Page 30 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 30

9. በቀን ውስጥ ስለ ኮቪድ 19 የሚመለከቱትን ዜና ይገድቡ




               በቀን  ውስጥ  ስለ  ኮቪድ  19  በተመለከተ

               የሚነገሩ  ዜናዎችን  በገደብ ያድርጉ፡፡  በቀን


               አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ለተወሰነ ደቂቃዎች

               ብቻ  ይገድቡ፡፡  ለክ  አካላዊና  ማህበራዊ


               ርቀቶችን  በማድረግ  የኮቪድ  19ን  ስርጭት

               መቀነስ  እንደምንችለው  ሁሉ  በኮቪድ  19


               ምክንያት  የሚከሰት  ጭንቀትን፣  መረበሽን  እና  ውጥረትን  ለማስቆም  የሚዲያ  ርቀትን


               መተግበር እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡






               ኮቪድ  19ን  በተመለከተ  ተአማኝ  እና  አስተማማኝ


               የመረጃ  ምንጮች የሚመጡ  ዜናዎች  እና  መረጃዎች

               ላይ ትኩረት ያድርጉ፡፡ ለምሳሌ የአለም የጤና ድርጅት


               (WHO)፣  የበሽታ  ቁጥጥር  እና  መከላከያ  ማዕከል

               (CDC)፣  እና  ሌሎች  አካባቢያዊ  የዜና  ምንጮች


               ተገቢውን  መረጃ  ይሰብስቡ፡፡  እነዚህን  አስተማማኝ


               መረጃዎች  ከጓደኞችዎ  እና  ከሚወዷቸው  ሰዎች  ጋር

               መጋራት ይችላሉ፡፡



               ከኮቪድ 19 አስደንጋጭ  ዜናዎ ይልቅ በመዝናኛ ሚዲያዎች ላይ ትኩረት አድርጉ፡፡



               በተጨማሪ ከኬር ኢትዩጵያ ወይንም ከኬር ኢንተርናሽናል የሚሰጡ መረጃዎች እንዲሁም

               መመሪያዎች በሚገባ ይከተሉ፡፡


                                                             27
   25   26   27   28   29   30   31   32   33   34   35