Page 18 - Ethiopia in the Bible by Abune Petros 2
P. 18

እነዚህ በዚያ ተወለዱ» ። (መዝ 86 ፥ 4)።

              ከዚህ በተጨማሪ ከአጎራባች አገሮች ጋር ኢትዮጵያ ተብላ አገሯ ብቻ ለምሳሌ አሜሪካ ፥ እንግሊዝ እንደ ማለት
         አይነት ማለት ነው ፥ በዚህ አባባል ምንም አይነት የቀለም ጉዳይ የለም ። በዚህም ምክንያት ኩሽ የሚለው ትርጉም ለዚህ
         ሊስማማ  አይችልም  ።  በኢትዮጵያ  የሚኖሩ  ኩሻውያን  ካልተባለ  በእንግሊዝ  የሚኖሩ  ነጮች  እንደ  ማለት  ነው  ።
         በኢሳይያስ የተጠቀሰው ይህንን ያስረዳል ። «በኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ ላለች ፥ ክንፍ ያላቸው መርከቦች ላሉባት» ።
         ኢሳ 18 ፥ 1 ።

              ኢትዮጵያ ቦታ ብቻ ነው ። አሁን ኢሳይያስ ኢትዮጵያ የምትባል አገር በግብጽ አጎራባች ሁና የነበረች መሆኗን
         ሲያመለከት እንደዚህ በማለት ያስነብበናል «እግዚአብሔርም አለ ። ባሪያዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት

         ዓመት ለምልክትና ለተአምራት ሊሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ ፥ እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን
         ምርኮ ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን ፥ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ ፥ ለግብጽ ጕስቍልና
         ይነዳቸዋል ። እነርሱም ከተስፋቸው ከኢትዮጵያ ከትምክሕታቸውም ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ ያፍሩማል» ። ኢሳ 20 ፥
         3-5 ።

              ይኸ ኢትዮጵያ የሚባል አገር አሁን በሌላ ሳባ በሚባል አገር አጎራባች እንደ ነበር የሚያስረዳ የመጽሐፍ ቅዱስ
         ክፍል እንዲህ ይነበባል «እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ ፤ ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ ፥

         ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ»። (ኢሳ 43 ፥ 3)።

              አሁን ደግሞ ሁለት አገሮችን በአገር ደረጃ ሲጠቅስ እንዲህ ይላል ። «ፋርስንና ኢትዮጵያን ፉጥንም ከእነርሱ ጋር
         ጋሻና የራስ ቍርን የለበሱትን ሁሉ» ሕዝ 38 ፥ 5 ።


              በሌላ  በኩል  የናሆም  መልእክት  ሲነበብ  ደግሞ  «ኢትዮጵያና ግብጽ የማይቈጠር ኃይልዋ ነበሩ ፤ ፉጥና ልብያ
         ረዳቶችዋ ነበሩ» ይላል ። ናሆም 3 ።


              እነዚህ  ሁሉ  የተጠቀሱት  የአግዚአብሔር  ቃላት  በማያሻማ  ሁኔታ  ኢትዮጵያን  በአገርነት  ፥  ኢትዮጵያውያንንም
         በሕዝብ ደረጃ የተቀበሉ የማይለወጡ እውነተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት ናቸው ።

              ከዚህ ካለፍንም መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ጊዜ አሁን በአገር ደረጃ እኛ የምናውቃቸው በተለይም ይህ የአፍሪካ
         ቀንድ  ተብሎ  የሚጠራው  ከላይኛው  ግብጽ  ጀምሮ  እስከ  ህንድ  ውቅያኖስ  ያለው  አገር  የተለያዩ  ግዛቶች  ግን  በአንድ

         መንግሥት ኢትዮዮጵያ የሚል ስያሜ ያለው መንግሥትና አገር እንደ ነበር የዘነጉ ወይም ማወቅ የማይፈልጉ ሰዎች አሁን
         ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋላቸው አስገራሚ አስደናቂም ነው ።

              ከዚህ  ቀደም  በጉድ  ኒውስ  የመጽሐፍ  ቅዱስ  ኅትመት  የተመለከትነው  በተለይም  ኢትዮጵያን  ሱዳን  በማለት
         ያሳተሙትን በመቃወም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጊዜ 1977 ዓመተ ምሕረት ለአሜሪካ መጽሐፍ ቅዱስ
         ማኅበር የጻፉት ደብዳቤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ስደት እስከ ወጡብት ጊዜ ሲጻጻፉ ቆይተው ለዓለም መጽሐፍ

         ቅዱስ  ማኅበር  ባቀረቡት  አቤቱታ  ኢትዮጵያን  ሱዳን  በማለት  የታተመው  መጽሐፍ  ቅዱስ  እንዳይሰራጭ  ፥  ደግሞም
         እንዳይታተም የተደረገውን ጥረት የያዘው ሰነድ ዛሬም ይገኛል ።

              ይህ ኅትመት መነሻው ምን እንደ ሆነ በሰነዱ ላይ የዘረዘሩት ነገር የለም ። አሁን ደግሞ ሱዳንን ቀይሮ ኩሽ በማለት
         ባለተራዎቹ ስም አጥፊ የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት የገንዘብና የሞራል ድጋፍ የኢትዮጵያን የተገንጣይ አራጋቢ
         ቡድን  ይዘው  የተከበረውን  የእግዚእብሔር  ቃል  ኢትዮጵያን  የማጥፋት  ዘመቻ  መሣሪያ  አድርገውት  ይገኛሉ  ።  ይህን

         ተቀብለው  የሚያራግቡ  ኢትዮጵያውያን  ተብለው  መጠራት  የማይፈልጉ  የአካባቢው  ጥቂት  ሰዎች  የፖአለቲካ
         አዠንዳቸውን በፈለጉት መንገድ ማራመድ ይችላሉ ። በእግዚኣብሔር ቃል ላይ ግን እንዲህ ሊቀልዱና ሊዘባበቱ ከቶ
         አይችሉም ። ይህንን መልእክት የምናጠቃልለው በሁለት ዓበይት ነጥቦች ነው ።






         “.ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።”   መዝሙረ ዳዊት - ም. 68 ቁ. 31                                                          18
   13   14   15   16   17   18   19