ጋር ይጻረራል ወይስ ይስማማል
        የሚለውን ነው” ።


              ከዚህ በላይ ያለውን የዶክተር በንቲን ሐተታ ስንመለከተው ፣ የመመረቂያው ጽሑፋቸው የኦሮሞን ሕዝብ እምነትና
        ባህል ፥ ከክርስትና ጋር በማወዳደር ላይ የተመሠረተ ነው ። በዚህ ከተመሠረተ ደግሞ ውጤቱ ያንኑ ለውድድር የቀረበውን
        እምነት ከክርስትና ጋር ማወዳደር ይሆናል ። ይህ ማለት እውነተኛ የክርስትና እምነትና ሌላ የክርስትና የሚመስል ሐሳብ
        ስለሚሆን የጠቅላላውን የመጽሐፍ ቅዱስንም ሆነ የጠቅላላ የሥነ መለኮትን አስተምህሮ ሐሳብ ሊይዝ ከቶ አይችልም ።

              የመጽሐፍ  ቅዱሱ  የትርጉም  ሥራ  ውስጥ  ሳይሳተፉ  ራሳቸውን  የተሳተፉ  አስመስለው  መቅረባቸውም  የሰውየውን

        ዓላማ በጥንቃቄ እንድናጤን ይጋብዘናል ። የጥንታዊ ጽሑፎች ሊቅ የሆኑት ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ይህን አስመልክቶ
        የጻፉት ነገር ደምቆ ሊሠመርበት ይገባል ። ፕሮፌሰር እንዲህ ይላሉ ፦

              “ጀርመኖች ማርቲን ሉተር መጽሐፍ ቅዱሱን ወደ ጀርመንኛ እስኪተረጕምላቸው ድረስ የሚጠቀሙት በላቲኑ ቅጂ
        ነበር ። የተረጐመውም ሐዲሱን ከግሪክኛ ፥ ብሉዩን ከዕብራይስጥ ነበር ። በንቲ ስለ ጀርመንኛ መጽሐፍ ቅዱስ ብዙም
        ስለማያውቅ ማርቲን ሉተር የተረጐመው ከላቲን ነው ይላል ። የጀርመን ቤተ ክርስቲያን አሁን ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሷን

        እንደ ገና ለ2017 ዓ.እ. እንዲደርስ አድርጋ ተርጕማለች ። የትርጐማው ግብረ ኀይል ሊቀ መንበር ፥ ፕሮፌሰር ዶክተር
        ክሪስቶፍ  ኬለር  (Professor  Dr.Christoph  Kähler,  Bishop  Emeritus)  በጽሑፍ  እንደ  ገለጠው  ፥
        ጀርመኖቹ መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ትርጐማ ሲከልሱ ፥ ረቨረንድ በንቲ እንኳን የማርቲን ሉተርን አጽፍ ተጐናጽፎ በትርጐማ

        ሊሳተፍ ቀርቶ ፥ አጠገባቸውም እንኳ አልነበረም” ።

              ለነገሩ እንኳን ወደ ጀርመንኛ የሚሠራ ትርጉም ሥራ ላይ ለመሳተፍ ቀርቶ መጽሐፍ ቅዱስን ጀርመኖቹ ከምን ቋንቋ
        እንደ  ተረጎሙት  እንኳ  በትክክል  የሚያውቁ  አይመስልም  ።  ጀርመኖቹ  ለብሉይ  ኪዳን  ዕብራይስጥን  ፥  ለሐዲስ  ኪዳን
        ደግሞ ግሪክን በምንጭነት ተጠቅመዋል- ፕሮፌሰር ጌታቸው እንደ ጻፉት ። ዶ/ር በንቲ የሚነግሩን ግን ሉተር በ16ኛው

        ክፍለ ዘመን ከላቲን ወደ ጀርመንኛ ስለ ተረጎመው መጽሐፍ ነው ። በዚያው ሉተር በሠራው ትርጉም ውስጥም ቢሆን
        ጥቁር ሕዝብ የተጠራው የግሪኩን ወይም የላቲኑን ቅጂ መጽሐፍ ቅዱስ ተከትሎ “ኢትዮጵያ” ሲል አይገኝም ። ይልቁንም
        የምናገኘው  “Mohrenland”  የሚል  ነው  ።  ስለ  ሆነም  አዲሱ  ትርጉም  የበፊቱ  ትርጉም  Mohrenland  ብሎ

        ያቀረበውን የዕብራይስጡን ተከትሎ በማረም ወደ Kush ቀየረ እንጂ ሌላ ያደረገው ነገር የለም ። ዶ/ር በንቲ እዚህም
        ላይ እውነተኝነት አይታይባቸውም ።

              የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ነኝ ከሚል ፓስተር እንዲህ እውነትን እንዳናገኝ ያደረገበት ዋና ምክንያት ይኸው የጎሣ
        ፖለቲካና ለዘብተኛ የሥነ መለኮት ቅኝት ነው ። ታዲያ በእነዚህ ሁለት ጭምብሎች ክርስቲያናዊ ማንነቱን ያጣ ሰው ቢዋሽ
        ምን ይገርማል ! እውነትን ከሐሰት እንዳይለይ የእውነትን ቃል ተራ ቃል አድርጎታል ። የሰው ልጅ መሆንን እንዳያስቀድም
        የጎሣ ፖለቲካ አእምሮውን አስሮታል ።


         “.ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።”   መዝሙረ ዳዊት - ም. 68 ቁ. 31                                                            5
   1   2   3   4   5   6   7   8   9   10