Page 40 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 40
22. ቤትዎን እንደውዴታዎ ያስተካክሉ
በተለይም በአሁኑ ወቅት ብዙውን ጊዜያችንን በቤት ውስጥ እያሳለፍን ባለበት ወቅት
ቤታችንን እኛ በምንወደው መልኩ ማደራጀት እና ማስተካከል በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
የቤትዎ አለመስተጋክል እና መዝረክረክ በስሜትዎት ላይ ተጨማሪ ጫና ሊፈጥርብዎት
አይገባም፡፡
ብዙ ወጪ ሳያወጡ ቤትዎን ማስተካከል የሚችሉባቸው መንገዶች አሉ ይኸውም፦
የቤት ውስጥ አትክልት ያኑሩ
ደመቅ ያሉ ቀለሞችን ይጠቀሙ ለምሳሌ የሶፋ ትራስዎት ላይ
የተፈጥሮ የፀሐይ ብርሃን ወደ ቤትዎ እንዲገባ ያድርጉ
የቤትዎን ሽታ የሚቀይሩ ሽታዎችን ይጠቀሙ
የሥነ ጥበብ ውጤቶችን ልጌጥነት ይጠቀሙ
የልጆችዎን እና የሚወዷቸውን ሰዎች ፎጦዎች ግርግዳ ላይ በመስቀል ቤትዎን በፍቅር
ይሙሉ
ቆሻሻ መጣያ ቅርጫቶችን በየክፍሉ ያኑሩ ወ.ዘ.ተ...
37