Page 17 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 17
ሰዎች በኳራንቲን በሚቆዩበት ወቅት የተለያዩ አላስፈላጊ ስሜት ሊያጋጥሟቸው
ለምሳሌ
ይችላል፡፡ ከነዚሁም መካከል:-
ስጋት፡ ለእራሳቸው እና ለሌሎች ጤና መታወክ ጠንቅ እንዳይሆኑ መስጋት
ከሌሎች ሰዎች ጋራ ያለማህበራዊና አከላዊ ግንኙነት በመቋረጡ ምክንያት
መሰላቸትና ተስፋ መቁረጥ
በኳራንቲን ማእከሎች ውስጥ በቂ የመሰረታዊ ፍላጎቶች ባለመሟላታቸው ምከንያት
መበሳጨት ለምሳሌ (ምግብ፣ ዉሃ፤ አልባሳት እና የመጠለያአቅርቦቶችን በበቂ ሁኔታ
አለማግኘት)
ኳራቲንን በተመለከተ ስለ አላማው በቂ መረጃ አለማግኘት
ጭንቀት፣ ድንጋጤ፣ ድብርት፣ የመዋረድ ስሜት፣ ፍርሃት፤ ሃዘንተኝነት፤ ብቸኝነት፤
ንዴት፤ የእንቅልፍ እጦት፤ የመሳሰሉት ስሜቶችን ማስተናገድ
በተጨማሪም ስለ ቫይረሱ በቴሌቪዥን እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በተደጋጋሚ
መስማት ፣ የሚያገኘን ሰው ሁሉ የሚያወራልን ስለ ቫይረሱ በመሆኑ ፣ የወደፊቱን
አለማወቅና ስለወደፊቱ ስጋት እና ጥርጣሬ መግባት ፣ ሁኔታው ከአቅማችን እና
ልንቆጣጠረው ከምንችለው በላይ ሆኖ መሰማት ፣ ለቫይረሱ ህክምና ወይም ክትባት
አለመኖሩ… ወዘተ… ሰዎች ላይ ትልቅ ጭንቀትን ፈጥሯል ፡፡
ጭንቀት ሰውነታችን ለሚያሳስበን ነገር ተፈጥሯዊ ምላሽ የሚሰጥበት መንገድ ነው ፡፡
በተጨማሪም ጭንቀት ስለወደፊቱና ስለሚመጣው ነገር የሚሰማን የፍርሃት ስሜት ነው።
ማስታወስ ያለብን ነገር ቢኖር በተለይም በአሁኑ ወቅት አካላዊ ውሱንነቶች በበዙበት እና
የገንዘብ ችግሮች እያጋጠሙን ባለበት ጊዜ የመጨነቅ ስሜት እና ከቁጥጥር ውጭ እንደሆኑ
14