Page 47 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 47

እንደ ልጅነታችን እንተኛ



               መሬት  ላይ  ጉልበቶችዎን  በማሳረፍ፣ሆድዎን


               በጭኑ  ላይ  ያርፉ  እና  እጆችዎን  ወደ  ፊት

               በረጅሙ ይዘርጉ።



               ይህንን እንቅስቃሴ ለ 20 ሴከንዶች ያህል ይያዙ፡

               ፡ ይህ እንቅስቃሴ ጀርባዎን አቀማመጥ ጀርባዎን


               ፣  ትከሻዎን  እና  የሰውነትዎን  ጎኖች  በመዘርጋት  ሰዎነትዎ  ብቻ  ሳይሆን  አዕምሮዎም


               እንዲረጋጋና እንዲዝናና ይረዳል ፡፡






                                                   ግድግዳ ላይ እግሮችን መስቀል



                                                   ይህ  ሌላኛው  ሰውነትን  የሚያፍታታና  መንፈስን

                                                   የሚያድስ  እንዲሁም  አእምሮን  እርፍ  የሚያደርግ


                                                   እንቅስቃሴ  ነው፡፡


                                                   ይህ አቀማመጥ ዘና           ለማለት፣ ምቾትን ለማምጣት እና


                                                   ጭንቀትን  ለማስወገድ  ብዙዎች  የሚመርጡት  ነው  ፡፡

                                                   እንቅስቃሴውን  ለመጀመር  በጀርባዎ  መሬት  ላይ


               በመንጋለል  እግርዎን  ግድግዳ  ላይ  ይስቀሉ፡፡  አይንዎትን  ጨፍነው  ጥልቀት  ያለው  አየር


               በመሳብ  አተነፋፈስዎን  ያስተካክሉ፡፡  ሰውነትዎንም  ዘና  ያድርጉ፡፡  በዚህ  ሁኔታ  የቻሉትንና

               የፈለጉትን ያህል መቆየት ይችላሉ፡፡ ለምቾት እንዲሁም ጉዳትን ለመቀነስ ሲባል ምስሉ ላይ


               እንደሚመለከቱት ከጭንቅላትዎ ስር እንዲሁም ከወገብዎ ስር ፎጣ ወይም ትራስ ያኑሩ፡፡




                                                             44
   42   43   44   45   46   47   48