Page 10 - Ethiopia in the Bible by Abune Petros 2
P. 10
ፕሮጀክት ተሠርቷል ብለውን ፣ አሁን ቃሉን የሚጠቀሙበት በዩንቨርሲቲ ብቻ ነው ያለው የሚል ክሕደት መቸም
ተሰምቶ አያውቅም ።
ኢትዮጵያ ዶ/ር በንቲ እንዳሉት የተወሰኑ ሰዎች ስም አይደለም ። ከላይ የጠቀስናቸው ምሁሩ አለቃ ኪዳነ ወልድ
ክፍሌና ሌሎችም ሊቃውንት እንደ መሰከሩት የብዙ ሕዝብና አገሮች ስምና ኑሮን ያጠቃለለ የአካባቢ ስም ነው ። ከዚህ
በተጨማሪም ፣ በዕብራይስጡ መጽሐፍ ቅዱስ “ኩሽ” የሚለው ቃል ያለው ፍቺና ዛሬ በዘመናችን ቃሉ ያለው ፍቺ አንድ
ዓይነት አይደለም ። ዛሬ “ኩሽ” የሚለው ቃል ያለው ፍቺ የመጣው ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የተነሡ የሥነ ልሳን
አጥኚዎች ቋንቋዎችን እያጠኑ በሚያቧድኑበት ጊዜ ተዛማጅ ላሏቸው ቋንቋዎች ከሰጡት ስም እንጂ ቃሉ በብሉይ ኪዳን
መጻሕፍት ውስጥ የሚወክለውን ሐሳብ ተከትለው አይደለም ።
ደጋግመን እንዳመለከትነው ፣ መጽሐፍ ቅዱስ “ኩሽ” በሚል ስም የሚጠራቸው ዛሬ “ኩሻዊ” ተብለው የሚጠሩ
ቋንቋዎችን የሚናገሩ ሰዎችን ብቻ ሳይኾን አጠቃላይ የራሱን ሀገረ መንግሥት አቋቁሞ በሰሜን ምሥራቅ አፍሪቃ ይኖር
የነበረን ጥቁር ሕዝብ ነው ። ይኽን ሕዝብ ደግሞ ግሪኮቹ “አይትዮፖስ” ብለው ይጠሩት ነበር ።
International Standard Bible Encyclopedia ይህኑ ቃል ለማብራራት ሞክሯል ። በዚህ
ኢንሳይክሎፒዲያ የተዘገበውም አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ከዘረዘሩት የተለየ አይደለም።
ቃሉ በራሱ ከሁለትና ከሦት በላይ ትርጉም አለው ። አንደኛው ብዙ አካባቢን የሚመለከት ሲሆን ኢትዮጵያ
የሚለውን ተጠቅሟል ። የሰውን መልክ በሚመለከት ኩሽ የሚለውን ተጠቅሟል ። አሁንም አገርን በሚመለከት ይህን
ኩሽ የሚለውን ሲጠቀም የኩሽ አገር የተባለው አሁን በንቲ ኩሽ ያሉትን አገር ሳይሆን ኩሽ የተባለው አገር የሚኖሩት
አሁን መስጶጦምያ የተባለውን የመካከለኛውን ምሥራቅ አገር አካሎ ነው ። አሁን ኢየሩሳሌምንም የሚያካትት ሰፊውን
ግብጽን ሁሉ የሚጨምረውን ነው ። በሌላ መልኩ ይኸው Encyclopediaን የጻፈው ሰው ፣ ኩሽ የሚለውን ቃል
ኩሲ ከሚለው የአንድ ሰው ስም ጋር ሲያገናኘው ይታያል ።
ለምሳሌ ሶፎንያስ «ወደ ሕዝቅያስ ልጅ ወደ አማርያ ልጅ ወደ ጎዶልያስ ልጅ ወደ ኵሲ ልጅ ወደ ሶፎንያስ የመጣ
የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው ። ሶፎ 1 ፥ 1 ።
ይህ ኢንሳይክሎፒዲያ የሚገልጸው ኩሽ የሚለውን ቃል ኩሲ እንደ ሆነ አድርጎ ነው ። ሐሳቡን ሲገልጠው e-th-
ioppe-e Heb kus’ gk Aithiopia geographical term ።
ኢትዮጵያ በዕብራይስጥ ኩሽ ፥ በግሪክ ኢትዮጵያ ። ይህን ቃል በጣም በብዛት የግለ ሰብ ስም እያደረገ ነው
የተጠቀመበት ። የጠቀሳቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ። ዘፍ 2 ፥ 13 ። ኢሳ 11 ፥ 11 ። ኤር 13፥ 23 ። 1ዜና 1 ፥ 8-10 ።
ኤር 36 ፥ 14 ። ኤር 38 ፥ 7-13 ።
ኩሽ የሚለውን ቃል ሲተርጉም ኢትዮጵያ ብሎ ነው የተረጎመው ። በተለይም አንዳንድ ተመሳሳይ ቃላትንም ከዚሁ
ጋር ተጠቅሟል ። ለምሳሌ በሶፎንያስ 1 ፥ 1 የኩሲ ልጅ የሚለውን ቃል ኩሽ ከሚል ቃል ጋር አዛምዶታል ። ኤርምያስ
36 ፥ 14 ። እንደዚሁ የሚል ነው ። አሁን እነዚህን ሁለቱን እንኳ ብናመዛዝናቸው በጣም የተለያየ ትርጉም ነው
የሚሰጡት ። ሶፎንያስ አንድና ኤርምያስ 36 ፥ 14 ፥ ኩሲ የተባለ የሰው ስም ሲሆን ፥ ይሄኛው ኤርምያስ 38 ፥ 7-13 ግን
ኢትዮጵያ ከሚባል አገር የመጣ የኢትዮጵያ ሰው ነው ። በስሙ ሳይሆን በአገሩ ነው የተጠራው ።
ስለ አካባቢውና የቦታው አቀማመጥ በዚሁ Encyclopedia መጽሐፍ የተጻፈ ሰፊ ክፍል ፥ ዝርዝር ዘገባ
ዘግቧል ። ከስድስት በላይ ፏፏቴዎች የተከበበ አካባቢ አድርጎ አቅርቦታል ። ግብጽ ፥ ኑብያ ፥ ሱዳን የሚለው ስም ኩሽ
በሚለው ስም ሲተረጎም የሚሰጠው ተተኪ ቃል ነው ። በዚህ ምድር የሚኖሩ ሰዎች ደግሞ ጥቁሮች ፥ ቀዮች ፥
ጠይሞችና የሕንድን መልክ የያዙ ሰዎች የሚኖሩባት ሀገር ናት ይላታል ። አገሮቹ በጠቅላላ ሲጠሩም ኢትዮጵያ የሚለውን
ስም ይሰጣል በማለት ሐሳቡን ያጠቃልላል ።
ከዚህ ተነሥተን ወደ ዝክረ ታሪክ ስንሄድ ፣ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም በኢትዮጵያነት የጠራው መጽሐፍ ቅዱስ
ብቻ ሳይሆን ፥ ከመጽሐፍ ቅዱስ በፊት የተከናውነውን ታሪክ የዘገበው ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን የተባለው የአይሁድ ታሪክ
ጸሐፊ ነው ። ይህ ታሪክ ጸሐፊ እንደሚለው ኢትዮጵያ የሚባል አገር ከግብጽ ቅጥሎ የተደራጀና ግብጽን በጦሩ
“.ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።” መዝሙረ ዳዊት - ም. 68 ቁ. 31 10