Page 16 - Ethiopia in the Bible by Abune Petros 2
P. 16
ጽፈውት ቢሆን አይመዘግቡትም ነበር ። ግን የእግዚአብሔርርን ሐሳብ ኢትዮጵያውያን ባይጽፉትም መንፈስ ቅዱስ
አስጻፈውና ሽንፈቱን እየመረረንም ቢሆን እንቀበላለን ።
አሁን እየሄድን ያለነው ኢትዮጵያ የምትባል አገር ላይ የሚኖሩ የተለያየ መልክና ቋንቋ ያላቸው ሕዝቦች አልነበሩም
የሚለውን ሐሳብ ለማምከን ነው ። በመሆኑም ይህን ታሪክ የምንመለከተው በቀለም ሳይሆን በሀገር ደረጃ የነበረን
መንግሥት በጦር ኃይል የበረታ ፥ በኢኮኖሚ የዳበረ ፥ አንድ ሚሊዮን ወታደር አሠልጥኖ የሚመግብ መንግሥት ኢትዮጵያ
በሚባል ምድርና አካባቢ የነበረ መሆኑን ለማሳየት ነው ።
ይህኑ ኢትዮጵያ የተባለ ቦታ እንደ ነበር ከነመልክዐ ምድሩ በአግባቡ ይገልጠዋል ። ይህኛው ሐሳብ የሚገልጸው
ለጦር የወጡ ወራሪዎች በኢትዮጵያ አዝማችነት የሊብያ ወታደሮችና ሰረገሎች ናቸው ፣ በበረሃው ማዕበል ጦርነት በአሜሪካ
መሪነት 35 አገራት እንደ ተሳተፉት ማለት ነው ። ልዩነቱ በኢትዮጵያ መሪነት የተሰለፈው ወራሪ ጦር ተመታ ፣ ለምን እንደ
ተመታ ታላቁ መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱሳችን እንዲህ ይላል “ኢትዮጵያውያንና የልብያ ሰዎች እጅግ ብዙ ሰረገሎችና ፈረሰኞች
የነበሩአቸው እጅግ ታላቅ ጭፍራ አልነበሩምን ? በእግዚአብሔር ስለ ታመንህ በእጅህ አሳልፎ ሰጣቸው” /2ዜና 16 ፥ 8/።
በእግዚአብሔር የታመነ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚመራውን የተባበረ ጦር አሸነፈ ። የእኛ ዋና ገለጣ ፥ ኢትዮጵያ የምትባል
አገር በላይኛው ግብጽ እስከ ህንድ ውቅያኖስ ድረስ ያለች ታላቅ አገር የነበረችና ያለች መሆኑን ለማሳወቅ ነው ።
ከዚህ ከኢትዮጵያ የተደራጀ ሀገራዊነት ማስረጃ ሳንወጣ ኢዮራም የተባለው ንጉሥ በመበደሉ ምክንያት በቅጣት
መልክ የተላኩበት ዐረቦችና ፍልስጥኤማውያን ሲነሡ ኢትዮጵያ በጉርብትና ተጠቅሳለች። ይህ ማለት ከግብጽ በመለስ
ያለው አገር ኢትዮጵያ የሚባል አገር እንደ ሆነ የሚያሳይ ነው ። ይህን ሐሳብ የአግዚኣብሔር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ
በማለት ይገልጸዋል ። “እግዚአብሔርም ፍልስጥኤማውያንንና በኢትዮጵያውያን አጠገብ የሚኖሩትን የዓረባውያንን መንፈስ
በኢዮራም ላይ አስነሣ”። /2ዜና 21 ፥ 16/ ።
ይህ ቃል ኢትዮጵያ የት እንደ ሆነች ለይቶ ያሳያል ፣ ፍልስጥኤምና ዓረቦች የተለዩ ቦታዎች ናቸው ። ይህን በደንብ
እንመልከተው ። ፍልስጥኤማውያንን በኢትዮጵያ አጠገብ ያሉ ዓረቦችን ፥ ፍልስጥኤም ከኢትዮጵያ ራቅ ያለች ፣ ዓረቦች
ደግሞ በጣም የቀረቡ ናቸው ። ይህ አሁንም ባለንበት ዘመን የመልክዐ ምድር አቀማመጥ ብንመለክት ከዚህ የወጣ
አይደለም ። ዐረብ ማለት ምድረ በዳ ማለት ስለ ሆነ ፥ ይህ አሁን ኢትዮጵያ ብለን በመጽሐፍ ቅዱስ ምስክርነት ያቆምንለት
አገር ከግብጽ በአንድ በኩል ከእስራኤል ጋር ግብጽን አልፎ የሚዋሰን መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ።
በሌላ ስፍራ ላይ ይኸው ኢትዮጵያ የሚባለው አገርና ሕዝብ ተዘልሎ በሰላምና በጸጥታ የሚኖር አገር እንደ ነበር
የነቢያቱ መጻሕፍት ያስረዳሉ ። የዚህ የነቢያት መልእክት ኢትዮጵያውያን እግዚአብሔርን የረሱ ሰዎች ይመስላሉ ፣ እንደ
ልብ የሚበላና የሚጠጣ ስላለ ሄሮዶቱስ እንዳለው የዳቦ ቅርጫት የወተት ጋን በሆነች አገር ይኖሩ ስለ ነበር ተዘልለው ይኖሩ
ነበር ። ከዚህ የዝለት እንቅልፍ ለመቅስቀስ እግዚአብሔር በመርከብ መልእክተኞችን እልካለሁ አለ ። ነቢዩ ሕዝቅኤል
እንዲህ በማለት ያውጃል ፦
“8 እሳትንም በግብጽ ባነደድሁ ጊዜ ረዳቶችዋም ሁሉ በተሰበሩ ጊዜ ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ ። 9
በዚያ ቀን መልእክተኞች ተዘልለው የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያንን ለማስፈራት ከፊቴ በመርከብ ይወጣሉ ፤ እንደ ግብጽም
ቀን ሁከት ይሆንባቸዋል ፤ እነሆ ፥ ይመጣልና” ። ሕዝ 30 ፥ 8-9 ።
መልእክቱ የመጣው በመንግሥት ለተደራጀ አካል ነው ። አብራ የተጠቀሰችው አገር ናትና ከፍ ሲልም የግብጽ ወዳጅ
ሁና የተጠቀሰች ተካፋይ ሁናለች ፣ ስለዚህ ይህ በግብጽ ላይ የመጣው አስደንጋጭ ወሬ ለኢትዮጵያ መሪዎች ማስጠንቀቂያ
ነው ።
ይገርማል ዛሬም እንኳ ግብጽና ኢትዮጵያ አንድ ጊዜ አብረው ሲበሉ ሲጠጡ ፥ ሌላ ጊዜ ሲወነጃጀሉ ይታያሉ ።
እነርሱ በዚሁ ስማቸው ጎረቤታሞች ሁነው ኑረዋል ። ኢትዮጵያ በመንግሥት የተደራጀች በዚያ ዘመን ከነበሩት አገሮች
እኩል ተሰሚነትና ኃይል የነበራት አገር ስለ ሆነች ይኸው መጽሐፍ ቅዱስ ከአካባቢ አገሮች ጋር አንድ አድርጎ አቅርቧታል
እና እነ ዶክተር በንቲና የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቆቻቸው የትኛው ሕዝብ ነው ይህን የሚወክለው? ኩሽ የተባለው አገር ያሁኑ
ሱዳን ያን ጊዜ ኑብያ በሚል ተጠርቷል ። የት ቦታ ላይ ነው ይኽንን ስም በአገር ደረጃ የሚያገኙት ? ጥቁር ከሆነ ጥቁር
ሕዝብኮ በዚያ ዘመን ይኖር የነበረ በኢትዮጵያ ብቻ አልነበረም ፥ በመካከለኛው ምሥራቅ ከነዓን የተረገመ ይሁን የተባለ እኮ
አሁን ፍልስጥኤም ከሚባለው አገር ነው የነበረ ። ለሞቃታማ አገር ከሆነ ዐረብ አገር ነበር ይህንን ስም መውሰድ ያለበት ።
ግን ሰብአ ሊቃናት ኢትዮጵያ የሚለው ይህ ቃል ለትርጉማቸው የተስማማ ሁኖ አገኙት ፥ እናም ተጠቀሙበት ።
“.ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።” መዝሙረ ዳዊት - ም. 68 ቁ. 31 16