Page 34 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 34
14. ከቤተሰብዎ ጋር ጊዜ ያሳልፉ
ብቸኝነት በራሱ ጭንቀትን ስለሚፈጥር
በተለይም በአሁኑ ጊዜ አካላዊና ማህበራዊ
ርቀትን ለመጠበቅ በምንገደድበት ወቅት
ከምንወዳቸው ቤተሰቦቻችን ጋር ጊዜን
ማሳለፍ አንድ ከስጋት፣ ከጭንቀትና ከፍርሃት
ራሳችንን የምንጠቀምበት መንገድ ነው፡፡ ቤት
ውስጥ አብረን ከምንኖራቸው ቤተሰቦቻችን
እንዲሁም ልጆቻችን ጋር የተለያዩ
ጨዋታዎችን በመጫወት፣ የአካል ብቃት
እንቅስቃሴዎችን በህብረት በማድረግ፣ አብሮ
በማብሰል፣ አዳዲስ የእጅ ሞያዎችን
በመማማር፣ አትክልቶቸን በመትከልና
በመንክባከብ፣ የቤትና የግቢ ጽዳቶችን
በማድረግ፣ የሰዎች ግርግር በሚቀንስበት ሰዓት አጠር ያሉ የእግር ጉዞዎችን በማድረግ፣
የሙዚቃ መሳሪያዎችን በመማር፣ ወዘተ... በማድረግ ጊዜያችንን ብናሳልፍ ለቤተሰባችን
ደስታን ከመስጠቱም በላይ ፍሬያማ ሊያደርግልን ይችላል፡፡
31