Page 12 - Ethiopia in the Bible by Abune Petros 2
P. 12

ኢትዮጵያ ከታሪክ ጥናት አንጻር




              ከታሪክ አዋቂዎችና ከባለ ቅኔዎች በመጠኑ እናንሣ ። ኢትዮጵያዊው የታሪክ ሊቅ ዶክተር ላጲሶ ድሌቦ በዚህ ዙሪያ
         ላይ ብዙ ሥራዎች አሏቸ ። አሁን ለዚህ አጭር ጽሑፍ የምጠቀመው ሁለቱን መጽሐፎቻቸውን ነው ።


              የመጀመሪያው  “የኢትዮጵያዊነት  ታሪካዊ  መሠረቶችና  መሣሪያዎች”  የሚለው  ነው  ።  ይኸኛው  ሥራቸው
         የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን የመነሻና የማንነት ግንዛቤ ከሚሉት ሥራዎቻቸው ውስጥ አራተኛው መጽሐፍ ነው ።

              ሁለተኛው  “የኢትዮጵያ  ረጅም  የሕዝብና  የመንግሥት  ታሪክ”  የሚለው  ነው  ።  ዶክተር  ላጲሶ  በዚህ  የታሪክ
         መጽሐፋቸው በመጀመሪያው ክፍል ላይ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ሲናግሩ ፦


              “በመጽሐፉ ተደጋግሞ “የኢትዮጵያ መንግሥት” ሲባል የሦስት ተዛማጅና የማይነጣጠሉ ነባርና ነዋሪ ሁኔታዎች
         ማለትም  ፦?የኢትዮጵያ  ምድር  ፥  ?የኢትዮጵያ  ሕዝብና  ፥  ?የኢትዮጵያ  የፖለቲካ  ሥርዓት  ታሪካዊ  አንድነት  ነው  ።
         የሕዝቦች ብዛትና ታሪካዊ መስተጋብር ማለት ነው ። ባጭሩ የኢትዮጵያ አንድ ምድር ፥ የኢትዮጵያ አንድ ሕዝብ ፥
         የኢትዮጵያ  አንድ  መንግሥት  ፥  የኢትዮጵያ  አንድ  ኅብረተ  ሰብ  ፥  የኢትዮጵያ  አንድ  ታሪክ  ፥  የመጽሐፉ  መሠረታዊ
         ትምህርት ነው” (ገጽ 10) ።


              በዶክተር  ላጲሶ  ትረካ  መሠት  ኢትዮጵያ  የሚለው  ስምና  አገር  አንድን  ነገር  ብቻ  የሚወክል  አይደለም።
         የሚወክለው ከአንድ ጥቁር ሕዝብ ከሚለው የላቀ ብዙ ትርጉም ያለው ሐሳብ ነው ። አንድ አገር የሚለውን ትርጉም
         የሚሰጠው አንድን ሰው ፥ ወይም ምድርን ብቻ አይደለም ፤ ብዙ ነገሮችንም ያካተተ ጉዳይ ነው ። ከዶክተር ላጲሶ
         መጽሐፍ  የምንረዳው  ይህንን  እውነት  ነው  ።  ዶክተር  ላጲሶ  ኢትዮጵያ  የሚባል  ምድር  ሕዝብና  መንግሥት  ከጥንት
         ጀምሮ የነበረ መሆኑን በማያሻማ መልኩ አስቀምጠዋል ። ከዚህ ስንነሣ ገና መጽሐፍ ቅዱስ ሳይጻፍ ይህ አገር ሕዝብና
         መንግሥት  ነበር  ማለት  ነው።  በመሆኑም  መጽሐፍ  ቅዱስ  ኩሽ  የሚለውን  የዕብራይስጥ  ቃል  ኢትዮጵያ  ቢሉ

         የሚወክለው ጠቅላላ አንድን አገር ሕዝብና በውስጡ ያሉትን መስተጋብር ጭምር ነው ። ስለዚህ ሰባ ሊቃናት የተባሉት
         የመጽሐፍ  ቅዱስ  ተርጓሚዎች  ኩሽ  የሚለውን  ቃል  ኢትዮጵያ  ብለው  መተርጎማቸው  እንደ  ዶክተር  ላጲሶም  ሐሳብ
         ትክክለኛ ሥራ ነው ።

              ዶክተር  ላጲሶ  በሌላው  መጽሐፋቸው  ሌላ  አስገራሚ  ሐሳብ  ገልጠዋል  ፣  የመጀምሪያው  አስገራሚ  ሐሳብ
         የኢትዮጵያ ሕዝብ ቋንቋና ባህል ሀገር በቀል ነው የሚል ነው ።


              ሁለተኛው ሐሳብ ኢትዮጵያውያን የኩሽም ሆነ የሴም ቋንቋዎችን የሚናገሩ ኢትዮጵያውያን ራሳቸው ከሌላ ስፍራ
         ተሰድደው  የመጡ  መጤዎች  አይደሉም  ይህ  ዘረኛ  ጀርመኖች  የጫኑብን  ነው  ብለዋል  ።  ዶክተር  ይህንን  የመሟገቻ
         ሐሳባቸውን ሲገልጡ ፦

              “በመሠረቱ የኢትዮጵያ ታሪክ ከሦስቱ መለኮታዊ  ሃይማኖቶች  ጋር እያያያዙ የኢትዮጵያን ታሪክ ከመካከለኛው

         ምሥራቅ የመጣ ነው ማለት ሚዛን አይደፋም ። የኢትዮጵያ ታሪክ ከመካከለኛው ምሥራቅ ታሪክ ቅድሚያ አለው ።
         ምክንያቱም  የአይሁድ  ታሪክ  ከአብርሃም  ከተነሣን  ያለው  ዕድሜ  4000  ዓመት  ነው  ።  የአፍሪካ  ቀንድ  ታሪክ  ግን
         ከአይሁድ ከሙሴና ከኖህ በፊት ነበር ፣ ሕዝቡም እዚሁ ምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ነበር ። ሙሴ ሲጽፍ በምሥራቅ አፍሪካ
         ያለውን ሕዝብ ፑንት ፥ በሱዳን ያለውን ሕዝብ ኩሽ ፥ በግብጽ የነበረውን ሕዝብ ግብጻዊ ብሏል ። እነዚህ ወንድማማች
         የሆኑ  ነባርና  ጥንታውያን  ሕዝቦች  በአካባቢው  መኖራቸውን  እንጂ  ከዐረቢያ  መምጣታቸውን  የሙሴ  ዘገባ
         አያመለክትም” /ኢትዮጵያዊነት፣ ገጽ 8/ ።





         “.ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።”   መዝሙረ ዳዊት - ም. 68 ቁ. 31                                                          12
   7   8   9   10   11   12   13   14   15   16   17