Page 26 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 26

5. ቃላቶቻችሁን አድሱ




               ይህ  ልምምድ  ለራስዎ  ደጋግመው  የሚነግሩአቸውን

               አሉታዊ  ንግግሮች  ለማስቀረት  እና  በአዎንታዊ


               ማረጋገጫዎች ለመተካት ይረዳናል፡፡




               በችግር ጊዜ ቶሎ ወደ አሉታዊ እና ራስን የሚያወግዙ

               ቃላት ማምራት ይቀላል ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ራሳችንን


               ለመግለጽ  የምንጠቀማቸው  ቃላት  አዕምሮአችንን  እና  ስሜቶቻችንን  እንዲሁም


               ምግባራችንን የመቆጣጠር ኃይል እና ዝንባሌ አላቸው ፡፡




               በተለይም  በአሁን  ወቅት  በኮቪድ  19  ምክንያት  የተለያዩ  እንቅስቃሴዎቻችን  ተገትተው

               ባሉበት  ወቅት  የሚከተሉትን  ተስፋ  የሚያስቆርጡ፣  በራስ  የመተማመን  ችሎታን


               የሚያዘቅጡ፣ ራስን የሚያወግዙ እና ራስን የሚወቅሱ ንግግሮችን ማስወገድ አለብን፡፡





                     “በቤቴ ውስጥ ተቆልፎብኛል”
                     “ያለስራ በቤት ውስጥ መቅረቴ ነው”

                     “እስር ቤት ነው ያለሁት”
                     “ጭንቀቱ እና ድባቴ ሊገለኝ ነው”

                     ” ከቤት ሆኖ መሥራት በጣም ከባድ ነገር ነው”
                     “ሁሉም ነገር ከኔ ቁጥጥር ውጭ ሆኗል”
                     “ልጆቼ ሊያሳብዱኝ ነው”
                     “ይህን አመት ማለፌን እንጃ”

                     “ኮሮና ይዞኝ ከወደቅኩ አልነሳም”፣ ወ.ዘ.ተ…







                                                             23
   21   22   23   24   25   26   27   28   29   30   31