Page 12 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 12

የራስ እንክብካቤ




               አካላዊ ርቀትን መገደብና ግንኙነትን በገድብ ማድረግ



               ኮቪድ 19 የሚተላለፈው በቅርብ ርቀት ላይ

               የሚገኙ  ሰዎች  (በ2  ሜትር  ርቀት  ውስጥ)


               በሚያስሉበት  ወይንም  በሚያስነጥሱበት

               ወቅት       ከአፋቸው         በሚወጡ          የምራቅ


               ነጠብጣቦች           ሲሆን       ርቀትን       መገደብ


               የቫይረሱን  መራባት  ለማስቆም  ይረዳል

               በተቻለ መጠን በኮቪድ 19 የተያዙ ሰዎችን


               የሚያስታምሙ ሰዎች  እራሳችው  ከፍተኛ  ተጋላጭነት  ያላቸው  ለምሳሌ  ፦ አዛውንት  እና

               እንደ የስኳር በሽታ፣ የልብ ህመም፣ ሥር የሰደደ የመተንፈሻ አካላት በሽታ ፣ ካንሰር ያሉ እና


               ሌሎችም ሥር የሰደደ የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች መሆን የለባቸውም፡፡





               የታመመ ሰው ለብቻ መለየት



               በተቻለ  አቅም  በኮቪድ  19  ተይዘው  የታመሙ  ሰዎች  በቤት  ውስጥ  ካልታመሙ  ሰዎች


               መለየት ይኖርባቸዋል፡፡


                     የሚቻል  ከሆነ  የታመመው  ሰው  የራሱ  የሆነ  መኝታና  መፀዳጃ  እንዲኖረውና  በዛ


                       በተመደበለት  መኝታ  ክፍል  እስኪሻለው  ድረስ  እንዲቆይና  ከሌሎች  ጋር  ንክኪ

                       እንዳይኖረው ያድርጉ፡፡ በተቻለ መጠን የታመመውን ሰው ሲንከባከቡ 2 ሜትር ርቀት


                       በመሃል እንዲኖር ያድርጉ፡፡


                                                              9
   7   8   9   10   11   12   13   14   15   16   17