Page 7 - Ethiopia in the Bible by Abune Petros 2
P. 7
እንደሚሉን ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ከስድብ ቈጥረው አይደለም ። ዶ/ር በንቲ ጀርመኖቹን ለምን በሐሰት የአፍሪካ የጎሣ
ፖለቲካ ቀለም ሊለቀልቋቸው እንደ ፈለጉ እንጃ ! ጀርመኖቹ ለራሳቸው በኹለተኛው የዓለም ጦርነት በዘር ቈጣሪ ናዚዎች
ለተፈጁት አይሁዳውያን ያላቸውን ጸጸት ለመግለጽና አይሁዳውያንን ለመካስ እጅግ ሲጥሩ ነው የሚታዩት ። የትርጉም
ሥራቸውን ዶ/ር በንቲ የጎሣ ፖለቲካ ማራመጃ እንዳደረጉት ቢያውቁ ምን ይሰማቸው ይሆን ! ዶ/ር በንቲንስ ምንኛ
ይታዘቡ ይሆን ?
ለነገሩ ዶ/ር በንቲ በአዲሱ የጀርመንኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም አሳብበው የተረሳና የማይጠቅም አጀንዳቸውን
ሊያራምዱ ተጣጣሩ እንጂ ኢትዮጵያ ከሚለው ስም ጋር ያላቸው ጠብ አሁን የጀመረ አይደለም ። ለዚህ ማስረጃ
የሚሆነው የማስተርስ ቲሲሳቸውን ሲጽፉ የተጠቀሙት የዛሬ ሠላሳ ዓመት “ኢትዮጵያ” የሚለውን ቃል በሙሉ ከመጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥ ፍቆ “ሱዳን” ብሎ ለመተካት ሞክሮ በነበረው የጉድ ኒውስ ባይብል ትርጉም ነው ። ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ
ትርጉም የዛሬ ሠላሳ ዓመት እንዲህ ያለውን ደፋር ስሕተት ሲሠራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ
ሲኖዶስ ባደረገው መጻጻፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ይቅርታ ጠይቆ የታተመው ብቻ እንዲሰራጭ እንጂ ከዚያ ሌላ
እንዳይታተም ፣ ወደ ሌላ ቋንቋም እንዳይተረጐም የሚል ውሳኔ ተላልፎ ነበር ። ዶክተር በንቲ ይህን እየተጠቀሙ ነው
የመመረቂያ ሥራቸውን የሠሩት ። የመመረቂያ ጽሑፋቸው ውስጥ ግን መጽሐፉ ሱዳን የሚለውን እርሳቸው ኢትዮጵያ
ብለው እያነበቡ ማለት ነው ፥ ወይም በግምት ከጀርመኑም መጽሐፍ ቅዱስ የሌለውን ይኖር ይሆናል ብለው ነው ማለት
ነው ። ስለዚህ ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ለዶክተር በንቲ ወይ የሚጽፉትን ነገር ሳይገባቸው ነው የሚጽፉ ፥ ወይ ሰው
ለማስደሰት ብለው ስህተት ይጽፋሉ ።
ዶ/ር በንቲ የሰብአ ሊቃናት ትርጉም በመባል የሚታወቀውን የብሉይ ኪዳን ትርጉም የሠሩት ግሪኮች ናቸው ይሉናል
በድፍረት ። ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ጥቂት የተማረ ወይም ያነበበ ሰው ይኽ አባባላቸው ምንኛ ስሕተት እንደ ኾነ
በቅጽበት ይረዳል ። ታሪክ በግልጽ እንደሚነግረን እነዚያ ተርጓሚዎች ግሪክኛ ተናጋሪ አይሁዳውያን ሊቃውንት እንጂ
ግሪኮች አልነበሩም ። የሚገርመው ይህን እንኳ በአግባቡ ሳይረዱና ራሳቸውን ሳይሆኑ ለመላ አፍሪካ ጥቁር ሕዝብ ጠበቃ
ሁነው መገኘታቸው ነው ። በነጻነት የኖረ ሀገር ፣ ዘረኛ ወራሪ ፈረንጅን ያሳፈረ ፣ ነጻነቱን ጠብቆ ከሦስት ሺሕ ዓመታት
በላይ የመንግሥት አስተዳደር የሚያውቅ ፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ ካሉ ታላላቅ መንግሥታትና ሀገሮች ጋር የተጎራበተ ፣
ራሱን የቻለ ስም ያለው ሀገር ነው ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ ። ኢትዮጵያ የሚለው ቃል በዓለም ታሪክ ዐውድ የሚጠራው
ፍቺ የቆዳ ቀለምን በመግለጽ ብቻ የተወሰነ አይደለም ።
በባርነት ተሽጠው አሜሪካ ገብተው የራሳቸውን ስምና ማንነት ያጡ አፍሪካውያን የመጡበት ሀገር ስም ስለ
ጠፋባቸው ራሳቸውን “አፍሪካን አሜሪካን” ብለው ይጠራሉ ። ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ለዚህ መከረኛ አፍሪካዊ ሁሉ
ታሪካዊ ክብር ነው ። እንደ ነዶክተር በንቲ ያሉት ደግሞ ይህ አፍሪካዊ ማንነትና ኮራት ስድብ ነው ይላሉ አባባላቸ
እንደሚከተለው ሰፍሯል
“ባሮጌው የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጾች ውስጥ "ኢትዮጵያ" የሚለው ቃል 45 ጊዜ ተጠቅሷል ። እነዚህ ቃላት እንደ
ስሕተት ተወስደው ኩሽ ወደሚለው ወደ ቀድሞ ትክክለኛ ቃሉ ተለውጠዋል ። ግልጽ ለመሆን የ2017 ትርጉም ኢትዮጵያ
የሚለውን ቃል ብቻ አይደለም የቀየረው ። ብዙ ቃላትና ያገባብ ስህተቶችን አርሞ ተርጉሟል ። በተለይ "ኢትዮጵያ"
የሚለው ወደ "ኩሽ" መቀየሩ የሚያስደስት ሁኖ አግኝቼዋለሁ ። ምክንያቱም እኛ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያ በመጽሐፍ
ቅዱስ በመጠቀሷ የምንኮራ ነበርን ። እውነታው ግን የግሪክ ተርጓሚዎች በስሕተት የሕዝብ ስም ነው ብለው አስበው ነበር
። አሁን ያ አለመሆኑን አወቅን ። ለኩሽ ሕዝብ የተሰጠ ክብር የሚነካ የሚያዋርድ መጠሪያ ነበር ፣ በጀርመን ኢቫንጀሊካን
ሉተራን ቸርች ይህ ተለይቶ መታወቁን በማየቴ በጣም ደስተኛ ነኝ”
በእውነት እንዲህ አይነት ጥላቻ ያሳደረባቸው ምን ይሆን ? እንዴት ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ያላቸው ዕውቀት እጅግ
አናሳ መሆኑ አልታያቸውም ? ይህን ሁኔታ ያስጠኗቸው ሰዎች ኢትዮጵያ የሚለው ስም ስድብ ነው ብለው ስለ ሆነ ያንኑ
ጠላት ስድብ ነው ያላቸውን እርሳቸው ደግመውት ይሆንን? ለዚህ ያለ በቂ እውቀት በድፍረት ለተናገሩት አባባላቸውም
የኢትዮጵያን ታሪክ በተራ ዲስኩር ሳይሆን በማስረጃ የሚያውቁት ሊቁ ጌታቸው ኃይሌ የሚሉት አላቸው ፦
“.ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።” መዝሙረ ዳዊት - ም. 68 ቁ. 31 7