Page 22 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 22
2. የስሜት የቁጠባ አካውንት
በዚህ መልመጃ እርስዎን የሚያስደስትዎን ፣ ምን ማድረግ እንደሚወዱ ፣ ለእርስዎ የሚሆኑ
የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎችን፣ ጉልበት የሚሰጥዎትን ተግባራት እና ስሜትዎን የሚያነቃቁ
ነገሮችን የሚፈልጉበት ነው፡፡ ልክ እንደባንክ ስርዓት ብዙ መልካም ነገሮችን ለራሳችን
ስናደርግ ስሜታችንን በሚያረጋጉ ነገሮች ሃብታም እንሆናለን፡፡ ነገር ገን ሁሌ ተናዳጅና
ሀዘንተኛ ከሆንን የባንክ ተቀማጫችን እየተመናመነ እየተመናመነ ይሔዳል፡፡
ይህንን ልምምድ ለማድረግ የሚጠበቅብዎት
ብዕር እና ወረቀት ወስዶ በቁጣ ወይንም
በሃዘን ጊዜ ሊያረጋጉዎት የሚችሉ ነገሮች
ዝርዝር ምፃፉፍ ነው፡፡ ዝርዝሩን ከመፃፍዎ
በፊት በፀጥታ ለጥቂት ደቂቃዎች ተቀምጠው
ምን ከቁጣ እንደሚያበርድዎና ከሃዝን ስሜት
ጎትቶ እንደሚያወጣዎ ያስቡ፡፡ ሲጨርሱ
ማስታወስ የቻሉትን ያህል ዝርዝር ይፃፉ፡፡ተጨማሪ ለመጨመር በማንኛውም ሰዓት
ተመልሰው መፃፍ እንደሚችሉ አይጨነቁ።
በሄዱበት ቦታ ሁሉ ዝርዝርዎን በኪስዎ ወይንም በቦርሳዎ ይዘው በመሄድ ሀዘን ፣ ብስጭት
፣ ጭንቀት ወይም ንዴት በተሰማዎት ጊዜ ሁሉ የሚያስደስትዎትን ነገሮች ዝርዝር የያዘውን
ወረቀት በመመልከት እራስዎን ያረጋጉ፡፡ በተለይም በአሁኑ ጊዜ በኮቪድ 19 ምክያት ጭንቀት
በተጠናከረበት ሰአት ለስሜታችን አፋጣኝ ድጋፍ የሚሰጡ እነዚህ ዝርዝሮች መያዝ እጅግ
ጠቃሚ ነው ፡፡ በዝርዝሩ ላይ ያለውን ነገር ሊረሱት ስለሚችሉ ሁልጊዜ እና ከዚያ ዝርዝርዎን
እንደገና መጎብኘት ይመከራል።
19