Page 11 - Ethiopia in the Bible by Abune Petros 2
P. 11

የሚያስፈራ ታላቅ አገር ሲሆን ፥ ዋና ከተማውም “ሜሮ” እንደሚባል ገልጿል ።
              ዶ/ር በንቲ ያላቸው የተሳሳተ የታሪክ ግንዛቤ በሚከተለው ንግግራቸውም የሚታይ ነበር ። ለአንባቢ ይረዳ ዘንድ
        ጥያቄውን በሙሉ አስፍረነዋል ፦

              ጥያቄ ፤ በኢትዮጵያ በትምህርት ላቅ ባሉ (elite) ክፍሎችም ሆነ በሌላው ማኅበረሰብ ዘንድ ማንነትን በተመለከተ

        የተጋጋሉ ክርክሮች ይስተዋላሉ ። ብቸኛው ማንነታችን "ኢትዮጵያዊነት" ነው ብለው የሚከራከሩ አሉ ። በሌላው በኩል
        ደግሞ ቀዳሚው የጎሳ ማንነታችን ነው ፣ ኢትዯጵያዊነት ሁለተኛ ደረጃ ነው ብለው የሚከራከሩ አሉ ። ሌሎች ደግሞ
        ጭራሽ ባጠቃላይ ኢትዮጵያዊ ማንነትን የማይቀበሉ አሉ ። ለዚህ አነጋጋሪ ለሆነው የማንነት ጉዳይ ይህ አዲሱ ትርጉም
        አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለው ያስባሉ ?


              ማለት በቀላል አባባል ላስቀምጠው ብል ይህንን ብቸኛ ማንነታችን ኢትዮጵያዊ ነው ለሚሉና ለዚህ ተቃራኒ ለሆኑ
        ሰዎች ይህ ትርጉም የሚሰጠው ፋይዳ ምንድ ነው? እንደ ማለት ነው ።

              መልስ እውነት ነጻ ያወጣሃል ብየ አስባለሁ ። የመጀመርያው ስም "ኩሽ" ለመሆኑ ማስረጃ እስካለ ድረስ ቃሉ
        "ኢትዮጵያ"  ነው  ብሎ  የሚያከራክር  ምክንያት  የለም  ።  "ኢትዮጵያ"  ብለው  ሊጠሩን  ያስቻላቸው  ሳይንሳዊ  ማስረጃ
        አያገኙም  ይሆናል  ።  ሳይንሳዊ  ስል  የአርኪዎሎጂ  የሥነ  ቋንቋ  እንዲሁም  የታሪክ  ማስረጃዎችን  ማለቴ  ነው  ።  አሁን

        ስላለችው ኢትዮጵያ ታሪክ እንድነግርህ ፍቀድልኝ ። ከ1900-1908 እስከዚህ ጊዜ ድረስ የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ሥነ መልክዐ
        ምድር (ካርታ) አልነበረም ። ከዚያ በፊት ሕዝቡ ኦሮሞ ፤ አማራ ፤ ሲዳማ ፤ አፋር ፤ ትግሬ ወዘተ. ይባሉ ነበር ። አሁን
        ያለችው ኢትዮጵያ ካርታ ዳር ድንበር የተቋቋመው ፤ የተመሠረተው ፤ በዳግማዊ ምኒልክ የአቢሲኒያው ንጉሥ ነው ።
        የደቡብን ኩሾችና ሌሎችንም በቅኝ የያዘውና አሁን ያለችውን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ግዛት የፈጠረ ። እስከ 1931
        ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ሕጋዊ እውቅና አላገኘም ነበር ። ከ1931 ዓም በፊት ሀገሪቱ አቢሲኒያ ነበር የምትባለው ። እና
        አቢሲኒያውያን ራሳቸውን የሴም ሕዝብ ብለው ነው የሚጠሩት ። ንጉሥ ኃይለ ሥላሴ ናቸው በ1931 ዓም በመጀመሪያ

        ሕገ መንግሥታቸው ውስጥ አቢሲኒያ የሚለውን ስም ጥለው ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ያጸደቁት ።

              ለእውነት የቆሙ የሚመስሉት ዶክተር በንቲ ይህን አስጨናቂ ጥያቄ ለመመለስ የጀመሩት ብልጥነት የተሞላበት
        አባባል ፥ ግን ደግሞ መሬት የለቀቀ ውሸትን ለመዋሸት ታላቁን ቃል እውነትን ተግባሩን ሳይሆን ቃሉን ብቻ ተጠቅመው
        “እውነት ነጻ ታወጣችኋለች” አሉ ።


              እውነት  ዶክተር  በንቲ  እውነተኛ  ሰው  ናቸውን  ?  የተጠቀሙትን  ቃል  ተገንዝበውት  ይሆንን  ?  እውነት  እኮ
        የሚጨበት  የሚዳሰስ  የሚታይ  ነገር  ነው  ።  እንደዚህ  ቢያንስ  በመቶ  የሚቈጠሩ  ዓመቶችን  የሚታይ  የሚጨበጥ
        የሚዳሰሰውን ጉዳይ እኮ ነው “ኩሽ ለመሆኑ ማስረጃ እስካለ ድረስ ኢትዮጵያ ነው ብሎ የሚከራከር ማንነው” የሚሉት ።

              ደግሞም  የአርኪዎሎጂ  ማስረጃ  የሚሉት  ዶክተር  እስከ  አሁንም  የሚያምኑት  በመጽሐፍ  ቅዱስ  ላይ  ኢትዮጵያ
        የሚለው ቃል በሙሉ ኩሽ ነው መባል ያለበት ብለው ነው ። ከዚያ ሲያልፍም ኢትዮጵያ የሚለው አገር እንደ አገር

        የተመሠረተው በአቢሲኒያው ንጉሥ በአጼ ምኒልክ እንዲያውም ሀገሩ የተከለለው በአጼ ኃይለ ሥላሴ ነው እያሉን ነው ።

              እንዴት ያሳፍራል ! ያሳዝናልም ! አስገራሚም ነገር ነው !! ይህ መከረኛ ክርስቲያንነት የሁሉም የውሸት ምሽግ ሁኖ
        እያገለገለ ይገኛል ። እኔ ክርስቲያን ነኝ ፥ አገልጋይ ነኝ ፥ እውነተኛ አገልጋይ መሆን አለብኝ ማለታቸው እሚገርም ነው ።
        ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከመውጣቱ በፊት አማራ ፥ ትግሬ ፥ ኦሮሞ፥ አፋር ነበር የሚባለው ይሉናል ።

              እኛም እኮ መጽሐፍ ቅዱስ ከመጻፉ በፊት እነዚህን ሕዝቦች ያካተተ ኢትዮጵያ የሚባል አገርና መንግሥት ነበር

        ነው የምንለው ። ይህ ከዚህ በላይ በመጠኑ የተመለከትነው ከሥነ ልሳን አንጻር ሲሆን ። አሁነ ደግሞ ይህ ኢትዮጵያ
        የሚለው ስምና አገር ከታሪክ አንጻር ምን ይመስላል የሚለውን እንመልከት ።






         “.ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።”   መዝሙረ ዳዊት - ም. 68 ቁ. 31                                                            11
   6   7   8   9   10   11   12   13   14   15   16