Page 23 - ለ COVID 19 ህመምተኞች እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለሚገኙ የሚጠቅሙ ራስን የመንክባከቢያ ክህሎቶች
P. 23
ፍላጎትዎን ያማከለ የስሜት የቁጠባ አካውንት ለመገንባት የሚረዱ አንዳንድ ምሳሌዎች
እነሆ። ሆኖም ዝርዝሩን ሲጽፉ የሚያስደስትዎትንና ዘና የሚያደርግዎትን ነገሮች እንዲሁም
ልምምዶች ማሰብ አለብዎት። በጣም ቀላል እና የሞኝ ስራ የሚመስሉ ነገር ግን ሊያነቃቁ እና
ጭንቀትን እንድንቋቋም ሊረዱን የሚችሉ ድርጊቶች እንኳን ቢሆን በዝርዝር ይጻፉ።
እነዚህ የስሜት የቁጠባ አካውንት ውስጥ ሊያስገቧቸው የሚችሉ ምሳሌዎች ናቸው፦
ልብ ወለዶችን ወይም መጽሔቶችን ማንበብ
ቴሌቪዥን መመልከት
አዲስ የእጅ ሙያ ወይም የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ መማር
ማታ ማታ ከዋክብትን መመልከት
ሰማይን መመልከት
ፀሐይ ስትወጣ ለመመልከት እና ወፎቹ ሲዘምሩ ለማዳመጥ ጠዋት መነሳት
ፀሐይ ስትጠልቅ መመልከት
ከጓደኛዎ እና ከቅርብ ወዳጅዎ ጋር ማውጋት
ገላ መታጠብ
እንስሳትን መንከባከብ
ህጻናትን አቅፎ መሳም
ለብቻ ወይም በቡድን መዘመር ወይንም መዝፈን
ዛፎች ወደሚገኙበት ቦታ መሄድና የዛፎቹን እንቅስቃሴዎች በመመልከት
በፍጥረታቸው መደነቅ
ተፈጥሮን ማድነቅ
ስፖርታዊ ዝግጅቶችን በቴሌቪዥን መስኮት መመልከት
ስፖርታዊ ጫዋታዎች ውስጥ መሳተፍ
ይሚወዷቸውን የምግብ አይነቶች ማብሰል ወይንም አዳዲስ ሞያዎችን
መልመድ
አንዳንዴ ማልቀስ በሚያስፈልገን ወቅት የውስጣችንን በማልቀስ በእንባ
ማስወገድ
20