Page 18 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 18
መሰማት ምንም ማለት ያልሆነና የተለመደ ነው፡፡ ማድረግ የምንችለውን እንዳናደርግ
የሚያደናቅፈን ግን ከመጠን ያለፈ ፍርሃት እና ጭንቀት ነው፡፡
ጭንቀትን ጤናማ በሆነ መንገድ መቋቋም ከተቻለ እርስዎንም ሆነ የሚወዷቸውን ሰዎች
ብሎም ማህበረሰብን የበለጠ ጠንካራ ያደርጋል፡፡
ጭንቀት ጥሩ እና መጥፎ ጎን አለው ሲሆን ጥሩው ጎን አካላችንን እና ሕይወታችንን አደጋ
ላይ ሊጥሉ በሚችሉ ሁኔታዎች ውስጥ ስንሆን ሰውነታችን እንዲዋጋ (fight) ፣ እንዲበርር
(flight) ወይም እንዲቀዝቅዝ (freez) በማድረግ ይረዳል።
ሆኖም የጭንቀት መጥፎው ጎን ጭንቀት ሲቆጣጠረን ቋሚ በሆነ ፍርሃት ውስጥ
ስለምንዘፈቅ በእኛ ቁጥጥር ስር ያሉትን ነገሮች እንኳን እንዳናከናውን ፣ በእጃችን ላይ
ያለውን ማድረግ የምንችለውን ነገር እንዳናደርግ ያሳስረናል፡፡
15