Page 3 - Ethiopia in the Bible by Abune Petros 2
P. 3

መግቢያ




              ቀድሞ በዚህ በምንኖርበት በአሜሪካ ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰባክያንና አማንያን የእግዚአብሔርን ቃል ሰዎችን ባሪያ
        አድርጎ  ለመግዛት  ይጠቀሙበት  ነበር  የሚባለውን  ሐሳብ  ለመቀበል  ረጅም  ጊዜ  ወስዶብኛል  ።    ምክንያቱም
        ለእግዚአብሔር  ቃል  ያላቸውን  ታማኝነት  በኩራት  የሚናገሩ    ወንጌላውያን  ፥  አብያተ  ክርስቲያናት  ፥  ሰባክያን  ይህን

        ይደፍራሉ ብየ በቀላሉ ስላላመንኩ ነበር ።

              መጽሐፍ ቅዱስን የሁሉ ዳኛ አድርገን ስለምናቀርብ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችንና ሐዋርያዊ ትውፊትን እንኳ ሳይቀር
        ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚስማማ መስሎ ካልታየን አንቀበልም እያሉ ሲምሉ ሲገዘቱ ስለምሰማ ነበር ። አሁን ላይ ሁኜ
        ሳስብ  ያ  እምነቴ  እውነትን  የተከተለ  አልነበረም  ።  ምክንያቱም  ወንጌላውያን  ነን  የሚሉ  ኢትዮጵያውያን  ይህንኑ  እያሉ
        የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን ለዕለት ጥቅምና ፥ ለጎሣ ፖለቲካ ፍጆታ ብለው ሲደፍሩት ስላየሁ ነው ።


              መቼም በጥላቻ የእግዚኣብሔርን ሐሳብ እንደ መለወጥ ያለ እርግማን የለም ። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቃሉን
        በባሪያዎቹ በኩል ሲያስተላልፍ የሚጠቀምበት ሕዝብ የተለየ ሁኖ ሳይሆን እግዚብሔር ለዚያ ሕዝብም ሆነ ለጠቅላላው
        ሕዝብ የሚያስተምርበት ስለ ሆነ ነው ። በዚህም ምክንያት እግዚብሔር ለቃሉ ታማኝ በመሆኑ ለፖለቲካ አጀንዳ ብሎ
        ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የጻፉትን ቅዱስ ቃሉን ማረም በጣም ድፍረትም ኃጢአትም እርግማንም ጭምር
        ነው ። (2 ጴጥ 1 ፥ 20-21) ።


              የእግዚእብሔር ቃል ፣ ባሪያዎቹ በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ስለ ጻፉት የሰው ሐሳብ አለበት  ብለን አናምንም ።
        በመሆኑም  እኛም  አንጨምርም  አንቀንስምም  ፥  እንደ  ተጻፈ  እንጠቀማለን  ።  እግዚአብሔር  እርሱ  በመንፈስ  እየመራ
        ያጻፈውን መጽሐፍ መቀነስም መጨምርም እንደማይቻል በግልጥ ተነግሯል ። «እኔ የማዝዝህን ነገር ሁሉ ታደርገው ዘንድ

        ጠብቅ ፤ ምንም በእርሱ ላይ አትጨምር ፥ ከእርሱም ምንም አታጕድል» (ዘዳ 4 ፥ 2) ።

              የሐዲስ ኪዳኑ ጸሐፍት ይህንኑ ሐሳብ በተገቢ መልኩ በማስጠንቀቂያ መልክ ገልጸውታል «ይህን በመጀመሪያ እወቁ
        ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥
        ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ» (2ጴጥ 1 ፥ 20-21) ።

              ይህን ውግዘት የሚያነብ ሰው ዐይነ ልቡናው ካልታወረ በቀር ለፖለቲካ ትርፍ ብሎ የተከበረውን የእግዚአብሔርን
        ቃል በማቃለል ያርማል ብሎ ማሰብ ይከብዳል ።

              የእግዚአብሔርን  ቃል  በተዛባ  አእምሮ  በመረዳት  እንዲህ  አይነት  በደል  መበደል  ምን  ይጠቅማል?  እግዚአብሔር
        ለቃሉ ስለሚጠነቀቅና ወደ መጨረሻው የሚመጡ ሰዎች ያልተላኩትን ተላክን ፥ ያላወቁትን አወቅን የሚሉትን ለማረም ።
        የመጽሐፍ  ቅዱስ  መደምደሚያ  የሆነው  የዮሐንስ  ራእይ  እንዲህ  በማለት  ያስጠነቅቃል  ።  «በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን
        የትንቢት ቃል ለሚሰማ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ ፤ ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ
        የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል ፤ ማንምም በዚህ በትንቢት መጽሐፍ ከተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል ፥ በዚህ
        መጽሐፍ ከተጻፉት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ዕድሉን ያጎድልበታል» ይላል ። (ራእ. 22 ፥ 18) ።
        እንግዲህ ከመተቸት አልፎ ቃሉን በድፍረት የሚሰርዝ ይህን እርግማን ሊሸከም ይችላል።

              በመሠረቱ  ኢትዮጵያውያን  ይህን  መብት  ጠይቀው  መንፈስ  ቅዱስን  አታልለው  ስማችን  በመጽሐፍ  ቅዱስ  ላይ
        ይጻፍልን ብለው የጻፉት መጽሐፍ አይደለም ። እኛም ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ የተነሣንበት ዋና አላማ ለኢትዮጵያ ስም
        ጥብቅና  ቁመን  በታላቁ  መጽሐፍ  የተጻፈውን  የኢትዮጵያን  ስም  ለማስከበር  አይደለም  ።  የተከበረውን  መጽሐፍ  ቅዱስ
        በአግባቡ እንዲቀበሉ ለማረም ነው ።







         “.ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።”   መዝሙረ ዳዊት - ም. 68 ቁ. 31                                                            3
   1   2   3   4   5   6   7   8