Page 6 - Ethiopia in the Bible by Abune Petros 2
P. 6

በንቲ በሥነ ልሳን ሚዛን ላይ

              ዶ//ር በንቲ ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በየጊዜው ተስተካክሏል ፣ የማስተካከሉ ሂደትም የሚያካትተው የስምም
        የግንዛቤም መስተካከል ነው ። አሁንም በመካሄድ ላይ ነው ይላሉ ። እርሳቸው እንደሚሉት ፦ የግንዛቤና የሐሳብ ልዩነት
        ካለበት መጽሐፍ ቅዱስ እስክ አሁን እየተመራንበት ያለው በስህተት ነው የሚሉትን ሐሳብ እንመልከተው ፦

              “ግሪኮች ብሉይ ኪዳንን ከሂብሩ ቋንቋ ወደ ግሪክ ሲተረጉሙ "ኩሽ" የሚለውን ወደ "ኢትዮጲስ" በመቀየር ስህተት
        ሠሩ ። ኩሽ የጥቁር አፍሪካ ሕዝብ ስም ነበር ወደ ኢትዮጲስ ተለወጠ ። ትርጉሙ "ፊቱ የተቃጠለ ሕዝብ" ማለት ነው ።
        ኩሽ በመሆንና የተቃጠለ ፊት በመሆን መካከል ትልቅ ልዩነት አለ ። ጥቁር ሕዝቦች ፊታቸው የተቃጠለ አይደለም ።
        ጥቁሮች ናቸው በቃ ። ይህ አዲሱ በጀርመን ኢቫንጀሊካን ሉተራን ቸርች በ2017 የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ እነዚያን
        ስሕተቶች በማረም ነው ማለት ነው” ።

              ይህንን ገለጣ ከተቀበልነው በእርሳቸው አባባል የጀርመን ሉተራን ኢቫጀሊካን ቸርች ያረመው ስህተት  ኢትዮጵያ
        የሚለውን  ስሕተት  ኩሽ  በማለት  ማስተካከል  ነው  ።  ታረመ  የተባለው  ይኽ  ነው  ማለት  ነው  ።  ለዚህ  አመለካከት
        ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ለዚሁ ጽሑፍ የሰጡት መልስ አጥጋቢ ነው ብለን እናስባለን ፣ እርሳቸው ለዚህ ጽሑፍ የሰጡት
        መልስ በኢትዮ ሚድያ ድኅረ ገጽ ከወጣው የሚከተለውን አብረን እንመልከተው ፦


              “እነዚህ ሰባ (ሁለት) ሊቃናት ሲተረጉሙ ፥ ዕብራይስጡ ብሉይ ኪዳን ውስጥ የሀገርና የሕዝብ ስም ሲያጋጥማቸው
        አንዳንዱን ዕብራይስጡ ውስጥ እንዳለው ይወስዱታል ። አንዳንዱን ፥ ለምሳሌ እንደ “ኹሽ” እንደ “ፍልስጥኤም” ያሉ
        ስሞችን እንዳለ በመውሰድ ፈንታ ፥ የግሪክ ተመሳሳይ ስም ይሰጡታል ። (ፍልስጥኤምን “ኢሎፍሊ” ፥ ኩሽን “ኤይቲኦፕ”
        አሏቸው)  የዕብራይስጡ  “ኩሽ”  የሚያመለክተው  ጥቁርን  ሕዝብ  ነው  ።  ግሪኮች  ደግሞ  ጥቁሩን  ሕዝብ  የሚጠሩት
        “ኤይቲኦፕ” ብለው ስለ ሆነ ፥ “ኩሽ” የሚለውን ስም “ኤይቲኦፕ” ቢሉት አይገርምም ። ባጭሩ ፥ ግሪኩ  “ኤይቲኦፕ”
        የሚላቸው ዕብራይስጡ “ኩሽ” የሚላቸውን ሕዝቦች ነው”

              ይህ በንቲ ኡጁሉ አንደኛ “ኢትዮጵያ” ማለት በዚያ ዘመን ግሪኮቹ ጥቁርን ሕዝብ የሚጠሩበት የማንኛውም ጥቁር
        መጠሪያ ነው  ። ከዚያ ሲያልፍም በግብፅ በስተደቡብ የሚገኙ ሱዳኖችና ኢትዮጵያውያንን አንድ  አድርገው ኢትዮጵያ
        ብለው ነው ።

              ከዚህ በላይ እንደምንመለከተው የሰብዐ ሊቃናት ትርጉም የሕዝብና የሀገር ስም ሲገኝ አንዳንዱን ስሙን አንዳለ
        ወስደውታል አንዳንዱን ግን እነርሱ ይቀርባል ያሉትን የስም ትርጉም ሰጥተውታል ። እርግጥ ነው ፣ ዕብራይስጡ የሚለው
        “ שׁוּכ ኩሽ” ነው ። ፍቺውም ከምድረ ፍልስጥኤም በስተደቡብ ፣ ከላዕላይ ግብፅ ወይም ከደቡባዊ የናይል ሸለቆ ጀምሮ
                                 1
                                                                                                          2
        የሚገኝ ሕዝብ ማለት ነው።  ይኽንን የዕብራይስጡን ፍቺ የዕብራይስጥ ቅርብ የኾነው ሱርስትም ይጋራዋል።  ይኽንን
        የቆዳ  መልኩ  ጥቁር  የኾነ  ፥  ሀገር  ፥  መንግሥት  አቋቁሞ  በደቡባዊ  የናይል  ተፋሰስ  የሚኖር  ሕዝብ  ደግሞ  ግሪኮቹ
                                        3
        “አይቶፒዮስ” ብለው ይጠሩት ነበር።  ከራሳቸው ውጪ ያለውን ዓለም “ባርቤርያን” ብለው ለመጥራት ያልሰነፉት ኩሩዎቹ
        ጥንታውያን ግሪኮች ይኽንን ሕዝብ በሚመለከት የነበራቸውን አመለካከት ስናይ ዶ/ር በንቲ እንደሚሉት ቃሉ የስድብ
        ሁኖ አናገኘውም ። ለዚኽም ኢትዮጵያውያንን አማልክት የሚወዷቸው ሕዝብ አድርገው የሚያቀርቡት የሆሜር ቅኔዎች
        ምስክሮቻችን ናቸው ።
              በንቲ እንደሚሉት “ኢትዮጵያ” ማለት በፀሐይ የተቃጠለ ፊት ማለት ስለ ሆነ ጥቁርን ሕዝብ ለመስደብ የተሰነዘረ
        ቃል አይደለም ። “ኢትዮጵያ” የሚለው ቃልም  አንድ የተለየ  ጥቁር ሕዝብ መጠሪያ አይደለም ። ይልቁንም በጠቅላላ
        ከዓባይ ከላይኛው ግብጽ ጀምሮ ያለ ሕዝብ  ማለት  ነው ። በሌላ  አባባል፣ በዚያ ዘመን ግሪኮች ግንዛቤ    “ኢትዮጵያ”
        የሚለው ቃል የተለያዩ ሕዝቦች የሚኖሩበት ፥ ግን በአብዛኛው ጥቁር ሕዝብ የሚኖርበት ምድር ማለት ነው ።

              የአዲሱን  መጽሐፍ  ቅዱስ  ትርጉም  የሠሩት  ጀርመናውያን  ሊቃውንት  ብሉይ  ኪዳንን  የመለሱት  ከግሪክ  ሳይሆን
        ከዕብራይስጥ  ነው  ።  ዕብራይስጡ  ደግሞ  ቀድሞውንም  “ኩሽ”  ነው  የሚለው  ።  ስለዚህም  በአዲሱ  የጀርመንኛ
        ትርጉማቸው የዕብራይስጡን ስያሜ ቢጠብቁ ለዕብራይስጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ ያላቸውን ታማኝነት እንጂ ዶ/ር በንቲ

       —————————————————
       1
        Brown, Francis et al. The Brown-Driver-Briggs Hebrew and English Lexicon.Boston, Hendrickson Publishers, 2015
       2
         Michael Sokoloff. A Syriac Lexicon.Piscataway, Gorgias Press, 2006.
       3
         Liddel, Henery and Scott, Robert.A Greek- English Lexicon.Oxfrod, Clarendon Press,1940
         “.ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።”   መዝሙረ ዳዊት - ም. 68 ቁ. 31                                                          6
   1   2   3   4   5   6   7   8   9   10   11