Page 37 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 37
17. ጠዋት ጠዋት መስኮትዎን ከፍተው የወፎች ጫጫታን
በመስማት፣ የጸሀይን መውጣት በመከታተል በመሳሰሉት
ተፈጥሮን ያዳምጡ
በተፈጥሮ ውስጥ መጓዝ ሺህ ተአምራትን
እንደመመስከር ነው ፡፡ተፈጥሮ ውስጥ አንዳች
ፈዋሽና አረጋጊ ነገር አለ ለዚህም ነው ብዙ የመንፈስ
ጭንቀት የሚያድርባቸው ሰዎች ከጭንቀታቸው
እፎይ ለማለት፣ በንዴት የሚንቦገቦጉ ሰዎች
ንዴታቸውን ለማስንፈስ፣ እንዲሁም ድብርት
ያጠቃቸው ሰዎች ድብርታቸውን ለማራገፍ የዛፎችን
ከለላ እና የወንዞችን ዋዜማ የሚመርጡት፡፡
ተፈጥሮን ለማድመጥ ከቤታችን ብዙ ርቀን መሔድ
አይጠበቅብንም ወደ ሰማይ አንጋጠን የሚያምረውን የጥጥ ባዘቶ የመሰለውን ደመና ብቻ
በቂ ነው፡፡ በጠዋት ተነስትን የወፎችን ዝማሬ
ብናደምጥ ቀናችን ብራ ሆኖ ይውላል፡፡ ማታ ማታ
የፀሃይን መግባት ብንመለከት ውይን የጨረቃና
የከዋክብትን ውበት ብናደንቅ የመንፈስ እፎይታን
እናገኛለን፡፡
34