Page 39 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 39
19. ጸሎት ማድረግ እና ሌሎችም የሃይማኖት
እንቅስቃሴዎችን ይተግብሩ
ብዙ ሰዎች እንደሚገልጹት በጭንቅ ሰአታቸው ወደፈጣሪያቸው ፊታቸውን ማዞርና ጸሎት
ማድረግ ትልቁ እርዳታችን ነው ይላሉ፡፡
20. ረዘም ያለ ሙቅ ውይም ቀዝቃዛ ሻወር እንደፍላጎትዎ
ይውሰዱ፡፡
ከፍተኛ ጭንቀት ሲሰማዎት እና ልብዎ ሲከብድብዎ እንዲሁም ሰውነትዎ ሲጫጫንዎ ሙቅ
ወይም ቀዝቃዛ የመረጡትን ረዘም ያለ ሻወር ይውሰዱ ፡፡ ጭንቀትን ጨምሮ ውሃ ሁሉንም
ቆሻሻዎችን ያስወግዳል ይባላል፡፡
21. ሰዎችን ይርዱ
ጭንቅ በያዘን ጊዜ ፣ በተለይም በአሁን ወቅት መከራ እንዲህ ሰፍቶ ስናይ የሌሎችን ፍላጎት
ለማሟላት እንዲሁም ሌሎችን ለመደገፍ ብንጥር የአእምሮ ሰላማችንን እናሰፋለን፡፡ በኮቪድ
19 ምክንያት እንደከዚህ በፊቱ አካላዊ ቅርርቦሽ የበዛበት ድጋፍ ለማድረግ ወይንም ብጎ
ፈቃደኛ መሆን ባንችልልም ዘመኑ ባመጣው የተለያዩ የፈጠራ ዘዴዎች በመጠቀም አሁንም
የህይወት አድን ስራ እንዲሁም ሌሎችን የመደገፍ ስራ መስራት እንችላለን፡፡
ሰዎችን መርዳት ወዲያውኑ የልብ ደስታን የሚፈጥር ፈጣን አማራጭ ነው፡፡ ስለዚህም
በዚህ ወቅት ህይወትዎን አደጋ ውስጥ ሳይጥሉ እና አካላዊ ርቀትዎን በጠበቀ ሁኔታ የተቸገሩ
ሰዎችን መርዳት የሚችሉበት መንገድ ይፈልጉ፡፡
36