Page 45 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 45
ሱፐርማን
ለመጀመር ስዕሉ ላይ እንደሚያመለክተው በእጅዎ እና
በጉልበትዎ ይንበርከኩ፡፡ አንድ ክንድ ወደፊት እና
ተቃራኒውን እግር ወደኋላ በመዘርጋት እኩል ይለጥጡ፡፡
ለምሳሌ ቀኝ እጅዎን ወደፊት ከዘረጉ ግራ እግርዎን
ወደኋላ ይለጥጡ፡፡ ይህንን መልመጃ ከ20-30 ጊዜ ቀኝና
ግራ እያቀያየሩ ይስሩ፡፡ ይህ መልመጃ ሆድዎን ፣ ጭንዎን
እና የጀርባ ጡንቻዎችን ያጠናክራል ፡፡
ድልድይ
ይህን እንቅስቃሴ ለመጀመር በጀርባዎት መሬት ላይ
ከተኙ በኋላ ጉልበትዎን ወደራስዎት ስዕሉ ላይ
እንደሚያመለክተው ይንጋለሉ፡፡ በመቀጠል
ከመሬት ተረከዝዎትን ሳይነቅሉ ወገብዎትን
እስከቻሉት ድረስ ከፍ ያድርጉና አየር ላይ ይያዙት፡፡
ከዚያም መጀመሪያ ወደነበሩበት ሁኔታ ይመለሱ፡፡
ይህንን መልመጃ ከ10-15 ጊዜያት በመደጋገም
ይስሩ፡፡ ይህ መልመጃ ይሆድ እና የእግር ጡንቻዎች
ያጠናክራል።
42