Page 36 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 36
16. ከዚህ በፊት ለማንበብ ጊዤ ያላገኙለትን መጽሐፍ
ያንብቡ
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል የሚባለው አባብል እውነት ነው፡፡
ብዙዎቻችን ከኑሮ ውጣውረድ፣ ከስራ ጫና እና ከጊዜ ማጣት
የተነሳ የምንወደውን የማንበብ ልምድ እርግፍ አድርገን
ትተነዋል፡፡ ነገር ግን አወቅነውም አላወቅነውም ኮቪድ 19
ካለምነው በላይ ጊዜ ሰጥቶናል፡፡ ስለዚህም ቤት ውስጥ
ተቀምጠን በጭንቀት ቀኑን ከምንገፋ እንዲሁም ዘመኑን
ከምናማርር እነዛን እንዳሉን እንኳን የረሳናቸውን መጽሃፎች
እናንሳና አቧራቸውን ጠርገን አእምሮአችንን በዕውቀትና
በጥበብ እንገንባ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ማንበብ የመቋቋም
ችሎታን ስለሚያበረታታ በዚህ ከባድ ጊዜ ትልቅ ጠቀሜታ
አለው፡፡
ትምህርት ቤቶች እንደመዘጋታቸው መጠን የልጆችም
ትምህርት አብሮ መዘጋት የለበትም፡፡ ስለዚህም ለልጆቻችን
የማንበብን ባህልና ጥቅም የማስተማሪያ እድሉ አሁን ነው፡፡
የሚወዱትን ትኩስ ወይም ቀዝቃዛ መጠጥ ከጎናችን
በምንወደው ኩባያ በማቅረብ፣ ስንፈልግ በቤት ውስጥ
በመረጥነው የተመቸ ቦታ አልያም ከቤታችን ውጭ በሚገኝ
ነፋሻማና አረንጓዴ ስፍራ በመሆን የንባብ ስሜት ልናነቃቃ
እንችላለን፡፡
33