Page 15 - Ethiopia in the Bible by Abune Petros 2
P. 15

ሳያስነሣ ለምን ግዮንና ዓባይ ጥያቄ ሊያስነሣ ቻለ ? ለዚህ እነዶክተር በንቲና ሊቆቻቸው መልስ ቢሰጡን ደስ ይለናል ።
         በእኛ በኩል ዘረኛ ነጮች ኢትዮጵያ የሚለው አገርና ስም ሊዋጥላቸው ስላልቻለ ነው ብለን እንገምታለን ። መልሳችን

         ዶክተር ላጲሶ እንዳሉት ነው ።

               የግዮን ወንዝ የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከባል ይላል ። ይህ እንግዲህ ከቀለም ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ፣
         ምድሩን ነው ይከባል የሚለው ፣ የሚከበው ደግሞ በጣም ብዙ ምድር ነው ። ከጣና ሐይቅ እስከ ግብጽ አስዋን ግድብ
         ድረስ የሚደርስ ከአሥራ ሁለት ሽህ ማይልስ በላይ ርዝመት ያለውን ደጋና ቆላ፥ እንዲሁም የተንጣለለ የሱዳንና የግብጽን
         በርሃ የሚያካትት ምድርን ነው የሚገልጸው ። በየትኛውም መለኪያ የጥቁር ሕዝብ መኖሪያ ተብሎ ኩሽ ብሎ ለመተርጎም
         በቂ ምክንያት አይኖርም ። ኢትዮጵያ የሚለውን ኩሽ ማለት በፍጹም ሊሆን አይችልም ። ኩሽ የሚለውን ኢትዮጵያ
         ማለት ግን ስሜት የሚሰጥ ትርጉም ነው ። ምክንያቱም የኩሽ አንደኛው ትርጉሙ ምድር ወይም አገር የሚል ስለ ሆነ ነው
         ። ስለዚህ ዶክተር በንቲ ረጋ ብለው ያስቡበት እንላለን ። ኢትዮጵያ የሚለው ስም እንደ ሀገር ፥ እንደ ነገድና ፥ እንደ
         መጠሪያ ስም ሁኖ ተገልጧልና ።
               ኢትዮጵያ  እንደ  ሀገር  ሁኖ  ሲጠራ  ፥  በሀገሩ  አዋሳኝ  ደግሞ  ነጻ  መንግሥት  በመሆን  ተመዝግባለች  ።  መጽሐፈ
         አስቴር ይህን ሲገልጸው «በአርጤክስስም ዘመን እንዲህ ሆነ ፤ ይህም አርጤክስስ ከህንድ ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ

         በመቶ ሀያ ሰባት አገሮች ላይ ነገሠ» ይላል ። አስ 1 ፥ 1 ።

               ይኸው  ሐሳብ  በዚሁ  በአስቴር  መጽሐፍ  እንዲህ  ሲል  በግልጽ  ተቅምጧል  ።  «መርዶክዮስም  ስለ  አይሁድ
         እንዳዘዘው ሁሉ ከህንድ ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ በመቶ ሀያ ሰባቱ አገሮች ላሉ ሹማምትና አለቆች አዛውንትም
         ለእያንዳንዱም  አገር  እንደ  ጽሕፈቱ  ለእያንዳንዱም  ሕዝብ  እንደ  ቋንቋው  ለአይሁድም  እንደ  ጽሕፈታቸውና  እንደ
         ቋንቋቸው ተጻፈ» ይላል ። /አስ 8 ፥ 9/ ።


               በዚያ ጊዜ አንድ ከሞት  ተርፎ በነጻነት ሊኖር የሚችል አይሁዳዊ ካለ ኢትዮጵያ ከሚባለው  አገር  ብቻ ነው  ።
         ምክንያቱም የሞቱ አዋጅ ኢትዮጵያን አይመለከትም ነበርና ፣ ይህ ነው የነጻነት አገር የሚያሰኘው ።



               ኢትዮጵያ የተደራጀ የጦር ኃይል ያላት ታላቅ አገር ሁና ተገልጣለች ፦


               በዚያ ዘመን አንድ ሚሊዮን  ወታደር የሚቀልብ መንግሥት በምድር ላይ መኖሩን የሚጠራጠሩ ይኖሩ ይሆን  ?
         በዘመናችንም እኮ ሳዳም ሁሴን የበረሃው ጦርነት ጊዜ አንድ ሚሊዮን ወታደር አሰልፎ ነበር። በዚያ ዘመንም መጽሐፍ
         ቅዱስ ኢትዮጵያ የሚባል በጦር የተደራጀ መንግሥት እንደ ነበር እንዲህ ያስቀምጠዋል ፦ኢትዮጵያዊውም ዝሪ አንድ
         ሚሊዮን ሰዎችና ሦስት መቶ ሰረገሎች ይዞ ወጣባቸው ፤ ወደ መሪሳም መጣ ። /2ዜና 14 ፥ 9/ ።

               ይህ ጦር ሊወር የመጣው በታሪኩና በታማኝነቱ እግዚአብሔርን ያከበረውን አሳ የተባለውን ንጉሥ ለመውጋት ነው
         ። ይህን ኢትዮጵያዊ ንጉሥ ምን አነሳሥቶ ይህን እርምጃ እንዲወስድ እንዳደረገው አይታወቅም ፣ ግን ሊወጋው የሄደበት
         ንጉስ የእግዚኣብሔር ሰው ስለ ነበር ወደ ጦርነቱ ከመግባቱ በፊት ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቅ ነበር ማለት ይቻላል ።
         ቀጣዩ ክፍል ይህን ምሥጢር ሳይሸሽግ ይናገራል «አሳም ፦ አቤቱ ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህም ፤ አቤቱ
         አምላካችን ሆይ ፥ በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና እርዳን ፤ አቤቱ ፥ አምላካችን አንተ
         ነህ  ፤  ሰውም  አያሸንፍህ  ብሎ  ወደ  አምላኩ  ወደ  እግዚአብሔር  ጮኸ  ።  እግዚአብሔርም  በአሳና  በይሁዳ  ፊት
         ኢትዮጵያውያንን መታ ፤ ኢትዮጵያውያንም ሸሹ ። አሳም ከእርሱም ጋር ያለው ሕዝብ እስከ ጌራራ ድረስ አሳደዱአቸው
         ፤ ኢትዮጵያውያንም ፈጽመው እስኪጠፉ ድረስ ወደቁ ፥ በእግዚአብሔርና በሠራዊቱ ፊት ተሰባብረዋልና ፤ እጅግም ብዙ
         ምርኮ ወሰዱ» ይላል ። /2ኛ ዜና 14 ፥ 11-13/።


               መጽሐፍ ቅዱስ የፖለቲካ መጽሐፍ አይደለም ። የሌለንን ስም አይሰጠንም ። ያለንንም ስም አይቀማንም ። ይህ
         ከላይ የተጠቀሰው ታሪክ አስደሳች ታሪክ አይደለም ፤ ምክንያቱም የሽንፈት ታሪክ ነውና ።
               ሽንፈቱ  በሁለት  መንገድ  ነው  ።  የመጀመሪያው  የሰው  አገር  መውረር  ከሞራል  አንጻር  ትክክል  አይደለም  ።
         ሁለተኛው  በጉልበት  ግን  ደግሞ  ያለ  እምነት  የተደረገ  ስለ  ነበር  ነው  ።  መቼም  ቢሆን  ይህን  ታሪክ  ኢትዮጵያውያን





         “.ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።”   መዝሙረ ዳዊት - ም. 68 ቁ. 31                                                            15
   10   11   12   13   14   15   16   17   18   19