Page 14 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 14
አስታማሚዎች ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች
ደም ፣ ሰገራ ፣ ወይም እንደ ምራቅ፣ ንፍጥ ፣ ትውከት እና ሽንት የመሳሰሉትን
የሰውነት ፈሳሽዎች ጋር ንክኪ ከማድረግዎ በፊት ጓንት ያጥልቁ።
የተጠቀሙበትን ጓንት ካወለቁ በኋላ መዝጊያ ባለው ቆሻሻ ያስወግዱ፡፡ በመቀጠል
እጅዎትን በሳሙናና በውሀ በሚገባ ይታጠቡ ወይም በአልኮል ነክ የንፅህና
መጠበቂያዎች ያፅዱ፡፡
እንደ ኩባያ፣ ብርጭቆ ፣ ማንኪያ፣ ሹካ፣ ፎጣ ፣ ስልክ፣ እና መኝታ የመሳሰሉትን የገል
እቃዎች በጋራ ከመጠቀም ይቆጠቡ፡፡
ወደ ታማሚው ከፍል አስታማሚው እንክብካቤ ለመስጠት ከመግባቱ በፊት
የታመመው ሰው የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እንዲልበስ መጠየቅ ፡፡
አስታማሚም ጭምብል መልበስ መርሳት የለበትም፡፡
11