Page 41 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 41

23.        በመደበኛነት  የአካል  ብቃት  እንቅስቃሴዎችን  ያድርጉ


                       ወይም በስፖርት    እንቅስቃሴዎች ላይ ይሳተፉ






               በኳራንታይን  ወቅት  እራስዎትን  ሲለዩ  ውይም  በቫይረሱ  ተይዘው  በሆስፒታል  ቆይታዎ


               ወይንም  ደግሞ  አካላዊ  ርቀትን  ለመገደብ  በቤትዎ  በሚቆዩበት  ወቅት  በአካል  ንቁ  ሆነው

               ይቆዩ፡፡



               የዓለም ጤና ድርጅት በሳምንት ውስጥ ለ 150 ደቂቃ ያህል መካከለኛ መጠን ያለው የአካል

               ብቃት  እንቅስቃሴ  ወይም  ለ75  ደቂቃ  ያህል  ጠንካራ  አካላዊ  እንቅስቃሴ  ወይም  ደግሞ


               የሁለቱም  ጥምረት  እንቅስቃሴ  እንድናደርግ  ይመክራል፡፡1    እነዚህን  ጤና  መመሪያዎችና

               ምክሮች በቤታችን ውስጥም ቢሆን ልዩ መሣሪያዎች ሳያስፈልሁንና በጠባብ ቦታዎች እንኳን


               ልናከናወናቸው እንችላለን፡፡ ቀጥሎ በኮቪድ 19 ወቅት አካላዊ መነቃቃትን እንዴት ማዳበር


               እንደምንችል የሚረዱ ምክሮች ይቀርባሉ፡፡  ከዚህ በፊት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርገው

               የማያውቁ ከሆነ ከአቅምዎት በላይ አካልዎን እንዳይወጥሩ ይጠንቀቁ ፣ የራስዎንም አቅም


               ውስንነት ይገንዘቡ ፡፡


               በቤትዎ  ውስጥ  ብዙውን  ጊዜዎን  የሚያሳልፉት  በመቀመጥ  ስለሚሆን                                        ፣  እርስዎ


               የመረጡትን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ቢያደርጉ ይመከራል፡፡ ይህ በምላሹ የአእምሮዎን /

               የአንጎልዎን ኃይል እና ንቁነት እና አጠቃላይ ጤና ያሳድጋል።











                 WHO. (2020). Global Strategy on Diet, Phsyical Activity and Health: Physical Activity and Adults . Retrieved
               1
               from Worl Health Organization: https://www.who.int/dietphysicalactivity/factsheet_adults/en/


                                                             38
   36   37   38   39   40   41   42   43   44   45   46