Page 38 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 38

በተጨማሪም ብዙም ሳንርቅ ባቅራቢያችን ወደሚገኝ የዛፎች ክምችት ጫካ ውስጥ አረፍ


               ብንል  ውይንም  የወንዝና  የፏፏቴ  ድምጽ  ወደምንሰማበት  አካባቢ  ጎራ  ብንል  ያሉብንን

               ችግሮችና ጭንቀቶች በቀላሉ ልንረሳ እንዲሁም የፈጠራ ችሎታችንን ልናዳብር እንችላለን፡፡






                   18.        ሙዚቃን በማዳመጥ መንፈስዎን ያድሱ



               ሙዚቃ  የነፍስ  ቋንቋ  ነው፡፡  የእያንዳንዱ  ሰው


               የሙዚቃ ምርጫ ይለያይ እንጂ በሙዚቃ ውስጡ


               የማይረሰርስ መንፈሱ የማይፈነጥዝ የለም፡፡


               ሙዚቃ ማዳመጥ ጭንቀትንና የአእምሮ ውጥረትን


               ለማስታገስ  ይረዳል  ፡፡  ከዚህ  በተጨማሪ  ሙዚቃ


               ስሜትን  ሊያሻሽል  እና  በአጠቃላይ  የደህንነት

               ስሜትን  ሊረዳ  ይችላል።  እንደ  እውነቱ  ከሆን


               የሙዚቃ ቴራፒ ጭንቀትን ለመቀነስ ብዙውን ጊዜ

               ከሌሎች የስነ አእምሮ ቴራፒዎች ጋር በጥምረት ይሰጣል፡፡ እንደውም ብዙውን ጊዜ ሙዚቃ


               የመንፈስ  ጭንቀትን  ባፋጣኝ  ለማስወገድ  እና  ፈጣን  የስሜት  ማበረታቻ  ለመስጠት


               ተመራጩ መንገድ ነው፡፡


               ስለዚህም በተለይም በዚህ አስጨናቂ ጊዜ፣ ቀኑን ሙሉ የምንሰማቸው ወሬዎች ውጥረት


               በሆኑበት ወቅት በቀን ቢያንስ ለ1 ጊዜ የምንወደውን ሙዚቃ ብንሰማ ከቻልንም አብረን

               ብናንጎረጉር በከፍተኛ ሁኔታ ይረዳናል፡፡









                                                             35
   33   34   35   36   37   38   39   40   41   42   43